Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Meleket
Member
Posts: 4796
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

አቡነ ተክለሃይማኖት፡ ተስፋዬ ገብረአብ፡ ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን፡ ዓወል ስዒድን፡ . . . . እንኪምርመሩ

Post by Meleket » 04 Jan 2025, 03:35

እዚ ጽሑፍ ዕምቖት ዘለዎ፡ ብዛዕባ ኣቡነ ተክለሃይማኖት ብዙሕ ጭብጥታትን ትንታነን ዝሓዘለ ኢዩ። ጸሓፊኡ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ኢዩ። ትሕዝቶኡ፡ ነፍስኄር ደራሲ ኤርትራዊ ተስፋዬ ገብረኣብ፡ ናይ ፍስሓጽዮን ፖለቲካ ዚብል አርእስቲ ሂቡ ብዛዕባ ኣቡነ ተክለሃይማኖት ኣብ ዝጸሓፎ ጽሑፍ ሰለስተ ተክለሃይማኖታት ኔሮም ቢሉ ንዝጸሓፎ ጽሑፍ ስነፍልጠታዊ ምላሽ ንምሃብ ዘድሃበ ኢዩ። ዓለም ዕንክሊል ነፍሲኄር ደራሲ ተስፋዬ ገብረኣብ፡ ብዛዕባ ኣቡነ ተኽለሃይማኖት ዝመሰሎ ጽሒፉ፡ ዕምሪ ምስተወደኣት ድማ ሓመድ ድበ ዚለበሰሉ ቤተክርስትያን ኣቡና ተኽለ ሓዝሓዝ ከምዝዀነ ምስፈለጥና፡ ጸሎት አዲኡ ከምዝሰመረ ጥራሕ ዘይኰነስ ጻድቓንስ ድኣ ጻድቃን፡ ቅዱሳንስ ድኣ ቅዱሳን፡ ንደቆም ዚእክቡ ቢልና ንክንምስክር አኽኢሉና።

ከምቲ ሕጂ ንሰምዖ ዘሎና፡ ተር ከምዓተር ብዓበይቲ ዓዲ ሕዝቢ ኤርትራ ዝጀመሮ ጸለመ ብምቅጻል ዓወል ስዒድ ድማ ብዛዕባ እዞም መንፈሳዊ ኣቦ ዚፈልጦን ዘይፈልጦን ዓዘፍዘፍ ቢሉሎ ኪበሃል ነቢብና። በዚ በለ በቲ ከምቲ ናይ መረጃ ኣሰግድ ዚብሎ “ዘየንብብ ካድረ፡ ኩሉ ነገር ዘይተጻሕፎ ይመስሎ” ከምዚበሃል፡ እስከ ነዚ ዘየንብብ ካድረ፡ እዚ ጽሑፍ ብትግርኛ ቀይርኩም ንበቡሉ፡ ደቂ እምነትን ደቂ ማእከለ ምድሪ ባሕሪን ሕዝብኩም መሃሩ! ቢዝብል ኣተና ንሕና ኤርትራዉያን ደያኑ ማእከልን መስመርን ብኤርትራዊ ጭዉነት ሓበንን ፍናንን ነዚ ብርቂ መጽናዕታዊ ጽሑፍ ነካፍለኩም ኣሎና። እዚ ቀዳማይ ክፋል ኢዩ፡ ካልኣይ ክፋሉ ድማ ዚያዳ ንአቡና ተኽለ ምስ ቦለቲካ ከተሓሕዙ ንዚፍትኑ ከም በዓል ዓወል ስዒድ ዝኣመሰሉ ነገር አንጀብረርቲ ትምልከት ኢያ እሞ ህድእ ኢልኩም መታን ከተንብብዋ ኪነስዕብለኩም ኢና። ነዚ ጽሑፍ ንክብሪ አቡነ እንጦንዮስ ክንውፍዮ እንከሎና ነዚ ምርምር ንዝቐረበልና ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ልዑል ምስጋናና ብምቕራብ ኢዩ።

ብሩኽ በዓለ ልደተ ክርስቶስ!

የሌለውን ፍለጋ -ክፍል አንድ
ተስፋየ ገብረ አብ ‹የስደተኛው ማስተዋሻ› የተሰኘ መጽሐፍ ማውጣቱንና ባነበው መልካም እንደሆነ ገልጦ አንድ ወዳጄ ‹ስስ ቅጅውን› ከሀገረ አሜሪካ ላከልኝ፡፡ ከዚህ በፊት ሌሎች መጻሕፍቱን አንብቤያቸዋለሁ፤ በአጻጻፍ ችሎታው የምደሰተውን ያህል እንደ አበሻ መድኃኒት ነገሩን ሁሉ እርሱ ብቻ የሚያውቀው ምስጢር ስለሚያደርገው፤ በአንዳንድ ጉዳዮችም ሆን ብሎም ሊያናጋቸው የሚፈልግ ኢትዮጵያዊ እሴቶች ያሉ ስለሚመስለኝ፤ ተስፋዬ ለምን እንደዚህ ይጽፋል? እያልኩ የምጠይቃቸው ነገሮች ነበሩ፡፡

በዚህ መጽሐፉ ውስጥም ያንን ጥርጣሬየን አጉልቶ ሥጋ ነሥቶ እንዳየው የሚያደርገኝ ነገር ገጠመኝ፡፡ ተስፋየ በገጽ 306 ላይ ‹‹የፍስሐ ጽዮን ፖለቲካ› በሚል ርእስ ስለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የማያውቀውን ነገር ጽፏል፡፡ ስለማያውቀው ነገር የጻፈው ባለማወቁ ብቻ አይመስለኝም፡፡ አንድም ለማወቅ ባለመፈለጉ፣ አለያም ሆን ብሎ የማፍረስ ዓላማ ይዞ ይመስለኛል፡፡

ይህን የምለው በሁለት ምክንያት ነው፡፡ ተስፋዬ ስለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ለመጻፍ ሲፈልግ ሊያነባቸው የሚችላቸው መጻሕፍት በምድረ አውሮፓ እንደ ማክዶናልድ በዝተው ሞልተው ይገኛሉ፡፡ አብዛኞቹ ደግሞ ኢትዮጵያውያን ባልሆኑ ሰዎች የተጻፉ ናቸው፡፡ ሌላው ቢቀር ኤንሪኮ ቼሩሊ የደብረ ሊባኖስ አበ ምኔቶች ታሪክ(Gli Abbati di Dabra Libanos, 1945)፣ ኮንቲ ሮሲኒ ከሐተታ ጋር ያሳተመውን ገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣በዋልድባ ቅጅ (Il Gadla Takla Haimanot secondo la redazione Waldebbana, 1896)፣ የዊልያም በጅን የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ሕይወትና ተአምር (The Life and Miracles of Takla Haymanot, 1906)፡፡ ከኢትዮጵያውያን ጸሐፍትም ውስጥ የታደሰ ታምራትን Church and State in Ethiopia, ማንበብ በተገባው ነበር፡፡

