Page 1 of 2

PLACE & TIME: THE FUNDAMENTAL PRINCIPLE OF EXISTENCE! THE CASE OF ADDIS ABEBA!!!

Posted: 03 Jan 2025, 01:16
by Horus
የሰው ባህሪም ሆነ የአንድ ማህበረሰብ ሶሺያል ሳይኮሎጂ ብቻ ሳይሆን ታሪክና ካልቸር ከቦታና ግዜ ጋር የተፈተሉ ናቸው! የአዲስ አበባ መዘመን ዝም ብሎ የአንድ ቦታ መጽዳት ብቻ ሳይሆን የከተማ እቅድ (urban design) አርት ነው። ቦታ በዲዛይን ሲለወጥ የግለሰቦች ሳይኮሎጂና የማህበረሰብ ካልቸር አብሮ ይለወጣል ። ለዚህ ምሳሌው በዚች አጭር ወራት ውስጥ የተከሰተው የህዝብ ባህሪ ነው። ይህን ሁሉ ሚሊዮን ሰው በሚንጋጋበት አዲስ የኮሪደር መንገድ አንዲት ብጣቂ ወረቀት መሬት ላይ ተወርውሮ አለማየት ፍጹም ፍጹም አስገራሚ የካልቸር ለውጥ ነው ። ይህ ብቻ ሳትሆን ሲጃራ የሚያጨስ ሰው ማየት ሁሉ ብርቅ እየሆነ ነው ። አጃይብ ያስብላል! ሳይንስ ዝንፍ አይልም! የሰዎችን ባህሪ ለመለወጥ አንዱ ግዙፉ ዘዴ ቦታቸውን መለወጥ ነው!!!

Re: PLACE & TIME: THE FUNDAMENTAL PRINCIPLE OF EXISTENCE! THE CASE OF ADDIS ABEBA!!!

Posted: 03 Jan 2025, 01:24
by Horus
IF YOU WANT TO CHANGE THE BEHAVIOR A PEOPLE, CHANGE THE PLACE AND TIME IN WHICH THEY LIVE. DITTO.

Re: PLACE & TIME: THE FUNDAMENTAL PRINCIPLE OF EXISTENCE! THE CASE OF ADDIS ABEBA!!!

Posted: 03 Jan 2025, 01:45
by Horus
BOTH IN LIFE AND NATURE, ONE THING LEADS TO ANOTHER. IN MOST CASES BIRDS OF THE SAME FEATHER FLOCK TOGETHER. SIMILAR THINGS ATTRACT EACH OTHER. CLEAN GOES WITH CLEAN. DIRT GOES WITH DIRT. BEAUTY ATTRACTS BEAUTY. THESE CORRIDORS WILL ATTRACT MORE CORRIDORS OF THEIR TYPE.

Re: PLACE & TIME: THE FUNDAMENTAL PRINCIPLE OF EXISTENCE! THE CASE OF ADDIS ABEBA!!!

Posted: 03 Jan 2025, 01:54
by Horus
ከራሳቸው ጋር እየተዋወቁ ያሉት ኢትዮጵያዊያን!!

Re: PLACE & TIME: THE FUNDAMENTAL PRINCIPLE OF EXISTENCE! THE CASE OF ADDIS ABEBA!!!

Posted: 03 Jan 2025, 02:17
by Horus

Re: PLACE & TIME: THE FUNDAMENTAL PRINCIPLE OF EXISTENCE! THE CASE OF ADDIS ABEBA!!!

Posted: 03 Jan 2025, 02:46
by Right
Dedeb Cadre,
You sale a money laundering scheme of artificial decorations as development.
Even among the thieves there is a smart thief vs a stupid thief.
At least the Weyannies stolen money through the ring road & Gerd. Abiye Ahmed Ali & BERHANU Nega are stealing through a dollar store light fixtures. MAFERIA.
MOLACHA LEBA.

Re: PLACE & TIME: THE FUNDAMENTAL PRINCIPLE OF EXISTENCE! THE CASE OF ADDIS ABEBA!!!

Posted: 03 Jan 2025, 03:00
by Selam/
ጭልፊቱ - አሁንም በጣም መሃይም ነህ። በአንተ ቤት Place & Time የሚል buzz word ተጠቅመህ አጭበርብረህ ሞተሃል።

