Page 1 of 1

"የመንግስት ለውጥ ለማድረግ አይደለም የምንቀሳቀሰው” ጃ-war

Posted: 28 Dec 2024, 06:10
by Wedi
"የመንግስት ለውጥ ለማድረግ አይደለም የምንቀሳቀሰው” ጃ-war

ጃ-war እይነገረን ያለው፤፟

1. የአብይ አገዛዝ (ኦህዴድ-ብልጽግና) ከተገረሰሰ ሥልጣን ከኦሮሞ ፖለቲከኞች ዕጅ ሊወጣ ይችላል። ያ ከመሆኑ በፊት ጫና በመፍጠር አሁን ሀገሪቱ ላይ የተፈጠረውን የሕዝብ ብሶትና ቁጣ የተወሰኑ የፖለቲካ ማሻሻያዎች በማድረግ አስተንፍሰን ኦህዴድ-ብልጽግና እንዲቀጥል እናድርገው እያለ ነው ማለት ነው። ወይም

2. የመንግስት ለውጥ ለማድረግ ቢፈልግ እንኳን በትህነግ ጊዜ እንዳደረገው ኦህዴድ ውስጥ ካሉ ሰዎች ጋር አንድ ላይ ሆኖ የኦሮሞ ወጣቶችን/ ቄሮዎችን/ ለሕዝባዊ አመጽ ለማንቀሳቀስ የሚያስችል ዕድል አሁን ላይ የለኝም ብሎ ያስባል ማለት ነው።

ያ ካልሆነ "ሀገሪቱ በታሪኳ አይታ በማታውቀው መንገድ አደጋ ላይ ነች። ወደ መበታተንም እየሄደች ነው። እነ አብይም ሰው የማይሰሙ ዕብሪተኞች ሆነዋል። " ብለህ ከደመደምክ በኋላ "የመንግስት ለውጥ ለማድረግ አይደለም የምንቀሳቀሰው" ማለት በፍጹም አይገናኙም።


Please wait, video is loading...

Re: "የመንግስት ለውጥ ለማድረግ አይደለም የምንቀሳቀሰው” ጃ-war

Posted: 28 Dec 2024, 06:52
by Wedi
ጃ-warን በወፍ በረር
*******************

Please wait, video is loading...