ሸጎዬ ሐረርጌ ዉስጥ የታወቀ ባህላዊ ዘፈን እና ዉዝዋዜ ነዉ።
ሸጎዬ ትርጉሙ ምን እንደሆነ እስከ ኣሁን ግምት ኣልነበረኝም።
ሰሞኑን ሸግዬ ከሚለዉ ቃል ጋር ተመሳሰለብኝ።
ሸጋ፣ ሸጌ፣ ሸጊቱ፣ ሸጎዬ፣ ሸግዬ ግጥምጥሞሽ ነዉ?
ቃሉ እና ቃልቻ ሐረርጌ ዉስጥ የተለመዱ ቃላት ናቸዉ።
ከኣሁን በፊት እንደጻፍኩኝ እኔ የማቀነቅነዉ የኢትዮጵያ እዴሳ ወይም ህዳሴ ከክርስትና እና ከእስልምና መቀበል በፊት የነበረዉ የኢትዮጵያ ባህል ላይ ብርሃን ቦግ ማድረግ ነዉ።
ከብዙ ዓመታት በፊት ዋሽንግተን ዲሲ ዉስጥ የተካሄደ ስብሰባ ላይ ድምጻዊዉ ቀመር ዩሱፍ ኣንድ ቁልፍ ጥያቄ ጠይቆ ነበር።
መካከለኛዉ ምስራቅ የሚባሉ በርካታ ሃገሮችን ተዘዋዉሮ ሲጎበኝ ቤተ ዘመድ ዉስጥ በሚደረግ ጋብቻ ምክንያት ብዙ ድኩማን ልጆችን ኣይቷል። የእኛ ሕዝብ ጥንት ግዜ የደረሰበት ምን ዕዉቀት ቢኖር ነዉ እስከ ሰባት ኣያቶች ቆጥሮ ማግባትን ባህል ያደረገዉ የሚል ነበር።
ጥያቄዉን ቃል በቃል ባላስታዉስም ጥያቄዉን ኣስታዉሳለሁ።
እዴሳ ይህ ጥንት ግዜ ጀምሮ ያለ ባህል መቼ እንደተጀመረ፣ ኢትዮጵያ ዉስጥ ከየት እስከ የት ባህል እንደሆነ ያጠናል።
እንደዚህ ዐይነት ከጥንት ግዜ ጀምሮ የሚተዋወቁትን የኢትዮጵያ ጎሳዎችን እንደገና እንዲጠያየቁ ይጋብዛል። ኣይጋብዝም?
ቦረና ዉስጥ ሞሮዋ የሚባል ጎሳ ኣለ ኣሉ። ሐረርጌ ዉስጥም ኣለ ኣሉ። ይህን ኣላረጋገጥኩም።
ባህር ዳር አከባቢ መራዊ የሚባል ስፍራ መኖሩን ሰምቻለሁ።
ኣንድ ግዜ በአጋጣሚ እንተርኔት ዉስጥ የጎንድር ባህል ዘፈን የተባላ ሸጎዬን የሚመስል ኣይቻለሁ።
እ አ አ በ1991 ሐረርጌ ዉስጥ እስከዛ ግዜ ድረስ ሰዎች እራሳቸዉን ሙስሊም እንጂ ኦሮሞ ብለዉ ኣይጠሩም ነበር ኣሉ።
ከጥቂት ኢትዮጵያዊያን በስተቀር ብዙዎቹ አዋቂዎች ነን የሚሉት የሚመሳሰሉትን የተለያዩ ናቸዉ ብለዉ ይሰብካሉ።
ለምሳሌ ሸጎዬ እና ሸግዬ ተመሳሳይ ናቸዉ ወይስ የተለያዩ ናቸዉ? እኔ እርግጠኛ የሆነ መልስ ዬለኝም። እርግጠኛ መልሱን ለታሪክ ተመራማሪዎች እተዋለሁ።
የእኔ አጭር ጥያቄ ይህቺን የታሪክ ጥያቄ በእርግጠኝነት መመለስ የምትችሉ የኢትቶጵያ የታሪክ ምሁራን ዬት ናችሁ ነዉ።
እንደዚህ ዐይነት ጥያቄዎችን በእርግጠኝነት መመለስ የሚችሉ ምሁራን ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ተመሳሳይ የታሪክ ዕዉቀት እንዲኖራቸዉ ማድረግ ይችላሉ። ተመሳሳይ የታሪክ ዕዉቀት ያላቸዉ ዜጎች ለሃገር እድገት ተመሳሳይ ትብብር ይኖራቸዋል።
ኣንዴ አክሱም ሴም ነበረ፣ ሌላ ግዜ አክሱም ኩሽ ነበረ፤ ኣንዴ የጎንደር ኣፄ አማራ ነበረ ፣ ሌላ ግዜ ኦሮሞ ነበረ፤ ኣንዴ ወለጋ ኦሮሞ ነዉ፣ ሌላ ግዜ ወለጋ ቢዛሞ ነበረ፣ ወዘተ ከሚሉ ዉዝግቦች በማዉጣት ማለት ነዉ።
Re: ሸጎዬ ምን ማለት ነዉ?