ደርግና ወያኔ ድሃው ህዝብ እንዳይታይባቸው በቆርቆሮ አጥር ይሸፍኑት ነበር። ዕርጉሙ ዓብዮት ደግሞ እስከ ጭራሹ ከመሃል ከተማ አባረራቸው። ልክ እንዳንተ በደብተር ወረቀት ዕጣን እየጠቀለሉ የሚሸጡት፣ አሮጌ መፅሐፍ ለአንባብያን የሚያቀርቡት፣ ኮንዶም፣ ካልሲም የሚሸጡት፣ ሎተሪ የሚያዞሩት፣ የተመራረጠ ካሴት፣ የጥርስ መፋቂያ፣ መስቲካ ወዘተ የሚሸጡት አሁን አንተ ከምትለጥፋቸው ኮሪዶሮች ላይ ተነቅለዋል። ይኸን ስል ግን ተሸጋሸጉ ማለቴ እንጂ ጭራሹን ጠፉ ማለቴ አይደለም ምክንያቱም ኑሯቸው ባሉበት ቦታ ሳይሆን የተሻሻለው ችርቻሮና ሱቅ በደረቴያቸውን ይዘው ወደ ሌላ ቦታ ነው የተገፉት።

ታዲያ ዛሬ ኮሪደሩ ላይ ያን አብሮ አደግህን የከተማ አውደልዳይ ፍየል፣ ያን ጦም-አዳሪውን ውሻ፣ የሙዝ ልጣጭና የቂጥህ መጥረጊያ የነበረውን ባለ መስመር ወረቀት፣ ከድሃ የጠዳው ኮሪዶርህ ላይ ልታየው ናፈቀህ እንዴ?

እንዳልከው ሰው በድንገት ሰልጥኖ ቢሆን ኖሮ፣ እንደልቡ መንገድ ላይ ጠግቦ በልቶ፣ የተረፈውን ምግብና መጠቅለያ ወረቀት ወርውሮ ጥሎ የቆሻሻ መጣያዎቹ ሞልተው እናያቸው ነበር። ነገር ግን ምንም የሚጣልም የሚተርፍም ነገር የለም። ለምንድነው የቆሻሻ መጣያዎቹ ባዶ የሆኑት ብለህ ባዶ ጭንቅላትህን ጠይቀው። ኮሪዶሩ በሰለጠነበት ዘመን አንተ ለምን የህይወት ምንጭ የሆነችውን እናት እንደ በረንዳ-አዳሪ እንዲህ ትሁን እንዲያ ትሁን እያልክ እንደምታዋርዳትም ቁሬማ ራስህን ጠይቀው።

የጊዜና የቦታ ተፅዕኖ ማለት እንግዲህ ይኸው ነው። ጊዜ ድሆችን ከቦታቸው አፈናቀላቸው፣ አንተንም ከሰው ወደ ጭልፊትነት ለወጠህ።
ቦታ የተባለውም በአንድ በኩል ግማሽ መልኩን አሳምሮ መስብዕ ሆነ፣ አሮጌው ጎኑን ደግሞ ድሃ ልጆቹን ይዞ ከእይታ ተሸሸገ።

Re: PLACE & TIME: THE FUNDAMENTAL PRINCIPLE OF EXISTENCE! THE CASE OF ADDIS ABEBA!!!

Posted: 03 Jan 2025, 13:07
by Horus
የመሸታ ቤት ለፍዳዳ መሃይም ሁላ ... ባዶ ቅል እራስክን በቀይ ቀለም ስድብ መለቅለቅ የሕይወትህ አላማ የሆነ እበት!

ተማር....
የመሸታ ቤት መሃይሞች መለፋደድ ተዘግቶ የሥራ ክቡርነት ዘመን ተገብቷል! ከጥቂት ግዜ በኋላ ያንቺም አላማ አልባ ሹል አፍ ይዘጋል :lol: :lol: :lol:
የሰው ባህሪም ሆነ የአንድ ማህበረሰብ ሶሺያል ሳይኮሎጂ ብቻ ሳይሆን ታሪክና ካልቸር ከቦታና ግዜ ጋር የተፈተሉ ናቸው! የአዲስ አበባ መዘመን ዝም ብሎ የአንድ ቦታ መጽዳት ብቻ ሳይሆን የከተማ እቅድ (urban design) አርት ነው። ቦታ በዲዛይን ሲለወጥ የግለሰቦች ሳይኮሎጂና የማህበረሰብ ካልቸር አብሮ ይለወጣል ። ለዚህ ምሳሌው በዚች አጭር ወራት ውስጥ የተከሰተው የህዝብ ባህሪ ነው። ይህን ሁሉ ሚሊዮን ሰው በሚንጋጋበት አዲስ የኮሪደር መንገድ አንዲት ብጣቂ ወረቀት መሬት ላይ ተወርውሮ አለማየት ፍጹም ፍጹም አስገራሚ የካልቸር ለውጥ ነው ። ይህ ብቻ ሳትሆን ሲጃራ የሚያጨስ ሰው ማየት ሁሉ ብርቅ እየሆነ ነው ። አጃይብ ያስብላል! ሳይንስ ዝንፍ አይልም! የሰዎችን ባህሪ ለመለወጥ አንዱ ግዙፉ ዘዴ ቦታቸውን መለወጥ ነው!!!

Re: PLACE & TIME: THE FUNDAMENTAL PRINCIPLE OF EXISTENCE! THE CASE OF ADDIS ABEBA!!!

