ሃገራዊ ትረካችን ባለፉት ሃምሳ ዓመታት
Posted: 31 Dec 2024, 13:18
ትረካ ያልኩኝ በእንግሊዘኛ ናራቲቭ የሚባለዉን ለማለት ነዉ።
ሃገራዊ ብሔራዊ ማለትም ይቻላል።
ሃገር ለሁሉም ዜጎችዋ ከለላ ናት።
ይህን በጥልቅ ያስተዋሉ ዜጎችዋ ሃገራዊ ትረካቸዉ ወጥ ወይም ኮሄረንት ነዉ። ሃገር የሁላችንም ከለላ ናት ማለት የማይችሉ ዜጎች ሃገራዊ ትረካቸዉ የተዛባ ወይም ኢንኮሄረንት ይሆናል።
ባለፉት ሃምሳ ዓመታት ሃገራዊ ትረካ ከግዜ ወደ ግዜ ምን ያህል ወጥ ሆኖ ዛሬ ደረሰ? ምን ያህልስ የተዛባ ሆኖ ነበር?
መዛባቱ ከምን ግዜም በተለይ ዘቅጦ የነበረዉ መቼ ነበር?
ይህን ለመገምገም መቶ የማይተዋወቁ ዜጎችን በደንብ የታሰቡበትን ጥያቄዎችን በመጠየቅ መገመት ይቻል ይሆናል።
አሜሪካኖች ስለ ዐለም ዜና ግድ ዬለሾች ናቸዉ ተብለዉ ቢታሙም ስለ ፕሌጅ ኦፍ አሌጅያንስ እና ናሽናል ኣንተም ወጥ የሆነ ማስተዋል ኣላቸዉ ማለት የሚቻል ይመስለኛል።
የእኛ ሃገራዊ ትረካዉ እንደዚህ ወጥ የሆኑ እነዚህ ናቸዉ ማለት ያስቸግረኛል።
የህፃንነት ዕድሜዬን ሳልጨርስ እ ኢ አ መስከረም ሁልት፣ አስራ ዘጠኝ ስልሳ ሰባት ጠዋት ያየሁኝን ወይም ያሳየኝን መቼም ኣልረሳም።
በወጣትነት ዕድሜዬ የዛሬ ሰላሳ ሶስት ዓመታት በፊት ጀምሮ መታዘብ የጀመርኩኝም ኣይረሳም።
እ ኢ አ ከስልሳ ሰባቱ ኣብዮት በኋላ የሰማንያ ሶስቱ ስብሰባ ተከሰተ።
በሁለቱ ግዜዎች ሃገር ያስተናገደችዉ ሃገራዊ ትረካዎች የተለያዩ ነበሩ።
የበለጠ ወጥ ወደ ሆነ ነበር ወይስ ወደ መዛባት ነበር ያቀናዉ?
ከዛም ከሃያ ኣንድ ዓመታት በፊት እ ኢ አ ዉሳኔ ዘጠና ስድስት እና በዛ ዉሳኔ ዙርያ የነበረ ንቅናቄ ተከሰተ። ከዛም ምርጫ ዘጠና ሰባት ተከሰተ።
በእኔ ማሰላሰል ምርጫ ዘጠና ሰባት ተያያዥ ቢሆንም ዉሳኔ ዘጠና ስድስት ዙርያ የተከሰተዉ ንቅናቄ ኣሁን ኢትዮጵያ ዉስጥ ላለዉ የፖለትካ ኣቅጣጫ የበለጠ ጉልህ ሚና ያለዉ ይመስላል።
ዉሳኔ ዘጠና ስድስት እና ምርጫ ዘጠና ሰባት አከባቢ ሃገራዊ ትረካ ከምን ግዜም በታች ዘቅጦ የነበረ ይመስለኛል።
ይህ ማሰላሰል እዉነትነት ካለዉ ባለፉት ሃምሳ ዓመታት የሃገራዊ ትረካችን መዛባትን መገምገም ኣስቸጋሪ ነዉ?
ለሃገራዊ ትረካ መዛባት የማይዘነጋ ኣንድ ኣመልካች ነጋሶ ግዳዳ የፍልስፍና ዶክተሬት ይዞ ርዕሰ ብሔር ሆኖ ከሰራ በኋላ ኣንድ ቃለ መጠይቅ ዉስጥ የኣፄ ምኒልክ የአደዋ ዉሎ መከበር ኣለበት ማለት የከበደዉ ነበር።
በዚህ ግዜ የሃገራዊ ትረካችን መዛበት የቀነሰ ቢሆንም የከሰመ ኣይመስልም።
ሃገር የሁሉም ዜጎችዋ ከለላ ናት ማለት እና ይህን ከለላ ሁሉም ዜጎች የመጠበቅ ሀላፊነት ኣለባቸዉ ማለት ምን ያህል ከባድ ነበር? የከለላ ሉዓላዊነት ስር እኩልነት ይስፈን እየተባለ።