Jawar
Posted: 19 Dec 2024, 10:35
ቢቢሲ- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ስልጣን እንደመጡ ብዙ በጎ ነገሮች በንግግርም፣ በተግባርም ታይቶ ነበር። ሆኖም ብዙም ሳይቆይ የትግራይ ጦርነት ተከሰተ፤ አሁንም በኦሮሚያ እንዲሁም በአማራ ክልሎች ግጭቶች እንደቀጠሉ ነው። ረሃብ፣ መፈናቀል እንዲሁም የከተማ ኑሮ ውድነት የአገሪቱ ገጽታ ሆኗል። በአንተ እምነት ኢትዮጵያ መስመር ስታ እዚህ ውስጥ የገባችው የቱ ጋር ነው?
ጃዋር፡- ዐቢይ ከመጀመርያውም መስመር ላይ አልነበረም። . . . [መጀመርያ አካባቢ] እኛ ከህወሓቶች ጋር እንደራደር ነበር፤ ስልጣን እንደሚለቁ፤ ማዕከላዊ ስልጣን እንደሚለቁ፣ ስምምነት ላይ ከደረስን በኋላ፣ ስልጣን ከለቀቁ በኋላ ማን ይሁን? የሚለው ሲመጣ የዐቢይ ስም በመምጣቱ አነጋግሬው ነበር።ያኔ ለእኔ ግልጽ ነበር።
ኢትዮጵያ ከኢህአዴግ አንድ ፓርቲ አገዛዝ፣ ወደ መድብለ ፓርቲ፣ ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መሄድ፣ መሻገር ነበረባት፤ ወደ ግጭት የማያደርስ ያለው ብቸኛ አማራጭ እርሱ ብቻ ነበር።
ገና ስልጣን ሳይይዝ፣ገና ስሙም ሳይታወቅ፣ለእኔ ከእርሱ ጋር በነበረኝ ውይይት የዲሞክራሲ ስርዓት የመገንባት ፍላጎት እንደሌለው ግልጽ ነበር።አምባገነናዊ ስርዓትን ከአንድ ፓርቲ ወደ አንድ ግለሰብ የማሻገር ህልም እንዳለው ለእኔ ግልጽ ነበር። ለዚያ ነው የተቃወምኩት።
በወቅቱ ግን ሰዉ የሚያየው ነገር የለውጥ ስሜቱ ወያኔ [ህወሓት] ብቻ ትጥፋ እንጂ ማንም ይምጣ የሚለው ስሜት በጣም ጠንካራ ስለነበር እኔ ሰዉን ማሳመን አልቻልኩም። መጀመርያ ኦህዴዶችን፣ ቀጥሎ ሕዝቡን ማሳመን አልቻልኩም። በዚያ ምክንያት አቆምኩ እንጂ ለእኔ በጣም ግልጽ ነበር
ከዚያ በኋላ የመጀመርያው አንድ ዓመት ሲደረግ የነበረውን ሳየው ነበር። ተወያይተን ይህንን ሽግግር እንምራ የሚለው ሲመጣ እኔ አሻግራችኋለሁ ማለት፤ የጋራ ፍኖተ ካርታ ይምጣ ሲባል አያስፈልገንም የሚል ምላሽ ተሰማ።በጎ በጎው በሚታይበት ወቅት ራሱ በውስጥ በውስጡ ወደ ዲሞክራሲ የሚያሸጋግረው ኃዲድ ተስቶ ነበር። መጨረሻ ላይ የለየለት ወደ ምርጫ ሲገባ፣ ተፎካካሪ ይሆናሉ ተብለው የሚታሰቡ ኃይሎችን ወደ መምታት ሲገባ ነው ሰዉ የነቃው እንጂ ከጅምሩም ዐቢይ ኢትዮጵያን ወደ ዲሞክራሲ የማሻገር ፍላጎት ፈጽሞ ኖሮት አያውቅም።