Posted: 03 Jan 2025, 14:14
by Right
የሥራ ክቡርነት ዘመን
Dedeb Cadre,
Painting BIKE LANE on the street of Addis in a language 99.5% Ethiopians don’t understand with money borrowed in their name is a job you are proud of. Why is it a priority in a city with 50% unemployed youths.
Everybody knows it is a money laundering scheme.
The plan is for the unemployed to join the Army to kill the Amharas.
Ethiopia will have justice on Abiye Ahmed Ali & BERHANU Nega as the Libyans had on colonel Gaddafi, very soon.
MOLACHA LEBA.

Re: PLACE & TIME: THE FUNDAMENTAL PRINCIPLE OF EXISTENCE! THE CASE OF ADDIS ABEBA!!!

Posted: 03 Jan 2025, 15:40
by Selam/
ጭልፊቱ - ሌላ ስድብ ፈልግ፣ እኔ ሰላም አልኮልና ሥጋ ያለበት ቦታ የማልደርስ ፅድት ያልኩኝ ኩሩ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብዬሃለሁ።

አንተ ግን በልጅነት አይምሮህ ውስጥ የተቀረፀው የጭድ ተራ የመሸታ ቤትና የሸርሙጣ ጉራንጉር እስከ አሁን ስላልለቀቀህ፣ ግጥምህም ዜማህም ስለ ሴተኛ አዳሪና ዝሙት ነው። ታጥበህ የማትፀዳ ሽንፍላ ስለሆንክ፣ “ኮሪዶር ኮሪዶር ስልጣኔ ስልጣኔ” ብለህ ትጮህና ተመልሰህ ወደዛው ወደ አደግክበት እርምጥምጥና ቆሻሻ ህይወት ትዘቅጣለህ። አቶ ዓብዮት ኮሪዶር መስራት ያለበት በአንተ አናት ላይ ነው። ድውይ!

Re: PLACE & TIME: THE FUNDAMENTAL PRINCIPLE OF EXISTENCE! THE CASE OF ADDIS ABEBA!!!

Posted: 03 Jan 2025, 16:46
by Abere
ይኸ ነገር እንዴት ነው ጊዜ ከታዋቂው ደራሲው አባባል ጋር ይቃረን ይሆን ወይስ

" አንድን ሰው ከገጠር ልታወጣው ትችላለህ፤ ገጠርን ግን ከሰውየው ልታወጣው አትችልም''

ትልቁን ምስል እናስተውል። ኢትዮጵያ የምትቀየረው አዲስ አበባ ላይ አንድ ነገር ሲቀየር ብቻ ነው። ያውም 4 ኪሎ የመሸገውን ጭራቅ ስታስወግድ። ያ እስካልሆነ ድረስ ጠብ ሲል ስደፍን አይነት የህዝብ ዕንባ ይቀጥላል። ታጥቦ ጭቃ ነው።

Re: PLACE & TIME: THE FUNDAMENTAL PRINCIPLE OF EXISTENCE! THE CASE OF ADDIS ABEBA!!!

Posted: 03 Jan 2025, 16:48
by Naga Tuma
Horus wrote:
03 Jan 2025, 01:16
የሰው ባህሪም ሆነ የአንድ ማህበረሰብ ሶሺያል ሳይኮሎጂ ብቻ ሳይሆን ታሪክና ካልቸር ከቦታና ግዜ ጋር የተፈተሉ ናቸው! የአዲስ አበባ መዘመን ዝም ብሎ የአንድ ቦታ መጽዳት ብቻ ሳይሆን የከተማ እቅድ (urban design) አርት ነው። ቦታ በዲዛይን ሲለወጥ የግለሰቦች ሳይኮሎጂና የማህበረሰብ ካልቸር አብሮ ይለወጣል ። ለዚህ ምሳሌው በዚች አጭር ወራት ውስጥ የተከሰተው የህዝብ ባህሪ ነው። ይህን ሁሉ ሚሊዮን ሰው በሚንጋጋበት አዲስ የኮሪደር መንገድ አንዲት ብጣቂ ወረቀት መሬት ላይ ተወርውሮ አለማየት ፍጹም ፍጹም አስገራሚ የካልቸር ለውጥ ነው ። ይህ ብቻ ሳትሆን ሲጃራ የሚያጨስ ሰው ማየት ሁሉ ብርቅ እየሆነ ነው ። አጃይብ ያስብላል! ሳይንስ ዝንፍ አይልም! የሰዎችን ባህሪ ለመለወጥ አንዱ ግዙፉ ዘዴ ቦታቸውን መለወጥ ነው!!!

አዲስ አበባ በኮሪደር መልማት ለኢትዮጵያ መልማት ምሳሌ ብትሆን የኢትዮጵያ በትይዩ መልማት ገና ኣይዴለም?

