ከሶማሊላንድ ጋር በተገባ የባህር በር መግባቢያ ስምምነት ከኢትዮጵያ ጋር ተፈጥሮ የነበረው ውዝግብ ተቋጭቷል-ሶማሊያ (MOU is now officially dead)
Posted: 03 Jan 2025, 15:23
ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ ያላቸውን ውዝግብ መፍታታቸውን" የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ አህመድ ሙዓሊም ፊቂ መግለጻቸውን ቢቢሲ ሶማሊ ዘግቧል
የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ አህመድ ሙዓሊም ፊቂ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ- በነጻ አገርነት ካወጀችው ሶማሊላንድ ጋር በተገባ የባህር በር መግባቢያ ስምምነት ከኢትዮጵያ ጋር ተፈጥሮ የነበረው ውዝግብ ተቋጭቷል ማለታቸውን የሶማሊ ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ መዘገቡን ቢቢሲ ሶማሊ አስነብቧል።
"አለመግባባቱ ተፈትቷል። አለመግባባቱ የተፈታው ጥያቄያችንን ወይም መርሆዋችንን ወደ ጎን በማድረግ እና ገሸሽ በማድረግ ሳይሆን የሶማሊያ ጥያቄ ቀርቦ ተቀባይነት ካገኘ በኋላ ነው" ብለዋል።
ሚኒስትሩ "የአንድን አገር መሬት ወይም ባህር የፈለግነው እኛ አይደለንም" ቢሉም ውዝግቡን በውይይት መፍታት የበሰለ አካሄድ ነው ብለዋል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሶማሊያ ያቀረበችው ጥያቄ ተቀባይነት ስላገኘ ውዝግቡ እልባት ማግኘቱን በጠቀሱበት በዚህ ንግግራቸው ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የገባቸውን የባህር በር መግባቢያ ስምምነት ሰርዛ እንደሆነ ገልጸዋል;;
https://www.bbc.com/amharic/articles/ce8e7e0p3j4o