ጃዋር መሀመድ በውቃቢ መንፈስ በስለት መወለዱን ራሱ በፃፈው መፅሐፉ አስፍሯል
Posted: 01 Jan 2025, 16:21
የጃዋር መፅሐፍ ሲገለጥ
#Ethiopia | ግለ-ታሪኩን ዳጎስ ባሉ ማለፊያ መልእክቶች አጅቦ፣ ጥሩ በሚባል አገላለፅ ከትቦታል። ለአንድ ሰው ከራስ በላይ እማኝ ላሳር ነውና የራሱ ብእር ያፈለቀውን ከልጅነት እስከ እውቀት ገድል ለታሪክ ማኖሩ አሌ የማይባል ጀብደኝነት ነው። ገድል በራስ ሲዘከር ሚዛን መሳቱ ሳይታለም የተፈታ ቢሆንም ትርክቱን እንደጨው ለማጣፈጥ የገቡ እውነታዎች ግን ለብዙሀኑ ጥያቄዎች ምላሽ የሚሆኑ ናቸው።
በመጀመሪያዎቹ ምእራፎች የተመለከትኳቸው፣ እንደዋዛ የተቀመጡ ስለ ጃዋር የህይወት ጅማሮ የሚተርኩ ገፆች ይህ ሰው ስለምን “የደማስቆ መንገደኛ” ሊሆን እንደበቃ በጥቂቱም ቢሆን ይጠቁሙናል።
መፅሀፉን ሲገለጥ ጃዋር፣ ጂኒ (ጋኔን) ከምትባል ስፍራ በስለት እንደተወለደ ይተርካል። “ጂኒ (ጋኔን) ከተማ ተወልጄ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወደ ጎሎልቻ ወረዳ፣ ጩሉል ጭርቅሳ ተወሰድኩ።” (ገፅ
ያቺ ታሪካዊ የጃዋር የትውልድ ቦታ ለምን ጋኔን እንደተባለችም ገልፆታል። ክርስቲያን የነበሩ እናቱ፣ ለጃዋርን አባት ሲታጩ ሰለሙ።
በተከታታይ ሴት ልጆችን የወለዱት እናቱ፣ ወንድ ልጅ እንዲሰጣቸው ለሼክ ሁሴን እንደሆነም በዚያው ምእራፍ ገልጾታል። በገጽ 11 ላይ “በእድለ-ቢስነትዋ” ያዘነችው እናቴ በአካባቢው ባሕል መሠረት ለሼኽ ሁሴን ተሳለች። “ቀጥሎ የምወልደውን ልጅ ወንድ አድርግልኝ፤ ወንድ ልጅ ካልሆነ ግን አምጥቼ በቀዬህ (ድሬ ሼኽ ሁሴን) እጥላለሁ” ብላ በዛቻ ተማጸነች።እያለ “በርሶ መጀን” ተብሎ በሳቸው የውቃቢ መንፈስ ወደዚች ምድር ብቅ ማለቱን ከትቦታል።
የውልደት ታሪኩ በዚያ ብቻ ያበቃ አይደለም። ጀዋረ የተባለ ከሼክ ሁሴን ውቃቢ የመጣ አመድ እንዳበሉትም በመፅሀፉ ውስጥ አስፍሯል። “አንደተባለውም አናቴ አምስተኛ ላይ ወንድ ልጅ ወለደች። ያንን ጀዋረ አጎረሱኝ፡ ስሜንም ሙሐመድ ጀዋር ብለው ሰየሙኝ። ትምሀርት ቤት ስመዘገብ መምህራኖቹ ሙሐመድን ጀዋር በሚለው አሳጠሩት።” (ገፅ 12)
ከዚያም ቀጠለ። አእምሮን ስለሚበርዘው የጫት ታሪክ። በደንብ ነብስ ሳያውቅ፣ የህይወትን ትርጉም በቅጡ ሳይረዳ የተዋወቀዉ የምርቃና ህይወት ጋር ዝምድናውን አጠናክሮ ቀጠለ። በአናቱ ላይ የኦነግ ሰንሰለት ተከተለ። በጨቅላ እድሜው የተጠመቀው የኦነግ ጠበል የሁለት አለም ሰው አደረገው።የፖለቲካ መሰላልን “ሀ” ብሎ ያስጀመረው ኦነጋዊ ትርክት የአሁን ማንነቱን መቅረፁን በለሆሳስ ያወጋናል።
ፈረንጆች The end justifies the means የሚል አባባል አላቸው። የዛሬ በሴራና አሜኬላ የተሞላ ህይወት የትላንቱን ጠባሳ ማሳያዎች ናቸው። “አንገቱን በሜንጫ….” እያለ ከፍቅር ይልቅ ጥላቻን የመስበኩን ምስጢር መቋጫ፣ እፁብ - ድንቅ፣ የተባለላቸውን ማህበራዊ ትውፊቶችቻችን እና እሴቶችችን ለመናድ ማስ ዳየመሮጡ ጉዳይ በራሱ ምህዋር እየጦዘ፣ ለታሪክ በተወልን “የእኔነት ማህደር” ይፈታዋል።
ይቀጥላል…
አዲስ አበባ በምሽት። አስደናቂ ...