በቅርብ ግዜ ነዉ እዚሁ ፎረም ላይ ሳይንስ ይዛነፋል ብለህ ብትከራከረኝ ሳይንስ ከሆነ ኣይዛነፍም ብዬ የመለስኩልህ።

ኣሁን ሳይንስ ዝንፍ ኣይልም በምለዉ ተስማማን።

ዘመን ተሻጋሪ ባህል በቅጽበት ወይም በኣብዮት የሚቀየር ኣይዴለም። ባህልን መምራት ብልህነትን ያስፈልጋል።

ከኢትዮጵያ ላይወጡ የተወራጩት ኢትዮጵያን ኣብረን እናሳድግ ማለት ገና ኣልተለማመዱም። ሰፈሮቻቸዉ ገና ብዙ ልማት ይጠብቀዋል።

ደጃ ኒዉስ ላይ የደነዘ ኣሁንም ኣዉቃለሁ ብሎ አፍ ይከፍታል።

ይህ የልማት አቅጣጫ በቀልድ የመጣ ይመስል ዛሬም ይቀለዳል።

አዲስ አበባ እየገዘፈች ሲቲ ስቴት እየሆነች ይመስላል። አስተዳደሯ ኣብሮ እየዘመነ ነዉ?

ቡሾፍቱ ግዙፍ አየር ማረፍያ እየተገነባ ነዉ የሚል ዜና ሰምቼ ነበር። ይህ ማለት ዲ ፋክቶ የሲቲ ስቴት አካል ትሆናለች ማለት ነዉ።

በአዲስ አበባ ዙርያ ያሉ ወረዳዎች በፍላጎት የሲቲ ስቴት አካል መሆን ከፈለጉ የስቴቱ አስተዳደር ከአርባን ዲዛይን በላይ ምሳሌ የሚሆን ነዉ። ሌሎችም አስተዳደሮች ምሳሌዎች ሊሆኑ ይችላሉ። ሌሎችን ሳይጠብቁ ከተንቀሳቀሱ።

የምትለጥፋቸዉ የኮሪደር ልማቶች ዉስጥ ድንቅ የምህንድስና ስራዎች ይታያሉ። የምህንድስና ትምህርት ምን ያህል ተምረሃል?

Re: PLACE & TIME: THE FUNDAMENTAL PRINCIPLE OF EXISTENCE! THE CASE OF ADDIS ABEBA!!!

Posted: 03 Jan 2025, 20:26
by Horus
Abere wrote:
03 Jan 2025, 16:46
ይኸ ነገር እንዴት ነው ጊዜ ከታዋቂው ደራሲው አባባል ጋር ይቃረን ይሆን ወይስ

" አንድን ሰው ከገጠር ልታወጣው ትችላለህ፤ ገጠርን ግን ከሰውየው ልታወጣው አትችልም''

ትልቁን ምስል እናስተውል። ኢትዮጵያ የምትቀየረው አዲስ አበባ ላይ አንድ ነገር ሲቀየር ብቻ ነው። ያውም 4 ኪሎ የመሸገውን ጭራቅ ስታስወግድ። ያ እስካልሆነ ድረስ ጠብ ሲል ስደፍን አይነት የህዝብ ዕንባ ይቀጥላል። ታጥቦ ጭቃ ነው።

አብረ፣
ሁለት ስህተቶችን ፈጽመሃል፤ ኣንዱ ከላይ ያለው ተረትና እኔ ያልኩት አንድ አይደሉም። ጥቅሱን ያለ ቦታው አስገባሃው። ሁለተኛው አንድ ቦታ ሲለወጥ ሌላ ቦታ ይለወጣል አላልኩም። ሰው ቦታው ሲለወጥበት ባህሪው ይለወጣል ነው ያልኩት። ለዚህ ትክክለኛ ቅዋሜ ካለው እንስማው ። አንድን ሰው ከገጠር ልታወጣው ትችላለህ ግን ገጠርን ከስውዬው አታወጣውም የሚለው ቢበዛ ቢበዛ ስለ ሰውዬው personality makeup and his thought structure ቢሆን እንጂ ስለ ሰው ባህሪ (behavior) ፍጹም ስህተት ነው።

አንድ ባላገር ገጠር ሲኖር ሽንት የሚወጣው ጫካ ውስጥ ከሆነ አዲሳባ ሲመጣ መንገድ ላይ አሩን ሊያራ አይችልም ። በግድ ሽንት ቤት መጠቀን ይማራል። ባህሪ ምን እንደ ግልጽ ሁን፣ ባህሪ ማለት ቢሄቪየር ሲሆን ያ ደሞ የሰው ልጅ የሚሰራው ፣ በአይን የሚታይ የሰው ስራ ማለት ነው ። ጠላ መጠጣት ባህሪ ነው። ጸሎት መጸለይ ባህሪ ነው። መንገድ ላይ ወረቀት መጣል ባህሪ ነው። የዛሬ ዓመት ፋኖ አዲስ አበባን ይስተዳድራል ብሎ ማሰብ ሃሳብ ነው። ሃሳብ በተግባር ሲሰራ ባህሪ ይሆናል። ካልተሰራ ባህሪ አይሆንም። ይህ አንደኛው ስህተትህ ነው።