ከዚህም ዘልሎ ጥልቅ ጥናት አድርጌ ደረቴን ነፍቼ እናገራለሁ ለሚል ደግሞ እንግሊዝ ምቹ ናትና ሎንዶን ወደሚገኘው ብሪቲሽ ሙዝየም ሄዶ በማይክሮ ፊልም የተነሡትንም ሆነ በአካል ያሉትን ብራናዎች ማየት ነው፡፡ እዚያም የማያደርሰው ከሆነ በዋና ከተማው በሆላንድ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙትን የጌታቸው ኃይሌን THE MONASTIC GENEALOGY OF THE LINE OF TÄKLÄ HAYMANOT OF SHOA, (Rassegna di Studi Etiopici, Vol. 29 (1982-1983), pp. 7-38)፤ የተስፋዬ ገብረ ማርያምን A Structural Analysis of Gädlä Täklä Haymanot(African Languages and Cultures, Vol. 10, No. 2 (1997), pp. 181-198)፤ የሐንቲንግ ፎርድን (G.W.B. Huntingford, "The Lives of Saint Takla Haymanot," Journal of Ethiopian Studies, 4(1966), 34-35.) የአሉላ ፓንክረስትን Dabra Libanos Pilgrimage Past and Present, The Mytery of the Bones and the Legend of Saint Takla Haymanot,(the sociology ethnology Bulletin) 1,3 (1994), P. 14-26ጥናቶችን ማየት ይቻል ነበር፡፡ ያም ካልሆነ ወደ ቤልጅየም ሄዶ ፒተርስ አሳታሚ ከጥልቅ ጥናት ጋር የሚያሳትማቸውን የኢትዮጵያ ጥንታዊ መዛግብት ኅትመቶች ማገለባጥ ይቻል ነበር፡፡

የገረመኝ ገድለ ተክለ ሃይማኖትን ያህል በኢትዮጵያ ታሪክ (History)ና የታሪክ አጻጻፍ(Historiography) ታላቅ ቦታ ያለው፣ በኢትዮጵያ ገድላት ጥናት (Hagiography) ቀዳሚ የሆነና በብዙ አጥኝዎች የተጠና ጉዳይ ያለ ምንም በቂ ማስረጃ አፈርሳለሁ ብሎ መነሣቱ ነው፡፡ ይኼ ደግሞ ከማይወጣበት የክርክር አዘቅት ውስጥ እንዲወድቅ አድርጎታል፡፡

ተስፋዬ ጽሑፉን የጀመረው በስድብ ነው፡፡ ኤርትራዊት እናቱ ‹ይዘምሩት ነበር‹ ብሎ ያቀረበው ጽሑፍ የራሱን ስድብ በእና ያሳበበበት ነው፡፡ የኤርትራን ቤተ ክርስቲያንና ኤርትራውያን ክርስቲያን እናቶችን ከእርሱ በላይ አውቃቸዋለሁ፡፡ ተሰድደው በየሀገሩ ከተበተኑት ጋር አብረን ቋንቋና ድንበር ሳያግደን አገልግለናል፡፡ አሥመራ ከተማ ከሚገኙት ታላላቅ አድባራት አንዱም የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ በምንም መልኩ አንዲት ኤርትራዊት እናት ተስፋዬ በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ላይ የተሳለቀውን ‹መዝሙር› አትዘምርም፤ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ደማቸው የፈሰሰው ሰባት ዓመት ሙሉ ለጸሎት የቆሙበት እግራቸው በጸሎት ብዛት በመቆረጡ እንጂ ሰይጣን ‹ፈንግሏቸው› አለመሆኑን ኤርትራውያን እናቶች በሚገባ ያውቁታል፡፡ የሚገርመው ነገር ተስፋዬ በጆሮ ጠገብ የሆነ ቦታ የሰማውን መዝሙር አጣምሞት እንጂ መዝሙሩ እንዲህ አይደለም፡፡
ተክለ ሃይማኖት የዓለም ብርሃን ናቸው
ይኼው ለዘላለም ያበራል ገድላቸው
ነው የሚለው፡፡

ተስፋዬ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን በተመለከተ አነበብኳቸው የሚለን አምስት መጻሕፍትን ነው፡፡ የአባ ዮሐንስ ከማ፣ የኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ የጽጌ ስጦታው፣ የዳኛቸው ወርቁና የኢረይን ሙራይ፡፡ አባ ዮሐንስ ከማን እንደማያውቃቸው፣ የጻፉትንም ገድል እንዳላነበበ የሚያሳብቅበት ‹ደብተራ› ሲላቸው ነው፡፡ አባ ዮሐንስ ከማ ሰባተኛው የደብረ ሊባኖስ እጨጌ እንጂ ደብተራ አልነበሩም፡፡ በዚያ ዘመን ‹ደብተራ› ማለት የንጉሡን ደብር(ድንኳን) የሚያገለግሉት ካህናት ናቸው፡፡ አባ ዮሐንስ ከማ በዐፄ ይስሐቅ(1407-1423)ዘመንና በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ(1437-1461)የመጀመሪያዎቹ ዓመታት የነበሩ ደብረ ሊባኖስን እንደገና ያሳነጹ ገድለ ተክለ ሃይማኖትንም ያስጻፉ አባት ናቸው፡፡ ተስፋዬ አባ ዮሐንስ ከማ ከ200 ዓመታት ቆይታ በኋላ ስለ ጻፉ ተሳስተዋል ይላል፡፡ ባታውቀው ነው እንጂ ሙሴ ኦሪትን የጻፈው ዓለም ከተፈጠረ ከሺዎች ዓመታት በኋላ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን ገድሎች ዘግይተው የሚጻፉት የአንድን ቅዱስ ቅድስና ለመመስከር ካረፈ ቢያንስ ግማሽ ምእተ ዓመት ስለሚያስፈልገው ነው፡፡ በመቃብሩ ላይ የሚሠሩት ተአምራት፣ በአማላጅነቱ የሚሠራቸው ተአምራትና ሌሎችም መታየት አለባቸው፡፡

ተስፋዬ አላዋቂነቱን እንደ ዕውቀት ስለወሰደው እንጂ የአቡነ ዮሐንስ ከማ ገድል የመጀመሪያው የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገድል አይደለም፡፡ በነገራችን ላይ ስለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አራት ቀደምት ሰዎች ጽፈዋል፡፡ 1)በስንክሳር ተጽፎ የሚገኘው(በተለይም በፓሪሱ ስንክሳር) አጭር የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ታሪክ፣ 2) የትግራይ ተወላጅ በሆነው በተክለ ጽዮን የተጻፈው የዋልድባው ገድለ ተክለ ሃይማኖት [አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት (በቆብ) የልጅ ልጅ ናቸው፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አቡነ መድኃኒነ እግዚእን ሲያመነኩሱ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ደግሞ ሰባቱ ከዋክብት የተባሉትንና በጣና ዙሪያ የሰበኩትን (አቡነ ዮሐንስ ዘቁየጻ፣ አቡነ ሳሙኤል ዘጣሬጣ፣ አቡነ ያሳይ ዘማንዳባ፣ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ አቡነ ዮሐንስ ዘጉራንቋ፣ አቡነ ታዴዎስ ዘባልተዋርና አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ዘጉጉቤን) ሲያመነኩሱ ነው ምንኩስናን ተቀብለው ለተልዕኮ የተሰማሩት፡፡ ለዚህም ነው የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን ገድል ዋልድባዎች የጻፉት፡፡] 3)ያልታወቀ ጸሐፊ አጭሩንና የሐይቅ እስጢፋኖስ ቅጅ የሚባለውን ጽፏል፡፡ ይኼኛው ገድል ቀዳሚ ሳይሆን አይቀርም፤ አንደኛ የተጻፈው ከሌሎች ቅዱሳን ገድሎች ጋር እስትግቡእ ሆኖ በስንክሳር መልክ ነው፡፡ ሁለተኛ የተጠቀማቸው አማርኛዎች በአሁኑ ጊዜ ጥቅም ላይ የሌሉ ዓይነት ናቸው፣ 4)አቡነ ዮሐንስ ከማ የጻፈው የደብረ ሊባኖስ ቅጅ ናቸው፡፡ ይህ የአቡነ ዮሐንስ ከማ ገድል ምናልባት ከ1418-19 ዓም ባለው ጊዜ ውስጥ በዐፄ ይስሐቅ ዘመን የተጻፈ መሆኑ ይገመታል(Encyclopedia Aethiopica, Vol. IV, P. 832)በግብጽ ቤተ ክርስቲያን የሚገኘው ዐረብኛው ገድል በዐፄ ገላውዴዎስ ዘመን(1533-1551) የተጻፈ ይመስላል(Encyclopedia Aethiopica,Vol.IV, P.832)፡፡ ያልተመዘገቡ አያሌ ገድላት በየገዳማቱ መኖራቸው እንደተጠበቀ ሆኖ 22 የብራና ገድሎች በአውሮፓ፣ 20 በኢትዮጵያ የማኑስክሪፕት ቤተ መጻፍት (EMML)፣ 3 በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት፣ 5 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናት ተቋም የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገድሎች ይገኛሉ፡፡ በአንድ ቅዱስ ላይ የተለያዩ ቅጅዎች መገኘታቸው መረጃዎችን ያሰፋቸዋል እንጂ ጉዳት የለውም፡፡ ስለ አንድ ክርስቶስ አራት ዓይነት ወንጌሎች መጻፋቸውን ማስታወስ ይበቃል፡፡

አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በብዙ ሥራዎቻቸው የተከበሩና የተመሰገኑ ሊቅ ናቸው፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን በተመለከተ ላነሡት ሃሳብ ግን ያቀረቡት ማስረጃ የላቸውም፡፡ ከኢትዮጵያ ገድሎች ሁሉ የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን ገድል ያህል የሚታወቅና የተጠና የለም፡፡ ከሌሎች ጋር እየተነጻጸረም ሆነ በራሱ(Textual analysis) ገድለ ተክለ ሃይማኖት በአውሮፓውያንም ሆነ በኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ተጠንቷል፡፡ እስካሁን ግን አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌም ሆኑ ሌሎች የሚሉት ‹ሌላ ገድል› አልተገኘም፡፡ አለቃምያነበቡት ከሆነ ያነበቡትን፣ ያገኙት ከሆነም ያገኙበትን አልነገሩንም፡፡ ምንጭ የላቸውምና ለታሪክ ክርክር ሊጠቀሱ አይችሉም፡፡

ጽጌ ስጦታውም ቢሆን ምናቡንና አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌን ጠቀሰ እንጂ አለ የሚለውን ‹የዚያኛውን ተክለ ሃይማኖት› ገድል ሊያመጣልን አልቻለም፡፡ ዳኛቸው ወርቁ የጻፈው ልቦለድ እንጂ ታሪካዊ ዋጋ ያለው ነገር ስላልሆነ ለክርክር የሚቀርብ አይደለም፡፡ ይባስ ብሎ ተስፋዬ ኢለይን ሙራይ ለልጆች ብላ የጻፈችውን ተረት ጠቅሶልናል፡፡ ይህ ነገር የቦሩ ሜዳን ክርክር ነው ያስታወሰኝ፡፡ በቦሩ ሜዳ ክርክር ‹ለኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ልደት አለው› የሚሉና ‹ሦስት ልደት አለው› የሚሉ ሊቃውንት ተከራክረው ነበር፡፡ በዚህ ክርክር የሁለት ልደትን ወክለው ከተከራከሩት መካከል የነበሩት መልከአ ብርሃን ወልደ ዮሐንስ ‹ነአምን ክልኤተ ልደታተ› የሚል ንባብ ከሊቃውንት መጽሐፍ ጠቅሰው ተከራከሩ፡፡ ዐፄ ዮሐንስም የሦስት ልደቶችን ተከራካሪ አለቃ ሥነ ጊዮርጊስን ‹በል አንተም እንደ እርሱ ከሊቃውንት መጽሐፍ ሦስት ልደት የሚል ንባብ አምጣ› አሉት በዚህ ጊዜ አለቃ ሥነ ጊዮርጊስ ‹በደብረ ብርሃን ተአምረ ማርያም ይገኛል› አሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ንጉሡ ‹ከምታስተምረው ከአራቱ ጉባኤ አጣህና ነው ከተአምረ ማርያም ትጠቅሳለህ›› ቢሏቸው ‹ ከጉባኤው መጽሐፍስ የለም›› አሉ ይባላል፡፡

የተስፋዬ አጠቃቀስ ከዚህም የወረደ ነው፡፡ አለቃ ሥነ ጊዮርጊስ የተወቀሱት ለእምነት ክርክር የማይጠቀስ የተአምር መጽሐፍ በመጥቀሳቸው ነው፡፡ ተስፋዬም ከዚያ ወርዶ ወርዶ ለታሪክ ክርክር የማይጠቀስ የተረትና የልቦለድ መጽሐፍ ሲጠቅስ ይገኛል፡፡ ተስፋዬ ወግዳ የተሸሸገ ለሕዝብ የማይቀርብ ገድለ ተክለ ሃይማኖት አለ ይላል፡፡ በሀገራችን ጠንቋይ እንዳይጋለጥ ሲፈልግ የሌለ ነገር ያዝዛል ይባላል፡፡ ተስፋዬም ወግዳ የተደበቀ ገድል አለ አለ፡፡ ወግዳ በሰሜን ሸዋ በደብረ ብርሃን ዙሪያ ወረዳ ሥር የሚገኝ ቦታ ነው፡፡ የኢትዮጵያ የብራና መጻሕፍት በ1964 ዓም ማይክሮ ፊልም መነሣት ሲጀምሩ ከሰሜን ሸዋ ነበር የተጀመረው፡፡ እነ ሥርግው ሐብለ ሥላሴ(አጥንታቸውን ያለምልመው እንጂ) እያንዳንዷን ወረዳ ለቅመው አንሥተውታል፡፡ እንኳን በገዳማት አድባራት የሚገኙት በግለሰቦች እጅ የሚገኙትም አልቀሯቸውም፡፡ እንኳን የቤተ ክርስቲያኒቱ መጽሐፍ የሕንድ፣ የግሪክ መጻሕፍት አልቀራቸውም፤ እንኳን ገድልና ተአምር የቤተ ክርስቲያንን እምነት የሚቃረኑ መጻሕፍት በክብር ተጠብቀው ነው የተገኙት፡፡ ተስፋዬ ወግዳ የማይደረስበት መስሎት መደበቂያ ዋሻ አለ ይላል፡፡ ወግዳኮ ከአዲስ አበባ የ120 ኪሎ ሜትር ጉዳይ ነው፡፡

በማይክሮ ፊልም ቀረጻው ወቅት በሥራ ላይ የተሠማሩት የሀገሬው ተወላጆች ነበሩና ያስቸገራቸው ነገር አልነበረም፡፡ በዚህ ጉዞ ውስጥ ይህ ‹የወግዳ ገድል› ይገኝ ነበር፡፡ ግን የለምና አልተገኘም፡፡ ይህ ዓይነት ፕሮፓጋንዳ ዛሬ አልተጀመረም፡፡ በትግራይ፣ በወሎ፣ በጎጃም በተክለ ሃይማኖት ስም ስለሚጠሩ ሌሎች ቅዱሳን የተጻፉ ገድሎች አሉ እየተባለ እንዲሁ በአፍ ታሪክ ይነገራል፡፡ እስካሁን ግን ማስረጃ አምጥቶ ያረጋገጠ አልተገኘም፡፡ የትግራይ ገዳማት የብራና መጻሕፍት በቅርቡ ዲጂታላይዝ ተደርገዋል፡፡ ግን የተባለው አልተገኘም፡፡

