እንዲያው ታጥቦ ጭቃ! [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ግጥም]
Posted: 18 Dec 2024, 04:05
እንዲያው ታጥቦ ጭቃ! [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ግጥም]
ኤርትራዊም ኢትዮጵያዊም እንዲነቃ፡
መቀሌም በሻሻ፡ አስመራም አምበራመጠቃ፡
ባህርዳር በሰቃ፡ ፍንፍኔም ወለቃ፡
መሆናቸው በይፋ እንዲያበቃ፡
እንዲያው ታጥቦ ጭቃ፡
አዲሳባም እንደብርሌ እንዳትነቃ፡
ኩሽ ሴም መባባሉ በይፋ እንዲያበቃ፡
የልጆች ጨዋታ እንዲያከትም ዕቃዕቃ፡
ምድሩ ላይ ትሰመር ብይኗ ደማምቃ።
መጋለብ እንዲያከትም በህዝብ ልጆች ጫንቃ፡
እንዲሁ እንዳትኖር ሓቅ ተደብቃ፡
ይፋ ትሁን ትውጣ ለሁላችን ታውቃ፡
እንዳይፏልልብን የማንም ሞልቃቃ፡
ግዙፍ ነኝ እንዳይለን የማንም ደቃቃ፡
ምድሩ ላይ ትሰመር ብይኗ ደማምቃ፡
ይህ ሲሆን ብቻ ነው የህዝቦች ፍንደቃ።
ብይን ተተግብሯል የሚሉት አባባል፡
በንጹሃን ህይወት መጫወት እንደ ጅል፡
ከድንበር ተርቆ ወንበር ላይ መፏለል፡
የድንበር ህዝቦችን ኣይችልም ሊያማልል።
ብይን ሚተገበር መሬት ላይ ተወርዶ፡
ምስክር ባለበት ሁሉም ፈቅዶ ወዶ፡
ምልክት አድርጎ ችካል ተቸክሎ፡
ሲታይ ብቻ እኮ ነው ሁሉም ተቻችሎ።
ከዚያ በተረፈ “ህድማ ኢዩ ንቕድሚት”፡
ከዚያ በተረፈ ሽሽት ነው ወደፊት፡
የድንበሩ ጉዳይ እንደ ሕገመንግሥት፡
ይቀመጥ ካላችሁ በቤተ መጻሕፍት፡
ለዚህስ ኣልነበረም ያ ሁሉ መስዋእት።
ህግ እንደማስቀደም ከቀደመ ጉልበት፡
ሃያልና ደካማ ሚቀያየርበት፡
ጊዜ የመጣ ዕለት፡
‘ዕንኪላሎ’ ማለት፡
በሕግ ካልተቋጨ ተወርዶ ተመሬት፡
ምስኪኑ ህዝባችን ያ ሁሉ መስዋእት ምን ሊፈይድለት?
በጦቢያና ኤርትራ የልብ ስምምነት፡
ብይኑ ምድር ላይ ተደርጎ ምልክት፡
እስቲ ህዝቦቻችን እፎይ ይበሉበት፡
ያመስግኑ ኣምላክን “ተመስገን” በማለት፡
ውሃና ኤሌክትሪክ በደንብ ያግኙበት፡
እጅጌ ሰብሰበው ያምሩ ወደ ልማት፡
እንዲህ ቅን ኣካሄድ የማይዋጥለት፡
ያ ኣካል ብቻ እኮ ነው የህዝባችን ጠላት።
“ላሎ ላሎ . . . ዕንኪላሎ” . . .የሚለውን የወዲ ሻውልን ሙዚቃ በመጋበዝ ተሰናበትናችሁ፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር። viewtopic.php?f=2&t=308857&
ኤርትራዊም ኢትዮጵያዊም እንዲነቃ፡
መቀሌም በሻሻ፡ አስመራም አምበራመጠቃ፡
ባህርዳር በሰቃ፡ ፍንፍኔም ወለቃ፡
መሆናቸው በይፋ እንዲያበቃ፡
እንዲያው ታጥቦ ጭቃ፡
አዲሳባም እንደብርሌ እንዳትነቃ፡
ኩሽ ሴም መባባሉ በይፋ እንዲያበቃ፡
የልጆች ጨዋታ እንዲያከትም ዕቃዕቃ፡
ምድሩ ላይ ትሰመር ብይኗ ደማምቃ።
መጋለብ እንዲያከትም በህዝብ ልጆች ጫንቃ፡
እንዲሁ እንዳትኖር ሓቅ ተደብቃ፡
ይፋ ትሁን ትውጣ ለሁላችን ታውቃ፡
እንዳይፏልልብን የማንም ሞልቃቃ፡
ግዙፍ ነኝ እንዳይለን የማንም ደቃቃ፡
ምድሩ ላይ ትሰመር ብይኗ ደማምቃ፡
ይህ ሲሆን ብቻ ነው የህዝቦች ፍንደቃ።
ብይን ተተግብሯል የሚሉት አባባል፡
በንጹሃን ህይወት መጫወት እንደ ጅል፡
ከድንበር ተርቆ ወንበር ላይ መፏለል፡
የድንበር ህዝቦችን ኣይችልም ሊያማልል።
ብይን ሚተገበር መሬት ላይ ተወርዶ፡
ምስክር ባለበት ሁሉም ፈቅዶ ወዶ፡
ምልክት አድርጎ ችካል ተቸክሎ፡
ሲታይ ብቻ እኮ ነው ሁሉም ተቻችሎ።
ከዚያ በተረፈ “ህድማ ኢዩ ንቕድሚት”፡
ከዚያ በተረፈ ሽሽት ነው ወደፊት፡
የድንበሩ ጉዳይ እንደ ሕገመንግሥት፡
ይቀመጥ ካላችሁ በቤተ መጻሕፍት፡
ለዚህስ ኣልነበረም ያ ሁሉ መስዋእት።
ህግ እንደማስቀደም ከቀደመ ጉልበት፡
ሃያልና ደካማ ሚቀያየርበት፡
ጊዜ የመጣ ዕለት፡
‘ዕንኪላሎ’ ማለት፡
በሕግ ካልተቋጨ ተወርዶ ተመሬት፡
ምስኪኑ ህዝባችን ያ ሁሉ መስዋእት ምን ሊፈይድለት?
በጦቢያና ኤርትራ የልብ ስምምነት፡
ብይኑ ምድር ላይ ተደርጎ ምልክት፡
እስቲ ህዝቦቻችን እፎይ ይበሉበት፡
ያመስግኑ ኣምላክን “ተመስገን” በማለት፡
ውሃና ኤሌክትሪክ በደንብ ያግኙበት፡
እጅጌ ሰብሰበው ያምሩ ወደ ልማት፡
እንዲህ ቅን ኣካሄድ የማይዋጥለት፡
ያ ኣካል ብቻ እኮ ነው የህዝባችን ጠላት።
“ላሎ ላሎ . . . ዕንኪላሎ” . . .የሚለውን የወዲ ሻውልን ሙዚቃ በመጋበዝ ተሰናበትናችሁ፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች በኤርትራዊ ጭዋነት ኩራትና ትህትና ጭምር። viewtopic.php?f=2&t=308857&