ሁለተኛው አንድ ቦታ ሲለወጥ ሌላ ቦታ ይለወጣል የሚለው ለውይይት የሚቀርብ ነገር አይደለም፣ ድንቁርና ነው። ቦታ ሰው አይደለም ፣ ተግባር አይፈጽምም፣ ሥራ አይሰራም ። አዲሳባ ሲለወጥ ወሎ አይለወጥም። ወሎ የሚለወጠው የወሎ ሰው ሲለውጠው ነው። ሰውና ቦታ የተለያዩ ካታጎሪዎች ናቸው።

ዞሮ ዞሮ ሳይንስ የኛን ስሜትና ፍላጎት ለማስደሰት አይለወጥም ። Facts don't bend to fit our desires. በጸዱት ኮሪደሮች ላይ ሰዎች ቁሻሻ መጣል ማቆማቸው fact ነው። በቃ!

Re: PLACE & TIME: THE FUNDAMENTAL PRINCIPLE OF EXISTENCE! THE CASE OF ADDIS ABEBA!!!

Posted: 03 Jan 2025, 20:43
by Horus
ናጋ ቱማ፣
አንተና የኦሮሙማ ወገኖችህ የምታካሂዱት ትርክ ወደኔ አታምጣው። እሱን እዛው ጨርሱት! ላንተ ያለኝ ጥያቄ ፤ ባህሪና ባህል ያላቸው ልዩነት ምን እንደ ሆነ እስቲ ነገረን? ባህል ምን እንደ ሆነ ከዚህ ቀደም ያስተማርኩህን ታስታውሰዋለህ?

Re: PLACE & TIME: THE FUNDAMENTAL PRINCIPLE OF EXISTENCE! THE CASE OF ADDIS ABEBA!!!

Posted: 03 Jan 2025, 22:14
by Selam/
ጭልፊቱ

ይኸ ከላይ ወደታች የወረደ አስተሳሰብህ ለውትድርና እንጂ ለከተማ ዕድገትና ለስነ-ህንፃ አይሰራም። ህንፃ ብቻውን ሰውን የሚቀይር ቢሆን ኖሮማ Chateau Rogue ልክ Saint-Thomas d'Aquinን ይመስል ነበር ፣ አንተም እንደ ጭድ-ተራ ማሰብ ታቆም ነበር። አሜሪካ የሚኖረው ሃበሻ ዘመናዊው ከተማ ውስጥ ተጣጥሞ የሚኖረው እኮ በቅድሚያ የኢኮኖሚ መሰላል ላይ ተንጠላጥሎ ኑሮውን ማስተካከል ስለቻለ ነው።

ኑሮውን ለማሻሻል ምንም ዕድል ያልተፈጠረለት ድሃ የኢትዮጵያ ህዝብ መኖሪያውን የቀማው ህንፃ ልማዱን ይለውጠዋል ማለት ግን የመጨረሻ ሹፈት ነው።

በሌላ በኩል አቶ ዓብዮት በህልሙ ያያቸውን ነጫጭ የአፓርታማ ዲዛይኖች አስገንብቶ፣ ዕልፍ ሰዎችን ከበሻሻ አስመጥቶ እንደፍየል ሊያጨቃቸው ይችላል። ህንፃው የሰዎቹን ባህል፣ ወግና ልማድ መጠበቅ፣ ማጠናከርና ማሻሻል ሲገባው፣ ሰዎቹ ባዕዱን ግንብ ይምሰሉ ተገደውም ይለወጡ ማለት ግን ጨካኝነትና ድንቁርና ነው።

በእኔ አስተያየት፣ ነዋሪዎቹን በሁሉም ሂደት በማሳተፍ የተስማሙበትን የመኖሪያ ሰፈር የሰራው የቦትስዋናው ከንቲባ፣ የተሻለ ተፈጥሯዊና መሬት የረገጠ ለውጥ አስመዝግቧል።

አቶ ዓብዮት የሚያስበው ልክ እንደ ምስራቅ አውሮፓ ወታደርዊ አገዛዝ ነው። እነሱ ነፍ የሆነ አንድ ዓይነት ግራጫ አፓርትመንቶች ገንብተው ከተሜውንና ገጠሬውን እስከነ አሳማው አጉረውት ነበር። ዓላማውም ሰዎቹ እንደ ህንፃው አንድ ዓይነት እንዲመስሉና አንድ ዓይነት ነገር እንዲያስብ ነው። የዚህ ዓይነት ከላይ ወደታች የተዋቀረ አሰራርና ሰዎችን በህንፃ ልክ ለመቅረፅ የሚደረግ ቤተ-ሙከራ የደነቆረ ብቻ ሳይሆን አደገኛ የሆነ አካሂድ ነው። በተለይም ብዙ ቀለምና የተለያየ የኑሮ ደረጃ፣ ባህልና ልምድ ላለው የአፍሪካ ውብ ህዝብ በጣም የወረደ አስተሳሰብ ነው።

Re: PLACE & TIME: THE FUNDAMENTAL PRINCIPLE OF EXISTENCE! THE CASE OF ADDIS ABEBA!!!