በመካከለኛው ዘመን ሌላው ቀርቶ ከማዕከላዊው መንግሥት ተጋጭተው ርቀው በነበሩት የደቂቀ እስጢፋኖሳውያን ገዳም በጉንዳ ጉንዲ እንኳን የደብረ ሊባኖሱን ገድል የመሰለ ቅጅ ነው የተገኘው፡፡ ማንኛውም ክርክር ሲቀርብ ለክርክሩ ብቁ የሆነ ማስረጃ መቅረብ አለበት፡፡ ልቦለዱንም፣ ቀልዱንም ለታሪክ ማስረጃ መጥቀስ ቧልት እንጂ ቁም ነገር አይሆንም፡፡

ተስፋዬ ስለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የሚባለውን የታወቀ ታሪክ (official history)ለመቀበል አልፈለገም፡፡ ያ በራሱ ችግር አይደለም፡፡ አዲስ ማስረጃ አምጥቶ ወይም ነባሩን ማስረጃ በክርክር አፍርሶ ያላየነውን ካሳየን እናመሰግነው ነበር፡፡ እርሱ ግን ወይ የታወቀውን አልተቀበለ፣ አለያም አዲስ ማስረጃ አላመጣ፣ ከሁለት የወጣ ጎመን ሆነብን፡፡

ሮማውያን የሕግ ሊቃውንት Argumentum ad Contrario የሚል መርሕ ነበራቸው፡፡ ‹አንድን ነገር የታመነውንና የታወቀውን ትተህ በተቃራኒው ያለውን አረጋግጥ› ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን በተመለከተ የሚባለውንና የሚታመነውን ተወውና ተቃራኒውን በማስረጃ፣ በተጠየቅና በትንታኔ አረጋግጥ ማለት ነው፡፡ ተስፋዬ ይህንን ለማረጋገጥ ዐቅም አላገኘም፡፡ እንዲሁ ቧልቱን ብቻ ነገረን፡፡

ተስፋዬ የታሪክ ስሕተቱን የሚጀምረው በሰባተኛው መክዘ ዐፄ ዳዊት የሚባሉ ንጉሥ ኢትዮጵያ ውስጥ ነበሩ ሲለን ነው፡፡ ተስፋዬ በቀላሉ የሚገኘውን የሬኔ ባሴን ታሪከ ነገሥት፣ የሥርግው ሐብለ ሥላሴን የነገሥታት ዝርዝር፣ የተክለ ጻድቅ መኩሪያን መጻሕፍት አለያም የብላቴን ጌታ ኅሩይን ‹ዋዜማ›፣ የጌታቸው ኃይሌን ባሕረ ሐሳብ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ1975 አሳትሞት የነበረውን The Dictionary of Ethiopian Biography, ብታይኮ እንዲህ ካለ ስሕተት ውስጥ አትወድቅም ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ዳዊት በሚል ንጉሥ መጀመሪያ የነገሠው ዐፄ ዳዊት አንደኛ ከ1374-1406 ዓም ነው፡፡ ከየት አምጥተህ ነው በሰባተኛው መክዘ ያደረግከው፡፡

እጂግ የሚገርመው ነገር የሀገራችን ሊቃውንት ‹ጨዋ ደፋር ነው› እንደሚሉት ተስፋዬም ያለ ምን ጥናት፣ ያለ ምንም ማስረጃ እርሱ ራሱም እንደሚለን ‹ኢትዮጵያ ሳለ የሰማቸውን አፈ ታሪኮች ሰብስቦ›(እኔ ግን አይመስለኝም፣ አሜሪካ ሆኖ ፈጥሮ እንጂ) በድፍረት ‹ሦስት ተክለ ሃይማኖቶች አሉ ይላል፡፡ ቢያንስ ለዕውቀት ክብር ሰጥቶ ‹ያሉ ይመስለኛል› ቢል እንኳን ምን አለበት፡፡ ለካስ እስከዛሬም በሌሎች መጻሕፍቱ ሲነግረን የነበሩት ‹የመንግሥት ምሥጢሮች› እንዲህ የተሰበሰቡ አፈ ታሪኮች ነበሩ ማለት ነው?

ለመሆኑ ተስፋዬ እናዳለው ሦስት ተክለ ሃይማኖቶች አሉን? ሦስቱስ በገድለ ተክለ ሃይማኖት ተቀላቅለዋልን? ሳምንት እንመለሳለን፡፡
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ ላይ የወጣ ነው


ኦ ክቡር ኣቦና ኣቡነ ኣንጦንዮስ ጸሎትኩምን ኣማላድነትኩምን ኣይፈለዬና!

ኦ ክቡር ኣቦና ኣቡነ ተክለ ሃይማኖት ጸሎትኩምን ኣማላድነትኩምን ኣይፈለዬና!
Last edited by Meleket on 04 Jan 2025, 04:41, edited 1 time in total.

Axumezana
Senior Member
Posts: 18452
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: አቡነ ተክለሃይማኖት፡ ተስፋዬ ገብረአብ፡ ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን፡ ዓወል ስዒድን፡ . . . . እንኪምርመሩ

Post by Axumezana » 04 Jan 2025, 04:29

ደብተራ መለከት የደብረሊባኖሱ ተክላሃይማኖት ዞንዳቸውንና ገድላቸውን ተነቅሎ እስከ ወድያኛው ተሸኝተዋል። የሌሎችን ታሪክ ብታስታውቀን መልካም ነው።

Meleket
Member
Posts: 4796
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: አቡነ ተክለሃይማኖት፡ ተስፋዬ ገብረአብ፡ ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን፡ ዓወል ስዒድን፡ . . . . እንኪምርመሩ

Post by Meleket » 04 Jan 2025, 05:18

ነዚ ብርቂ ምርምራዊ ጽሑፍ ደኣ እንታይ ሰሙን ክንጽበዬሉ፡ ሕጂ ክንህበኩም እምበር፡ መታን ምስቲ ክቡር በዓል ልደተ ክርስቶስ አሰኒኩም ከተስተማቕርዎ።
የሌለውን ፍለጋ - ክፍል ሁለት

ባለፈው ሳምንት ተስፋዬ ገብረ አብ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን በተመለከተ ያነሣቸውን ነጥቦች ማየት ጀምረን ‹የሦስቱን ተክለ ሃይማኖቶች› ጉዳይ ለዛሬ አቆይተነው ነበር፡፡ እንቀጥል፡፡