ሸጎዬ እና ሸግዬ ማለት ምን ያህል እንደሚመሳሰሉ ካስተዋልኩኝ ወዲህ መርሳት ኣልቻልኩም።
ከሁሉም በላይ የደነቀኝ ሁለቱም ቃላት ዉስጥ ዬ እንደተቀጽላ መሆን ነዉ።
ከኣሁን በፊት የቃሉ እና ቃልቻን መመሳሰል ካስተዋልኩኝ ግዜ በላይ ነዉ ይህኛዉ የደነቀኝ።
የሸጎዬ እና የሸግዬን መመሳሰል ኣስተዉዬ የነበረ ቢሆን ስለ ሸጎዬ ባህል በደንብ የምያዉቀዉን ድምጻዊዉ መሓመድ ሼካ እንድያዝናና ያስተባበርኩኝ ግዜ እጠይቀዉ ነበር። ሌሎች ኣዲሱ ሀይማኖታችን ባህልን ከልካይ ነዉ ብለዉ ሲሰብኩ የነበረ ግዜ ነበር መሃመድ ሼካ ተጋብዞ በሸጎዬ ባህል ያዝናናዉ።
ሐረርጌ ዉስጥ ብዙ ግዜ የተንቀሳቀሰዉ ኦነግ ሸጎዬ እያልን ሸግዬ እያሉ፣ ቃሉ እና ቃልቻ እያልን ቃልቻ እያሉ ምንድነዉ የምንታገለዉ ብሎ እራሱን እየጠየቀ ነበር ሲንቀሳቀስ የነበረዉ? ለምን ነበር ቃሉ እና ቃልቻ መሠረታቸዉ ኣንድ ሊሆን ይችላል ከማለት የተለያዩ ናቸዉ ብሎ ሲሰብክ የሰነበተዉ?

አዲ፣ ኣዲስ፣ እዴሳ፣ ህዳሴ ብዙ ሀሳቦችን ያመጣሉ።
እዴሳ ማለት ህዳሴ ከማለት መብራራት የሚችል ይመስለኛል።
እዴሳ እንደ enlighten ሊሆን ይችላል።
Light በግሪክ ቋንቋ leukós (ለኩስ) መሆኑን ዲክሽነሪ ዉስጥ ኣነበብኩኝ።
ለኩስ ማለት ኣብራ ማለት ነዉ። ብርሃን ይሁን ማለት ነዉ።
Enlighten እንደዛዉ ማለት ነዉ።
አዉሮፓ ዉስጥ enlightenment movement የተባለዉ እንደዚህ አይነት ጥናትም ነበር።
የሸጎዬ እና ሸግዬ መመሳሰል ኣንዱ ከሌላዉ ተዉሶ ነዉ ወይስ መሠረታቸዉ ኣንድ ቢሆን ነዉ?
ሸጎዬ ስለ ጎረምሳ እና ኮረዳ ጓደኝነት ነዉ።
አዶዬ ስለ ኮረዳዎች ጓደኝነት ነዉ።
ምቹ ስለ ወንዶች ጓደኝነት ነዉ።
ኣዴ በኦሮምኛም በትግርኛም ዉስጥ ያለ ቃል መሆኑን ኣዉቃለሁ።
ኣዴ እና አዶዬ መሠረታቸዉ ኣንድ የሆነ ቃላት ይመስላሉ።
እንደዚህ አይነት ጥናት ባህል ተመልሶ እንድያብብ ያደርጋል።
ስለ ሸጎዬ እና ሸግዬ መመሳሰል ካስተዋልኩኝ ወዲህ አሊ ብራ እና ማህሙድ ኣህመድ ሸጎዬ እና ሸግዬ እያሉ ኣንድ ላይ ዘፍነዉ በነበረ እላለሁ።
ገዳን በዴ ዴብቴ ብሎ የዘፈነዉ ቀመር ዩሱፍ ሸግዬ የሚልን ዘፋኝ ፈልጎ ኣብረዉ ሸጎዬን እና ሸግዬን ቢዘፍኑ ኣዳንስ ስርናን ዴብቴ ማለት ይችል ይሆናል።
ገዳን በዴ ዴብቴ ኣለ፣ ወጀጋ ወይ አከ ወጀጋ ቁሉቢ ሰነ። ገዳን ዬሮ ከበጀሙ እጆሉማት አርጌረ። ህን በኔ ቱሬ። ናኖ እት ሀፌ ቱሬ።