Posted: 04 Jan 2025, 14:10
by Abere
ሆረስ፥

እኔ እንደ ጥያቄ ነው ያቀረብኩት። አንድ ሰው ከገጠር ወደ ከተማ ብታስገባው፤ አዲሱ ቦታ (ከተማ) ገጠራዊ ልማዱን እና እሳቤውን ያጠፋዋል ወይ ነው። ለምሳሌ ከገጠር ወደ ከተማ የፈለሱ የከተማ ኗሪዎች ብዙ ልጅ የመውለድ፤ እንደ ገጠር ቤተሰብ አይነት አኗኗር ይበዛባቸዋል። Immigrants high fertility and continue the same lifestyle as the countryside.

ሌላው አዲስ አበባ ከኢትዮጵያ ጋር የተመጣጠነ ልማት ሳይሆን የብዝበዛ እና ማቆርቆዝ ላይ ነች። አዲስ አበባ ጥገኛ እና መጣጪ ነች። Addis Ababa is a primate city where no other second city in the country accounts having 10% of Addis Ababa. It is an obese city with urban disease, unemployment and unfair wealth accumulation.

Addis Ababa has no multiplier effect on the nation, it has an exploitative relationship. If it can trigger change in the rest of the country what is the point of all the so-called BS propaganda of OLF-PP.

Horus wrote:
03 Jan 2025, 20:26
Abere wrote:
03 Jan 2025, 16:46
ይኸ ነገር እንዴት ነው ጊዜ ከታዋቂው ደራሲው አባባል ጋር ይቃረን ይሆን ወይስ

" አንድን ሰው ከገጠር ልታወጣው ትችላለህ፤ ገጠርን ግን ከሰውየው ልታወጣው አትችልም''

ትልቁን ምስል እናስተውል። ኢትዮጵያ የምትቀየረው አዲስ አበባ ላይ አንድ ነገር ሲቀየር ብቻ ነው። ያውም 4 ኪሎ የመሸገውን ጭራቅ ስታስወግድ። ያ እስካልሆነ ድረስ ጠብ ሲል ስደፍን አይነት የህዝብ ዕንባ ይቀጥላል። ታጥቦ ጭቃ ነው።

አብረ፣
ሁለት ስህተቶችን ፈጽመሃል፤ ኣንዱ ከላይ ያለው ተረትና እኔ ያልኩት አንድ አይደሉም። ጥቅሱን ያለ ቦታው አስገባሃው። ሁለተኛው አንድ ቦታ ሲለወጥ ሌላ ቦታ ይለወጣል አላልኩም። ሰው ቦታው ሲለወጥበት ባህሪው ይለወጣል ነው ያልኩት። ለዚህ ትክክለኛ ቅዋሜ ካለው እንስማው ። አንድን ሰው ከገጠር ልታወጣው ትችላለህ ግን ገጠርን ከስውዬው አታወጣውም የሚለው ቢበዛ ቢበዛ ስለ ሰውዬው personality makeup and his thought structure ቢሆን እንጂ ስለ ሰው ባህሪ (behavior) ፍጹም ስህተት ነው።

አንድ ባላገር ገጠር ሲኖር ሽንት የሚወጣው ጫካ ውስጥ ከሆነ አዲሳባ ሲመጣ መንገድ ላይ አሩን ሊያራ አይችልም ። በግድ ሽንት ቤት መጠቀን ይማራል። ባህሪ ምን እንደ ግልጽ ሁን፣ ባህሪ ማለት ቢሄቪየር ሲሆን ያ ደሞ የሰው ልጅ የሚሰራው ፣ በአይን የሚታይ የሰው ስራ ማለት ነው ። ጠላ መጠጣት ባህሪ ነው። ጸሎት መጸለይ ባህሪ ነው። መንገድ ላይ ወረቀት መጣል ባህሪ ነው። የዛሬ ዓመት ፋኖ አዲስ አበባን ይስተዳድራል ብሎ ማሰብ ሃሳብ ነው። ሃሳብ በተግባር ሲሰራ ባህሪ ይሆናል። ካልተሰራ ባህሪ አይሆንም። ይህ አንደኛው ስህተትህ ነው።

ሁለተኛው አንድ ቦታ ሲለወጥ ሌላ ቦታ ይለወጣል የሚለው ለውይይት የሚቀርብ ነገር አይደለም፣ ድንቁርና ነው። ቦታ ሰው አይደለም ፣ ተግባር አይፈጽምም፣ ሥራ አይሰራም ። አዲሳባ ሲለወጥ ወሎ አይለወጥም። ወሎ የሚለወጠው የወሎ ሰው ሲለውጠው ነው። ሰውና ቦታ የተለያዩ ካታጎሪዎች ናቸው።

ዞሮ ዞሮ ሳይንስ የኛን ስሜትና ፍላጎት ለማስደሰት አይለወጥም ። Facts don't bend to fit our desires. በጸዱት ኮሪደሮች ላይ ሰዎች ቁሻሻ መጣል ማቆማቸው fact ነው። በቃ!