1) የሰባተኛው መክዘ ተክለ ሃይማኖት
ተስፋዬ የጠቀሳቸው የሰባተኛው መክዘ ተክለ ሃይማኖት የሉም፡፡ እስካሁንም እንደርሱ ፈጠራቸውን የሚናገሩ እንጂ ማስረጃ ያመጡ አልተገኙም፡፡ ይህንን ነገር መጀመሪያ ያነሣው የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ገድለ ተክለ ሃይማኖትም ስለ ጽላልሽ (ኢቲሳ) ተክለ ሃይማኖት እንጂ ስለ ሰባተኛው መክዘ ሌላ ተክለ ሃይማኖት አይናገርም፡፡ ገድለ ተክለ ሃይማኖትን በተመለከተ ልዩ ልዩ ቅጅዎች ቢገኙም ሁሉም ግን በተወለዱበት ቦታ፣ በተወለዱበት ዘመን፣ በወላጆቻቸው ስም፣ በሠሯቸው ሥራዎችና በገዳማቸው ላይ የሚተርኩት ታሪክ ተመሳሳይ ነው(Encyclopedia Aethiopica, Vol., IV,.P.833)በአንድ ወቅት ታላቁን የታሪክና የኢትዮጵያ ጥንታውያን መዛግብት ሊቅ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌን ስለዚህ ጉዳይ ስጠይቃቸው ‹አለኝ ያለ ማስረጃውን ያምጣ፣ የለም የምንለው ፈልገን ልናመጣ አንገደድም›› እንዳሉት አለን የሚሉት እስኪያመጡ ድረስ የምናውቀውን ይዘን እንቀጥላለን፡፡

2) መራ ተክለ ሃይማኖት የሚባል ንጉሥ ነበረ፡፡ እንደ ደብረ ሊባኖስ ዘሺምዛና(ኤርትራ) እና ደብረ ሐይቅ መዛግብት ከሆነ መራ ተክለ ሃይማኖት የዛግዌ ሥርወ መንግሥት መሥራች ንጉሥ እንጂ ‹ቄስ› አልነበረም፡፡ የዛግዌን ዘመን በተመለከተ የተጻፉ የዛግዌ ቅዱሳን ገድሎች(ፔሩሾ የጻፈውን የገድለ ላሊበላ መቅድም መመልከት) ይህንን አይነግሩንም፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን የዛግዌን ታሪክ ያጠኑት ሊቃውንት(ለምሳሌ E. A. Wallis Budge, A History of Ethiopia, London, 1928; Sergew Hable Sellassie, Ancient and Medieval Ethiopian History) መራ ተክለ ሃይማኖት ቄስ ነበረ አይሉንም፡፡ የላስታ ትውፊትም ይህን አይናገርም፡፡ በላስታ አድባራትና ገዳማት የሚሳሉት ቅዱሳን አራቱ ነገሥታት ናቸው (ቅዱስ ላሊበላ፣ ቅዱስ ሐርቤ(ገብረ ማርያም)፣ ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስና ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ)፡፡ ከእነዚህም ክህነትና ንግሥናን እንደያዘ የሚነገረው ይምርሐነ ክርስቶስ ነው፡፡

ተስፋዬ እንዲሆን የሚፈልገውን ብቻ ነው የነገረን፡፡

ስለዚህም በገድለ ተክለ ሃይማኖት የሦስት ሰዎች ገድል ተቀላቅሏል የሚለን ማስረጃ አልባ ሕልም ነው፡፡

ስለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የተጻፈው በገድላቸው ብቻ አይደለም፡፡ በብዙ ጥንታውያን መዛግብትም ጭምር እንጂ፡፡ በገድለ አቡነ ኢየሱስ ሞአ(ወሎ)፣ በገድለ አቡነ ፊልጶስ፣ በገድለ አቡነ አኖሬዎስ(ባሌ)፣ በገድለ አቡነ እንድርያስ(ደቡብ ጎንደር) በገድለ አቡነ ፊልጶስ ዘደብረ ቢዘን (ኤርትራ፣ እንዲያውም በ ደብረ ቢዘኑ(ኤርትራ) ገድለ አቡነ ፊልጶስ ወአቡነ ዮሐንስ ላይ ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት አልፎ የእርሳቸውን ደቀ መዛሙርት ዝርዝር በሚገባ ይነግረናል፡፡ C. Conti Rossini, Gadla Filipos e il Gadla Yohannes,1901, P.156)፣ በገድለ አቡነ ዜና ማርቆስ(ሰሜን ሸዋ)፣ በገድለ አቡነ ቀውስጦስ፣ በገድለ አቡነ ዕንባቆም(ወለጋና ምዕራብ ሸዋ)፣ በገድለ አቡነ ተክለ ሐዋርያት(ምዕራብ ሸዋ)፣ በገድለ አቡነ ተክለ አልፋ(ምሥራቅ ጎጃም)፣ በገድለ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ(ትግራይ)፣ በገድለ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ(ኤርትራ)፣ በገድለ አቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ(ምዕራብ ሐረርጌ)፣ ተጽፎ ይገኛል፡፡

እነዚህ በተለያዩ ዘመናት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተጻፉ ገድሎች በደብረ ሊባኖስ በ12ኛው መክዘ መጨረሻና በ13ኛው መክዘ መጀመሪያ ላይ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የሚባሉ አባት ተነሥተው እንደነበረ ታሪካቸውን በአጭርም ሆነ በስፋት ይነግሩናል፡፡ ከኢትዮጵያውያንም ውጭ በ16ና17ኛው መክዘ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩት እነ ኢማኑኤል አልሜዳና ፓድሮ ፓኤዝ ወደ ኢትዮጵያ በመጡ ጊዜ ያገኙትን ነገር መነሻ ስለ ደብረ አስቦው አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጽፈዋል፡፡ ሌላ ተክለ ሃይማኖት ስለመኖሩ ግን ያነሡት ነገር የለም፡፡

በርግጥ አልሜዳ ተክለ ሃይማኖትን በሰባተኛው ወይም በስምንተኛው መክዘ የተነሡ ናቸው ብሎ ገምቷል፡፡ ወደዚህ ግምት የወሰደው የኢትዮጵያውያንን ገድላት አጻጻፍ ባለማወቁ ነበር፡፡ ኮንቲ ሮሲኒ ‹‹ወደ ኢትዮጵያ ታሪክ ጥናት ይበልጥ ራሴን ባስገባሁ ቁጥር ሀገራዊውን ትውፊት ማወቅ እንዳለብኝ ይበልጥ እየተረዳሁ መጥቻለሁ፡፡ ይህንን ሀገራዊ ትውፊት፣ ከሕዝቦችን ንቅናቄ ታሪክና ከተከታታይ መሪዎቹ ታሪክ ጋር(ምንም እንኳን አንዳንዴ አፈ ታሪክም ቢሆን) እያወቅን በመጣን ቁጥር ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ ርግጠኛ የሆነ ግንዛቤ ይኖረናል›› እንዳለው(C. Conti Rossini, "Note di agiografia etiopica (Abiya- Egzi, Arkaledes e Gabra Iyesus)," Rassegna di studi orientali, 17(1938), 409-10. )የኢትዮጵያን ባህል ና ትውፊት ካላወቁ የሚፈጠረውን ስሕተት ነው አልሜዳ የፈጠረው፡፡ ለምሳሌ አልሜዳ እንደ አንድ ማሳያ ያነሣው ‹በገድለ ተክለ ሃይማኖት ውስጥ ስለ ሙስሊሞች አልተገለጠም› የሚል ነው፡፡

የመካከለኛው ዘመን የኢትዮጵያ ገድሎች ግን ከክርስትና ውጭ ያሉትን ሕዝቦች ‹ተንባላት› እያሉ ነው የሚጠሯቸው፡፡ ሙስሊም ወይም እስላም የሚለውን ስም በሚገባ የምናገኘው የክርስቲያን ሙስሊም ግንኙነት እየሻከረ በመጣባቸው የመካከለኛው ዘመን የመጨረሻዎቹ ዓመታትና ከግራኝ አሕመድ ጦርነት በኋላ ነው፡፡ በገድለ አኖሬዎስ፣ በገድለ አቡነ አሮን፣ በገድለ አቡነ በጸሎተ ሚካኤልና በገድለ አቡነ ፊልጶስም በተመሳሳይ ሁኔታ ነው የሚገኘው፡፡

አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ከፖለቲካ ጋር የማያያዝ ነገር በተስፋዬ አልተጀመረም፡፡ ሌሎች አካላትም ሲያራምዱት የኖሩና የሚራምዱትም ነገር ነው፡፡ በዚህ ረገድ ያልተጠኑ ሦስት ነገሮች አሉ፡፡ አንደኛው የሰሎሞናዊ መንግሥት ምለሳ (Restoration) የሚባለው ነገር፡፡ ሁለተኛው በዚህ ምለሳ ላይ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ነበራቸው የሚባለው ሚና እና የታሪኩ ምጮች ናቸው፡፡

እንደ እውነቱ ከሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ በአኩስም ዘመን የነበሩ ነገሥታት ራሳቸውን ሰሎሞናውያን ብለው የጠሩበት መረጃ የለንም፡፡ ለኢትዮጵያ ነገሥታት ግን ራሳቸውን ከኢየሩሳሌምና ከቅድስት ሀገር ጋር ማያያዝ የተለመደ ነው፡፡ በዚህ ረገድም የዛግዌ ነገሥታት ሰሎሞናውያን የማይሆኑበት ምክንያትም የለም፡፡ እንዲያውም ለሰሎሞናዊነቱ ከኋለኞቹ ነገሥታት ይልቅ የዛግዌ ነገሥታት ይቀርባሉ፡፡በውቅር ቤተ ክርስቲያኖቻቸውም ሆነ በማኅተሞቻቸው ላይ የዳዊትን ኮከብ በብዛት እናየዋለን፡፡ ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድም የዛግዌ ነገሥታት ይበልጣሉ፡፡ ቅዱስ ላሊበላም የሮሐን አብያተ ክርስቲያናት ሲያንጽ ኢየሩሳሌምን እያስታወሰ ነው፡፡ በኋላ ዘመን ‹ሰሎሞናውያን› ከተባት የይኩኖ አምላክ ዘሮች ነገሥታት ወገን እንድም ንጉሥ ኢየሩሳሌም ሄደ ተብሎ አልተጻፈለትም፣ አልተነገረለትምም፡፡ የዛግዌ ነገሥታትን ግን ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ የሚተካከላቸው የለም፡፡

የአኩስምን ነገሥታት (በተለይ ዐፄ ካሌብና ዐፄ ገብረ መስቀል በወሎ አካባቢ አያሌ አብያተ ክርስቲያናትን ተክለዋል፡፡ የዛግዌ ነገሥታትም (በደብረ ሊባኖስ ዘሺምዛና ወንጌል እንደ ተገለጠው) ለኤርትራና ትግራይ ገዳማት ርስት ሰጥተዋል፡፡ የሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት መላሽ የሚባለው ይኩኖ አምላክም ቢሆን በእናቱ የቡግና ተወላጅ ነው፡፡ ውትድርና ተቀጥሮ የኖረውም ቡግና ነው፡፡ የተማረውም ወሎ ሐይቅ እስጢፋኖስ ነው፡፡ አቡነ ኢየሱስ ሞአ ትውልዳቸው ቡግና ስለሆነ ነው ይኩኖ አምላክ ወደ ሐይቅ ለትምህርት የሄደው፡፡ እርሱ ሲነግሥም መጀመሪያ ያሳነጸው የወሎዋን ገነተ ማርያምን ነው፡፡ አጽሙም የሚገኘው በወሎዋ አትሮንሰ ማርያም ነው፡፡ ይኩኖ አምላክ በሸዋ ውስጥ ስሙ እንጂ ቅርሱ ያለ አይመስልም፡፡

ይኩኖ አምላክ ወደ ሸዋ የወረደው እርሱ ሸዬ ስለሆነ አይመስልም፡፡ የዛግዌ ነገሥታት የበረታ ኃይል ከሚገኝበት ከወሎ አካባቢ ለመሸሽና የደቡቡን ኃይል ለማሰባሰብ እንጂ፡፡ ኮንቲ ሮሲኒ ከኤርትራ አግኝቶ ባሳተመው እንድ ጥንታዊ የብራና ጽሑፍ ላይ ‹‹(የይኩኖ አምላክ ሠራዊት) ሰባቱ ጉደም ናቸው፡፡ እነርሱም ወግዳ - መለዛይ፣ ዲንቢ - ዳባራይ፣ ሙገር - እንደ ዛቢ፣ ወጅ - እነጋሪ፣ ወረብ - እነካፌ፣ ጽላላሽ እነ ጋፌ እና ሙዋይ - አውዣዣይ ናቸው፡፡ የእነርሱም አለቃ መለዛይ ከንጉሡ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፤ ተዋግቶም ጠላቶቹን ድል ነሣ›› ይላል (Taddesse Tamrat, Ethnic Interaction and Integration In Ethiopian History: The case of The Gafat, JES, Vol. XXI,1988, P. 125)

ይኩኖ አምላክ የዛግዌ ነገሥታትን ሊያሸንፍ የቻለው በዚያ ዘመን በጥበበ ዕድ አንድነት በፈጠሩት(ሰባት ጉዳም) ጋፋቶች ርዳታ ነው፡፡ ምንጊዜም የመሣሪያ ኃይል ያለው ያሸንፋልና፡፡ ይኩኖ አምላክ ወደ ሸዋ ባደረገው መስፋፋት ወደ ክርስትና ተመልሶ ከደጋው ሸዋ ክፍል ጋር የነበረውን ጠላትነት ያጠፋውን የዳሞትን መንግሥት ኢኮኖሚያዊ ዐቅም ተጠቅሞበታል፡፡ ልክ በኋላ ዘመን ዐፄ ምኒሊክ የደቡቡን ኃይልና ዐቅም በመጠቀም ገንነው እንደወጡት ማለት ነው፡፡ ይኩኖ አምላክ ወደ ሸዋ በመምጣት ኃይሉን በማደራጀቱ ሸዬ ሆኖ ቀረ፡፡

ልክ በኋላ የሸዋ ነገሥታት ወደ ጎንደር ሄደው ጎንደሬ ሆነው እንደቀሩት ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ‹ሰሎሞናዊ› የሚባል የተለየ መንግሥት አልነበረንም፡፡ ነገሥታቶቻችን ሁሉ ራሳቸውን ከኢየሩሳሌም ጋር ያያይዙ ነበር፡፡ ዐፄ ካሌብም ከናግራን ዘመቻ መልስ ዘውዳቸውን ኢየሩሳሌም ነው የላኩት፡፡ የዐፄ ገብረ መስቀል ልጅ ሙሴም መጀመሪያ ወደ ኢየሩሳሌም፣ በኋላም ወደ ሶርያ በመጓዝ በዚያ ገመንነው ገዳም መሥርተዋል፡፡ ገዳማቸውም ‹ሙሴ አል ሐበሽ ገዳም› ይባላል፡፡


የዛግዌ ነገሥታትም ሰሎሞናውያን የማይሆኑበት ምክንያት የላቸውም፡፡ በገድሎቻቸው ላይ ኢየሩሳሌምን አብዝተው የሚያነሡ፣ ማኅተሞቻቸው ሁሉ የዳዊት ኮከብ የሆኑ፣ በውቅር ቤተ ክርስቲያኖቻቸው የዳዊትን ኮከብ የቀረጹ የዛግዌ ነገሥታት እንዴት ሰሎሞናውያን አይሆኑም፡፡ በመሆኑም የጠፋና የተመለሰ የሰሎሞን መንግሥት አለ ብሎ ለመናገር ያስቸግራል፡፡ ሥርወ መንግሥታቱንም ‹የአኩስም፣ የላስታ፣ የሸዋ፣ የጎንደርና የሸዋ 2ኛ› ብሎ መክፈሉ የተሻለ ነው፡፡

