Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
netsi
Member
Posts: 188
Joined: 06 Oct 2019, 04:29

በትናንትናው እለት በ100 አመታቸው ያረፉት የቀድሞው የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጂሚ ካርተር የኢትዮጵያ ወዳጅ ነበሩ

Post by netsi » 30 Dec 2024, 11:18

በትናንትናው እለት በ100 አመታቸው ያረፉት የቀድሞው የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጂሚ ካርተር የኢትዮጵያ ወዳጅ ነበሩ
የካርተር ማዕከል (The Carter Center) እንደ ትራኮማ፣ የጊኒ ትል በሽታ፣ ወባ እና ወዘተ ያሉ በሽታዎችን ከመከላከል እስከ የምግብ ምርት ማሳደግ እንቅስቃሴዎች እንዲሁም ከምርጫ ታዛቢነት እስከ እርቅ ማፈላለግ ባሉ ስራዎች ላይ በሀገራችን በስፋት ተሳትፋል።
አንዳንድ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ምናልባትም የጂሚ ካርተር ተቋም በአለም ዙርያ ካሉት ስራዎቹ ሁሉ ትልቁን ያከናወነው በኢትዮጵያ ነው፣ በዚህም በአብዛኛው የሀገራችን የገጠራማ አካባቢዎች ነዋሪ ተጠቃሚ ሆኗል።
ብዙዎች የካርተር ማዕከልን የሚያስታውሱት ምርጫ 97'ን ተከትሎ የተገደሉ ንፁሁንን በማውገዙ እና ምርጫው ላይ የታዩ ጉድለቶችን በግልፅ በማሳወቁ ነበር። ደርግ ሊወድቅ ሰሞን ደግሞ በኮሎኔል መንግስቱ እና በህወሓት እንዲሁም የኤርትራ ሀይሎች መሀል የሰላም ንግግር ናይሮቢ ላይ አስጀምረው ነበር።
የአሜሪካ ተንታኞች ጂሚ ካርተርን ከቀደሙት መሪዎች ሁሉ ከስልጣን ከወረዱ በሗላ ከፍተኛ ተፅእኖ የፈጠሩት ናቸው ይሏቸዋል፣ ሀገራችንም አንዷ ተጠቃሚ ነበረች።
እናመሰግናለን፣ ነፍስ ይማር!

ራሱን የሚከተለውን ማራኪ የገጠር ውበት እያዩ ያዝናኑ። ይህ የገጠር ውበት አውሮፓ እና እስያ ላይ ያሉ ናቸው። በዚሁ የት ሀገራት ሊሆኑ እንደሚችሉ ይገምቱ። Stunning Rural Villages Like Never Before! [media]
[/media] A stunning blend of natural and man-made beauty.

Affable
Member
Posts: 638
Joined: 15 Jul 2023, 13:21

Re: በትናንትናው እለት በ100 አመታቸው ያረፉት የቀድሞው የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጂሚ ካርተር የኢትዮጵያ ወዳጅ ነበሩ

Post by Affable » 30 Dec 2024, 11:44

Ethiopians and Eritreans were widely accepted first as refugees to US during the Carter administration. More than any other US president his impact on the region has been enormous.

Post Reply