Re: PLACE & TIME: THE FUNDAMENTAL PRINCIPLE OF EXISTENCE! THE CASE OF ADDIS ABEBA!!!

Posted: 04 Jan 2025, 14:25
by Horus
አበረ፣
በመጀመሪያ ነጥብ ላይ ተባባልንኮ! ባህል እምነት ነው፤ ሃሳብ ነው። ባህል የሚገለጸው ወይም የሚተገበረው በባህሪ ወይም በስራ ነው። አንድ ባላገር የባላገር ባህሉ/እምነቱን ይዞ አዲሳባ ይመጣል። እምነቱን ባንጎሉ ይዞ መኖር ይችላል ግን ባህሉን ከተማ ውስጥ መተግበር አይችልም ። ስለዚህ ወይም አውቆና ወዶ አለያም በነባራዊ የከተማ ባህል ተገዶ ባህሪውን ይለውጣል። ይህ ሳይንስ ነው ። ቦታ ሰውን ይለውጣል።

ሁለተኛ ያነሳሃው የፖለቲካ አቋምህ ስለሆነ መምትህ ነው ። እኔ አዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ቁጭ ብዬ ስንት ሰው አዲሳብ ይግባ፣ ስንቱ ይከልከል! ስንቱ ተገዶ ወሎ ይስፈር ስንቱ ካዲሳባ ተነስቶ ደምቢዶሎ ይወሰድ ለማለት ስልጣን ላይ አይደለሁም ! አንተ ያሻህን በይን! እኔ ስለ አዲሳባ እድገት ፍጥነትና ስንት መቀነስ እንዳለበት ያልኩት ነገር የለም! ያ ያንተ ሃሳብ ስለሆነ ልታስተምረን ትችላለ!

እኔ በዚህ ሃረግ መክፈቻ የጠቀስኩትን ግን ልትሽረው አትችልም ፣ በምርምር የተረገጋገጠ ሳይንስ ነው! ፋክት ነው።

Re: PLACE & TIME: THE FUNDAMENTAL PRINCIPLE OF EXISTENCE! THE CASE OF ADDIS ABEBA!!!

Posted: 04 Jan 2025, 14:35
by Selam/
የከተማ መሻሻል የሰዎችን መጥፎ ባህል በዘላቂነት ሊለውጥ የሚችለው የሰዎቹ ኑሮ አብሮ ሲሻሻል ብቻ ነው።

ለምሳሌ በሰለጠኑት ሃገራት የህዝብ ማመላሻ ሲሻሻል፣ ሲስፋፋና የኪራይ ብስክሌቶች አቅርቦት ሲኖር፣ ሰዎች ከግል አውቶሞቢል ይላቀቃሉ፣ ጤናቸው ይሻሻላል፣ የአየር ብክለትም ይቀንሳል። የስራ ቦታዎች፣ የመኖሪያ ሰፈሮች፣ የትራንስፖርት አቅርቦቶችና የተለያዩ የገቢ ምንጭ ያላቸው ነዋሪዎች ሲሰበጣጠሩና ሲቀናጁ አንዱ ከአንዱ እየተመጋገቡ የሁሉም የኑሮ ደረጃ አብሮ ይሻሻላል፣ የህዝቦች ማህበራዊ ስብጥር ይጠናከራል፣ የትራንስፖርት ጫና ይቀንሳል።

ድሃውን ወደ ዳር በመግፋት፣ ሃብታሙን ብቻ መሃል ላይ በመጠቅጠቅ፣ መብራት በማሸብረቅና አስፋልት በማነጠፍ እውነተኛ መሻሻልና የአኗኗር ለውጥ ይመጣል ብሎ ማሰብ ራስን ማሞኘት ነው። እርግጥ ነው፣ ብልጭልጭ መብራቱና ነጫጬ ህንፃ ለመሃይም ካድሬዎች ዋነኛ የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ነው።

Re: PLACE & TIME: THE FUNDAMENTAL PRINCIPLE OF EXISTENCE! THE CASE OF ADDIS ABEBA!!!