ሲባል እንደኖረው አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሲሦ መንግሥት ቢቀበሉ ኖሮ በገድለ አቡነ አኖሬዎስና በገድለ አቡነ ፊልጶስ ላይ እንደምናነበው እነዚህ ሁለት ቅዱሳን ወደ ደብረ አስቦ(የአሁኑ ደብረ ሊባኖስ) ሲመጡ ግንባር በምታክል መሬት ላይ አተር ዘርተው ሲሰበስቡ ባላገኟቸው ነበር፡፡ ደብረ ሊባኖስ ይበልጥ እየታወቀና በማዕከላዊ መንግሥት ቦታ እያገኘ የሄደው ከዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን በኋላ ነው(ምናልባት ኤርትራ ይገኝ ከነበረው ከደብረ ሊባኖስ ዘሺምዛና ጋር ያለው ግንኙነት እየተዳከመ ሲመጣ)፡፡ ደብረ ሊባኖስ የሚለውን ስም ያገኘውም ያኔ ነው፡፡(Les chroniques de Zara Ya’eqob.,P. 91) አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከነገሥታቱ ጋር የተለየ ቀረቤታ ቢኖራቸው ኖሮ በዓለ ዕረፍታቸው ነገሥታቱና መኳንንቱ በተገኙ ነበር፡፡ ነገሥታቱ በደብረ ሊባኖስ መገኘት የጀመሩት አቡነ ተክለ ሃይማኖት ካረፉ ከ100 ዓመታት ቆይተው ከዐፄ ይስሐቅ ዘመን (1406-1421 ዓም) በኋላ ነው፡፡ እንዲያውም የደብረ ሊባኖስ አባቶች በነበራቸው ጽኑዕ አቋም የተነሣ ከነገሥታቱ ጋር ባለ መስማማት ነው የሚታወቁት፡፡ 3ኛውን እጨጌ አቡነ ፊልጶስን፣ አሥራ አንዱን ንቡራነ ዕድና እጨጌ እንድርያስን ማስታወሱ ይበቃል፡፡

ከላስታ ወደ ሸዋ የመንግሥት ዝውውር ሲደረግ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሐይቅ እስጢፋኖስ በትምህርት ላይ ነበሩ(የሚጣቅ ዐማኑኤሉ ገድለ ተክለ ሃይማትና ገድለ ኢየሱስ ሞአ በዝርዝር እንደሚተርከው)፡፡ በዚህ የሥልጣን ዝውውር ላይ ይበልጥ ተሳታፊ የነበሩት አቡነ ኢየሱስ ሞአ ዘሐይቅ ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ሐይቅ የዐቃቤ ሰዓትነት ሥልጣን ነበረው፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሲሦ መንግሥት አግኝተዋል የሚለው ትረካ መንግሥት ወደ ጎንደር ከተቀየረ በኋላ(17ኛው መክዘ) በተጻፈው በብዕለ ነገሥት ላይ የተገለጠ ነው፡፡ ብዕለ ነገሥት የነገሥታትን ሀብት ለማሳየት የተጻፈ ነው፡፡ በዚህ መጽሐፍ ነው ከይኩኖ አምላክ ጋር ቃል ኪዳን ገብተዋል ተብሎ የተጻፈው፡፡

የዚህ ምክንያቱ ደግሞ ግልጽ ነው፡፡ መንግሥት ወደ ጎንደር ሲዞር ደብረ ሊባኖስ ከማዕከላዊው መንግሥት ራቀ፡፡ በአካባቢውም ክርስቲያን ባልሆኑ ሕዝቦች ተከበበ፡፡ የጎንደር ነገሥታት ገዳሙን እንዳይረሱትም በብዕለ ነገሥት የአባታቸውን ይኩኖ አምላክን ቃል ኪዳን እንዲያስታውሱ የሚያደርግ ነገር ተጻፈ፡እናም ተስፋዬም ሆነ ሌሎች እንደሚሉት አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከቅድስና ሥራ በቀር የገቡበት ፖለቲካ የለም፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን ፈጽመው ወደ ደብረ አስቦ ሲገቡ ይኩኖ አምላክ በመንበሩ ላይ ነበር፡፡ ነገር ግን የጠበቃቸው ዘንዶ ይመለክበት የነበረ ዋሻ እንጂ ከሲሦ መንግሥት የተገኘ ግብር አልነበረም፡፡ ያንን ዋሻም ያገኙት ከጣዖት አምላኪዎች አስለቅቀው ነው፡፡

28 ዓመት በደብረ አስቦ ሲቀመጡም የጎበኛቸው ንጉሥ አልነበረም፡፡ ደቀ መዝሙሮቻቸውም ከዝንጀሮ ጋር እየተሻሙ እህል ዘርተው ከማብቀል ውጭ የተለየ ርስት አልነበራቸውም፡፡ ደብረ ሊባኖስ ሲተከልም የአካባቢውን ሕዝቦች በማሳመን እንጂ በነገሥታቱ ድጋፍ አልነበረውም፡፡ ከይኩኖ አምላክ በኋላ የመጣው ያግብዐ ጽዮንና አምስቱ የያግብዐ ጽን ልጆች ለአቡነ ተክለ ሃይማትም ሆነ ለደብረ አስቦ ያደረጉት ነገር አልነበረም፡፡ ዐፄ ዐምደ ጽዮንና ዐፄ ሰይፈ አርእድም ከደብረ ሊባኖስ እጨጌዎች ጋር በሰላም አልኖሩም፡፡

አቡነ ፊልጶስ ወደ ደብረ ሊባኖስ ሲመጣ የአካባቢው ሰዎች ‹የገዳሙ መነኮሳት ሰው ይበላሉ›› ብለው ነው የነገሩት፡፡ ይህም ደብረ አስቦ በዚያ ዘመን የመነኮሳት ማኅደር እንጂ እንኳን ነገሥታቱ የአካባቢው ሰዎችም በቅጡ እንዳልቀረቡት ያሳየናል፡፡ የደብረ ሊባኖስ የመጀመሪያዎቹ አባቶችም በራሳቸው ጥረት በደብረ አስቦ ዋሻ ውስጥ ገዳም የተከሉ እንጂ በነገሥታቱ ድጋፍ ሲሦ መሬት የያዙ እንዳልነበሩ ያሳየናል፡፡

