የኢትዮጵያ መንግሥት ጥሰት የፈጸሙ ኃላፊዎችን ከስልጣን እንዲያነሳ የአሜሪካ የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍትህ ቢሮ ኃላፊ መከሩ
Posted: 24 Dec 2024, 14:09
የኢትዮጵያ መንግሥት፤ በሰብአዊ መብት ጥሰት የሚከሰሱ ባለስልጣናትን፤ "በተለይም የሠራዊት አባላትን በአስተዳደራዊ ፈቃድ" ከስልጣን እንዲያነሳ የአሜሪካ የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አምባሳደር ቤዝ ቫን ስካክ መከሩ።
በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች "የሚፈጸሙ ያሉ ጥሰቶች" በቀጠሉበት ሁኔታ ሁሉን አቀፍ የሽግግር ፍትህን መተግበር "አስቸጋሪ" ካልሆነም "የማይቻል" እንደሆነ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን "የሲቪክ ምህዳር መዘጋት እና በተለይም በአማራ እና ኦሮሚያ የቀጠሉትን ጥሰቶች" እንደሚያውቁ ጠቅሰዋል። እነዚህ ሁኔታዎች መንግሥት ሊተገብር እየተዘጋጀ ያለውን ሁሉን አቀፍ ሽግግር ፍትህ "አስቸጋሪ ካልሆነም የማይቻል" እንደሚያደርገው ገልጸዋል።
"ሰዎች ሀሳባቸውን ለመግለጽ፣ እውነታውን ለመናገር ነጻነት ካልተሰማቸው የፍትህ ሂደት ላይ እንደማይሳተፉ እናውቃለን። በእነዚህ ሌሎች ክልሎች እየተካሄዱ ያሉ ግጭቶችም በፖለቲካዊ ንግግር መፈታት አለባቸው" ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cvg69094qgeo