Posted: 04 Jan 2025, 14:38
by Abere
ሆረስ፤

እኔ ሰው የለውጥ ሃይል ይመስለኛል። ሰው በአስተሳሰብ ሲለወጥ አካባቢውን ይለውጣል። ያለውጥ ደግሞ ዘላቂ፤ ቀጣይ፤ ተቀጣጣይ ሁኖ ይፋፋማል። አንድ በንጉሰነግስቱ ወቅት የነበሩ ፕሮፌሰር በደቡብ አካባቢ የሞደል ሽንት ቤቶች በከተማዎች ለህዝብ የማለማመድ ጥረት በተመለከተ የነገሩኝ ነበር። ብዙዎች ስላልተመቻቸው ድንጋይ በኪሳቸው ይዘው እየገቡ ተጠቅመው ሲጨርሱ ሽንት ቤቱን በድንጋይ በመሙላት ከጥቅም ውጭ እንዳደረጉት። I hope you heard the CADU and WADU success stories during Majesty's time.

ዛሬ ከ50 አመታት በሗላ ግን የገጠሩ ገበሬ ከአባት እናት እርስቱ የትም ሳይሄድ በዛው በጓሮው ሽንት ቤት ሰርቶ እየተጠቀመ ይገኛል። በዐይኔ የገጠሩን ህዝብ ኑሮ አይቸዋለሁ - አይደለም የከተማው። ያ የገጠር ህዝብ ባህርይ ለውጥ የመጣው በበርካታ የትምህርት እና ዕውቀት ማስፋፋት ነው። ከመሰረተ ትምህርት መሰረተ ጤና እስከ መደበኛ ትምህርት የአርሶ አደሩ ልጆች ዘመናዊ አኗኗር እውቀት።
ቦታ እንደ እስር ቤት ሰውን የማስገደድ ሳይሆን ሰው በህሊናው ማወቅ መቻል፡ የሚፈልገውን መሰረታዊ ነገሮች ማግኜት።

Horus wrote:
04 Jan 2025, 14:25
አበረ፣
በመጀመሪያ ነጥብ ላይ ተባባልንኮ! ባህል እምነት ነው፤ ሃሳብ ነው። ባህል የሚገለጸው ወይም የሚተገበረው በባህሪ ወይም በስራ ነው። አንድ ባላገር የባላገር ባህሉ/እምነቱን ይዞ አዲሳባ ይመጣል። እምነቱን ባንጎሉ ይዞ መኖር ይችላል ግን ባህሉን ከተማ ውስጥ መተግበር አይችልም ። ስለዚህ ወይም አውቆና ወዶ አለያም በነባራዊ የከተማ ባህል ተገዶ ባህሪውን ይለውጣል። ይህ ሳይንስ ነው ። ቦታ ሰውን ይለውጣል።

ሁለተኛ ያነሳሃው የፖለቲካ አቋምህ ስለሆነ መምትህ ነው ። እኔ አዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ቁጭ ብዬ ስንት ሰው አዲሳብ ይግባ፣ ስንቱ ይከልከል! ስንቱ ተገዶ ወሎ ይስፈር ስንቱ ካዲሳባ ተነስቶ ደምቢዶሎ ይወሰድ ለማለት ስልጣን ላይ አይደለሁም ! አንተ ያሻህን በይን! እኔ ስለ አዲሳባ እድገት ፍጥነትና ስንት መቀነስ እንዳለበት ያልኩት ነገር የለም! ያ ያንተ ሃሳብ ስለሆነ ልታስተምረን ትችላለ!

እኔ በዚህ ሃረግ መክፈቻ የጠቀስኩትን ግን ልትሽረው አትችልም ፣ በምርምር የተረገጋገጠ ሳይንስ ነው! ፋክት ነው።

Re: PLACE & TIME: THE FUNDAMENTAL PRINCIPLE OF EXISTENCE! THE CASE OF ADDIS ABEBA!!!

Posted: 04 Jan 2025, 15:05
by Selam/
አንድ ሌላ ነገር በጥያቄ መልክ ላቅርብ፥

በአዲስ አበባ የተሰሩት የህዝብ መዝናኛዎችና ፓርኮች በእርግጥ የህዝብ ናቸው ወይ፣ ማንንስ ነው በዋነኝነት እያገለገሉ ያሉት?

እንደሰማሁት ከሆነ ረብጣ ገንዘብ ካልከፈልክ ፓርክ ውስጥ አትገባም። አብዛኛው ህዝብ ደግሞ ፓርክ ውስጥ መዝናናት ሳይሆን የናፈቀው፣ ዳቦ መግዥያ ነው የተቸገረው። ታዲያ 80%ቱን ነዋሪ ፓርኩን እንዳይጠቀም ከልክለኸው፣ ህዝባችን በፅዳት አጠባበቅ ሰልጥኗል ብትል የኔ ውሻ ሳትቀር ትስቅብሃለች።

እኔ ፓርክ መሰራቱን አልተቃወምኩም ግን ቀደምትነት የሚሰጠው ለመብላት፣ ለመጠጣት፣ ለተመጣጣኝ ፍትህና ሰላም ነው መሆን ያለበት ነው ያልኩት።