በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ዛሬ ጠዋት ገደማ ለስራ እየተንቀሳቀሱ የነበሩ የመንግስት አመራሮችን ጨምሮ አምስት ሰዎች በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች መገደላቸውን ምንጮች ለመሠረት ሚድያ ጠቁመዋል።
በተተኮሰባቸው ጥይት የሞቱት ግለሰቦች ለስራ ጉለሌ ወረዳ 3 ላይ ቆይተዉ ወደ ፍቼ ከተማ እየተመለሱ በነበረበት ወቅት ነው ተብሏል።
የዞኑ የውሃ ሀብት ቢሮ ሀላፊ፣ የመስኖና ተፋሰስ ሀላፊ፣ የቡሳ ጎንፋ ሀላፊ እንዲሁም አንድ የቀበሌ ሊቀንመበር እና ሹፌራቸው በአጠቃላይ አምስት ሰዎች በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ወይም መንግስት 'ኦነግ ሸኔ' በሚላቸው ታጣቂዎች መገደላቸውን ምንጮቻችን ጨምረው ገልፀዋል።
የሰሜን ሸዋ ዞን በቅርብ ወራት በመንግስት ጦር እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባላት መሀል ከፍተኛ የሆነ ግጭት እያስተናገደ ይገኛል።
ከዚህ በፊት በአንፃራዊ ሰላሙ የሚታወቀው ይህ የሰላሌ አካባቢ አሁን ላይ ከፍተኛ እገታ፣ ግድያ እና ተያያዥ ጉዳቶችን በህዝቡ ላይ እያስከተለ እንደሆነ ይታወቃል።
ምንጭ:
(መሠረት ሚድያ)-
ከተማዋ በዚህ መልክ ደምቃለች ሰው ግን በኑሮ ውድነት እና በመሳሰሉት ጠውልጎል