ከዐሥረኛው መክዘ ጀምሮ በነበረው የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት በሰሜኑና በደቡቡ የሀገራችን ክፍል ምክንያት የነበረው ግንኙነት ተቋርጦ ነበር፡፡ ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት እንደሚገልጡትም የሰዎች ፍልሰት ከሰሜኑ የሀራችን ክፍል አሁን ሸዋ ወደሚባለው አካባቢ በየተወሰነ መጠን ብቻ ይከናወን ነበር፡፡ ይህንን ከሦስት መቶ ዓመታት በላይ ለሆነ ዘመን የተለያየ ሕዝብ እንደገና ያዋሐዱት አቡነ ተክለ ሃይማኖት ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዳሞትን ከሸዋ ጋር ካገናኙ በኋላ ወደ ወሎ በመሄድ ሐይቅ ቆዩ፤ ቀጥለውም ወደ ትግራይ በመጓዝ ደብረ ዳሞ ገቡ፡፡ ለሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የምንኩስና ሕይወት ማንሠራራት አንዱ ምክንያት የሆኑትን አቡነ መድኃኒነ እግዚእን አመነኮሱ፡፡ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ደግሞ አምስቱን ከዋክብት(አቡነ አሮን ዘክቱር፣ አቡነ መርቆሬዎስ ዘዶባ፣ አቡነ ዘካርያስ ዘኬፋ፣ አቡነ ገብረ ክርስቶስ ዘዳኅና፣ አቡነ ዳንኤል ዘጸዐዳ)ና ሰባቱን ከዋክብት በማመንኮስ(R. Basset, Etudes sur I historie d Ethiopie,.p 10) የሰሜኑን ገዳማዊ ሕይወት እንደገና ነፍስ ዘርተውበታል፡፡ በዚህም ምክንያት የሰሜኖቹ ወደ ደቡብ በመምጣት፣ የደቡቦችም ወደ ሰሜን በመሄድ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱ እንዲያንሠራራ አድርገውታል፡፡

ተስፋዬም ሆነ መሰሎቹ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ላይ የሚዘምቱት የእምነትም ሆነ የታሪክ ክርክር ስላላቸው አይደለም፡፡ ሀገሪቱ የቆመችባቸውን ተራዳዎች የመናድና እሴት አልባ የማድረግ ተልዕኮ ስላላቸው እንጂ፡፡ ይህ ተልዕኮ ደግሞ በዚህች በብዙ ቅዱሳን ጸሎት በታጠረች ሀገር ላይ ፈጽሞ የሚሳካ አይደለም፡፡ የሌለን ነገር የሚፈልግ አያገኝምና፡፡

© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት የወጣ ነው
ማስተዋሻ
አቡነ ተክለ ሃይማኖትን የተመለከተ አንድ መጽሐፍ በማዘጋጀት ላይ ነኝ፡፡ ጻድቁ በጸሎታቸው ቢረዱኝ በዚህ ዓመት መጨረሻ ላይ ይወጣ ይሆናል፡፡ እናንተም ጸልዩበት


ነዚ ብርቂ ጽሑፍ እናንበብኩም ከሎኹም፡ መለሳ ኪኾነኹም ካብ ናይ ተጋዳላይ ተኽለ ክፍለማርያም (ወዲ ትዅል) ዜማታት እናመረጽኩም ክትሰምዑ ትኽእሉ ኢኹም፡ ንኣንፍኹም ናይ ጀነራላት ተኽለ ልብሱን ተኽላይ ሃብስሉስን ተኽለ ማንጁስን፡ቃለመጠይቓት ክትሰምዑ ትኽእሉ ኢኹም፡ ታሪኽ ምንባብ ትፈትው እንተደዀንኩም ማለት’ኡ። እዞም ኩሎም ገዳይም ሻዕብያ ኣቦታቶም መፍቀርቲ “ተኽለሃይማኖት” ከምዝዀኑ ንደቆም ካብ ዝሃብዎም ስም ንግምት። ነዚ ኣብ ልቢ ህዝቢ ዝሰፈረ ጻድቅን ቅዱስን ንምቁንጻብ ምፍታን ናይ ጥዕና ኣይዀነን ንምባል’ኡ! ጽባሕ’ከ ንመንዶዀን የቆናጽብ ይኸውን እዚ ዘረባ አንጀባራሪ ብሓባር ንርእዮ ንብል ንሕና ኤርትራዉያን ደያኑ ማእከልን መስመርን ብኤርትራዊ ጭዉነት ሓበንን ፍናንን።

ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ንስለቲ ምርምራዊ ጽሑፍኻ ደጊምና ነመስግነካ።

ኦ ኣቦና ኣቡነ እንጦንዮስ ጸሎትኩምን ኣማላድነትኩምን ኣይፈለዬና!
ኦ ኣቦና ኣቡነ ተክለሃይማኖት ጸሎትኩምን ኣማላድነትኩምን ኣይፈለዬና!
ብሩኽ በዓለ ልደተ ክርስቶስ!


Selam/
Senior Member
Posts: 16998
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: አቡነ ተክለሃይማኖት፡ ተስፋዬ ገብረአብ፡ ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን፡ ዓወል ስዒድን፡ . . . . እንኪምርመሩ

Post by Selam/ » 04 Jan 2025, 08:30

ዓይጠ መጎጡ

አቡነ ተክለ ሃይማኖት የነቀሉትን ዘንዶማ እናንተ ዕርጉም ወያኔዎች መልሳችሁ ተከላችሁት። ክልፍልፍ!

Axumezana wrote:
04 Jan 2025, 04:29
ደብተራ መለከት የደብረሊባኖሱ ተክላሃይማኖት ዞንዳቸውንና ገድላቸውን ተነቅሎ እስከ ወድያኛው ተሸኝተዋል። የሌሎችን ታሪክ ብታስታውቀን መልካም ነው።

Selam/
Senior Member
Posts: 16998
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: አቡነ ተክለሃይማኖት፡ ተስፋዬ ገብረአብ፡ ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን፡ ዓወል ስዒድን፡ . . . . እንኪምርመሩ

Post by Selam/ » 04 Jan 2025, 13:50

ይኸን ስድብ ተርጉሙልና የህግደፍና የህወሓት ደብተራዎች:


Meleket
Member
Posts: 4796
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: አቡነ ተክለሃይማኖት፡ ተስፋዬ ገብረአብ፡ ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን፡ ዓወል ስዒድን፡ . . . . እንኪምርመሩ

Post by Meleket » 06 Jan 2025, 02:42

sesame ጽቡቕ ሕቶ ኢዩ። መልሲ እስከ ኣብዚ ተወከሲ። “መን ኢዩ ትግራዋይ?” ብዚብል ርእሲ ጎይታ ነብሱ ዚተባህለ ጸሓፊ ንአቡነ ተኽለሃይማኖት ሽሕ እኳ ኣብ ሸዋ ይወለዱ እምበር፡ መሰረቶም ከም በዓል ኩስቶ "ተምቤን ኢዩ" ይብለና አሎ አብ ገጽ 2። ካልኦት ተመሳሳሊ መንፈሳዊ ታሪኽ ንዘለዎም ቅዱሳን እውን ዘርዚርዎም ኣሎ። ንአብነት
1. ቅዱስ ያሬድ [505-571]
2. አቡነ ተክለሃይማኖት [1215-1313] http://www.aigaforum.com/amharic-articl ... grayan.pdf
3. አቡነ ኤስጣቴዎስ ዘገርዓልታ [1273-1353] ሕዚ ደብረ ቢዘን ተባሂሉ ዝጽዋእ ኣብ ኤርትራ ዘሎ ገዳም መስረቱ ተኸተልቲ አቡነ ኤስጣቴዎስ እዮም።
4. አቡነ ዳንኤል ዘዋልድባ [ከባቢ 14ክ/ዘመን]
5. ነብርኢድ ይሳቅ [ከባቢ 15ክ/ዘመን]
6. አቡነ እስጢፋኖስ [ከባቢ 15ክ/ዘመን]
7. ዘርአ ያእቆብ ፈላስፋ [1599-1692]


sesame wrote:
04 Jan 2025, 07:04
I have only one question: WAS TekleHaimanot an Agame?
ብሩኽ በዓለ ልደተ ክርስቶስ!

Post Reply