Page 1 of 1

Ticking time bomb: very low salary of civil servants with no doubt dethrones Abiy. Salary of Civil servants vs security

Posted: 26 Dec 2024, 03:06
by Abaymado
ከዚህ ቀደም ብሎ ኢንዳልኩት ሲቪል ሰራተኞች በዚህ አገር በየትም አገር የሌለ ደሞዝ ነው የሚከፈላቸው፡፡ አሁን መንግስት ደሞዝ ጨምርኩ የሚለው ቀልድ ነው ፡ ብሩ ምንም መሸፈን የማይችል እንደሆነ ሁሉም የሚረዳው ነው፡፡ የሚያሳዝነው አንድ የዲግሪ ምሩቅ ከጽዳት ሰራተኛ እኩል ሲከፈለው ማየት ነው፡፡
ወደድንም ጠላንም አለምን እዚህ ያደረሳት የተማረ ሃይል ነው፡፡ እኛ አገር ግን የተማረ ሃይል ዋጋ እንደሌለው እና ወዛደርነት ዋጋ እንዳለው ይታመናል፡፡ ምን አይነት ዝቅጠት ነው?

ከዚህ በፊት አንድ የዲግሪ ምሩቅ የሚያገኘው መነሻ ደሞዝ 4609 ሲሆን ለግብርና ለጡረታ ሲነሳለት በእጁ የሚደርሰው 3652 ብር ነው፡፡ አሁን ይህ ብር ይባላል? በአሁኑ ግዜ ምን ይሰራል?

በአሁኑ ሰአት ነዳጅ ጨምሯል፡ ትራንስፖርት ዋጋ ጨምሯል፡ ኑሮው በጣም ውድ ነው የሆነው፡፡ በዛ ላይ አገራችን በተከተለችው ገበያ መር፡ ብር ዋጋውን አጥቷል፡፡ ድሮ አንድ ዶላር 57 ብር የነበረው አሁን ወደ 127 ገደማ ደርሷል፡፡ ይህ በሰራተኛው ላይ ከፍተኛ ተጽኖ አለው፡፡

እናስ?
መንግስት ደሞዝ እጨምራለሁ አለ፡፡ ሰራተኛውም በተስፋ ጠበቀ፡፡ ራሱ መንግስት ባሰማራቸው ኢንተርኔት አርበኞች የሚጪመረው ደሞዝ ይህ ነው ኢያሉ ለሰራተኛው ያለሆነ ተስፋ ሰጡ፡፡ ግን እውነተኛ ሲወጣ ሰራተኛው ማማረር ይዟል፡፡ የተጨመረው ከ 1500 አይበልጥም፡፡

የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው ቀድሞ ያገኝ ከነበረው መነሻ 4609 ወደ አዲሱ እርከን ሲሄድ 7447 ገደማ ሆነለት፡፡ በእጁስ ምን ያህል ይደርሳል፡ ቀድሞ 3652 የነበረ ሲሆን አሁን 5300 ነው፡፡ ይህ ብር ምን ይገዛል?

ጥበቃ vs ሲቪል ሰራተኞች ደሞዝ
የሚያሳዝነው መንግስት ለጥበቃ የሚከፍለው መጠን ነው፡፡ ለጥበቃዎችም ጭማሪ ተደርጓል፡፡ እናም አስደንግጦግኛል፡፡ ለፌደራልና ለፖሊስ አባላት የተጨመረው ዶክተር የማያገኘውን ብር ነው ፡፡

አንድ ዶክተር በእጁ የሚያገኘው የተጣራ ብር ከ 9000 አያልፍም፡፡ ግን አንድ የፖሊስ አባል ለምሳሌ ረዳት ኢንስፔክተር በእጁ የሚደርሰው ወደ 13,000 ነው፡፡ የምንሄድበት አካሄድ ትክክል ነው?



Re: Ticking time bomb: very low salary of civil servants with no doubt dethrones Abiy. Salary of Civil servants vs secur

Posted: 26 Dec 2024, 03:18
by Fed_Up
10 billion dollar በላይ ይሚፈጅ ቤተመንግስት እየተሰራላችሁ ነው:: መንገዶች ከኤሽያ አገሮች በለማ የገና በአል አምፖለች ሸብርቃለች:: እና ይሄ አይበቃችሁም? የምን ማማረር ነው:: ህዝቡ ይህን ልማት ካዩ እና ከሰሙ ከምግብ በላይ ነው:: ለምንስ ሳይበላ አይከረምም... ለምንስ መንገድ አይታደርም?

የብሻሻው አራዳ ህኅቡን በህልም ቅቤ እያበላ እርሱ ንጉስነቱን እያጠናከረ ነው:: እሱ እና ጀሌዎቹ ምን ተእዳቸው ብርጭቆ መስለው በዝምታ የሚማቅቀው ህዝብ እንደማይነካቸው ስላወቁ ዝም ጭጭ ነው:: አቤት ይሄ ጉድ ግብጽ ህዝብ ላይ ሆኖ ቢሆን... ዋው! መንግስታቸውን ይቦነቁሩት ነበር::

Re: Ticking time bomb: very low salary of civil servants with no doubt dethrones Abiy. Salary of Civil servants vs secur

Posted: 26 Dec 2024, 05:59
by Abaymado

Re: Ticking time bomb: very low salary of civil servants with no doubt dethrones Abiy. Salary of Civil servants vs secur

Posted: 26 Dec 2024, 06:06
by ethiopianunity
Indeed, instead of wasting unnecessary city development, creating jobs, factories, employing civil servants and use the city building waste by paying and improving the lives of workers in every institution. The superficial nature of Addis development ( except essential infrastructures such as roads) , the focus being only Addis development. Why not start another city development in other regions? However the reason the focus in Addis is because for pp protection, the city is full of security, spying and radiation under the pretext of development. We know Yplf and Weyane is not the problem for pp as they are working targeting citizens and Ethiopias and Diaspora riches who worked hard .