Page 1 of 1
Ankara Declaration & MOU
Posted: 05 Jan 2025, 14:15
by Horus
Re: Ankara Declaration & MOU
Posted: 06 Jan 2025, 12:25
by Za-Ilmaknun
"ዕውቅና ለማግኘት ሲባል ወደ ሲኦል አናመራም" የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
የመግባቢያ ስምምነቱን የፈረሙት የቀድሞው የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ እና የኢትዮጵያ መንግሥት "ስምምነቱን አስመልከቶ የሚናገሯቸው ጉዳዮች እርስ በርስ የሚጣረሱ ናቸው" ሲሉ ሚኒስትሩ አብዲራህማን ዳሂር አደን አስረድተዋል።
"እነሱ [ኢትዮጵያ] የባህር ጠረፍ ስናገኝ ነው ስለ ዕውቅናው የምናስበበት ነው የሚሉት። ለሶማሊላንድ ዕውቅና እንሰጣለን ያሉበት ቦታ የለም" ሲሉ ሚኒስትሩ ከፓርላማው የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ስምምነቱን አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።
ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር የመግባቢያ ስምምነቱን የፈረመውን የሶማሊላንድ መንግሥት የተካው የአዲሱ አስተዳደር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እርሳቸውም ሆነ ፓርላማው የመግባቢያ ስምምነቱን መፈተሽ ይገባናል ብለዋል።
"ለዕውቅና ስንል ሁሉንም ነገር እናደርጋለን ነገር ግን ለዕውቅና ሲባል ወደ ሲኦል አናመራም እንዲሁም ህዝባችንን አናጠፋም። ዕውቅናው የሶማሊላንድን ጥቅም እና የዚያችን አገር [ዕውቅናውን የምትሰጠው አገር] ጥቅም ባጣጠመ መልኩ ሊሆን ይገባዋል" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።
አክለውም "ዕውቅና ሰጥተናችኋል ለማለት ሃገራችንን ለሌላ አገር መሸጥ እንዲሁም ሃብታችን እና ህይወታችን ሌሎች እንዲቆጣጠሩ ማድረግ ትርጉም የሌለው ነው" ሲሉ አክለዋል።
ስምምነቱን ተከትሎ የሶማሊያ የማስታወቂያ ሚኒስትር ዳውድ አዌይስ ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የተፈራረሙት የመግባቢያ ሰነድ "ሙሉ በሙሉ ውድቅ ተደርጓል" ብለዋል
https://www.bbc.com/amharic/articles/cge9llldzj2o
Re: Ankara Declaration & MOU
Posted: 06 Jan 2025, 18:56
by Somaliman
Let Horus keep beating the dead horse.
