Page 1 of 1

Ethiopian Commercial Bank to lay off 12,000 employees following the opening of banking sector to foreign banks

Posted: 06 Dec 2024, 18:28
by sarcasm
Ethiopia is opening its banking sector to foreign banks and investors:

Bill approved

In June 2024, Ethiopia's cabinet approved a bill that allows foreign banks to establish local subsidiaries, open branches, and acquire shares in local banks.

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 12 ሺህ ሰራተኞቹን ሊያሰናብት እንደሆነ ተሰማ

(መሠረት ሚድያ)- መሠረት ሚድያ ባሳለፍነው ሳምንት ባቀረበው አንድ መረጃው ከሰሞኑ በፓርላማ የፀደቀው የመንግስት ሰራተኞች አዋጅን ተከትሎ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የመንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኞች ከስራቸው ሊሰናበቱ እንደሆነ ጠቁሞ ነበር።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ በአዋጁ አላማና አስፈላጊነት ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተው በነበሩበት ወቅት ስለ ሰራተኛ ቅነሳው ያነሱት ነገር ባይኖርም በመንግስት አቅጣጫ ከተያዘባቸው ጉዳዮች አንዱ "ከሚያስፈልገው በላይ የመንግስት ሰራተኛ አለ" የሚለው ዋናው መሆኑን ምንጮቻችን ጠቅሰው ነበር።

አዋጁ እንደ ፍርድ ቤት፣ አቃቤ ህግ፣ ፖሊስ፣ መከላከያ፣ እና ደህንነትን የመሳሰሉ ተቋማት ውስጥ የብሄር ስብጥር ለማድረግም ያለመ መሆኑን የጠቁሙት ምንጮች አዋጁ "የብሔር ብሔረሰቦች ብዙሃነት እና አካታችነት ስርዓትን ይገነባል" በሚል በመንግስት እንደታሰበ አስረድተዋል።

መሠረት ሚድያ በደረሰው አዲስ መረጃ ደግሞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 12 ሺህ ሰራተኞቹን ሊያሰናብት እንደሆነ ሰምተናል።

ከሰሞኑ የባንኩ ሀላፊዎች በተለያዩ መርካቶ አካባቢ ባሉ ቅርንጫፎች ካሉ ሰራተኞች ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት 12 ሺህ ሰራተኛ በቅርቡ እንደሚቀነስ እና ከተቀናሾች ውስጥ አንዱ እንዳይሆኑ ጠንክራችሁ ስሩ እንደተባሉ ሰራተኞቹ ጠቁመዋል።

"በቅርቡ ብዛት ያላቸው ቅርንጫፎች ስለሚታጠፉ በዚሁ አትቀጥሉም ተብለናል፣ እኛንም መግቢያ መውጫ አጥተናል" ያሉት ሰራተኞቹ እጣ ፈንታቸውን እየተጠባበቁ መሆኑን ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ከሰሞኑ በመርካቶ አካባቢ ካለው የገቢዎች እና የነጋዴው አለመግባባት እና ከቀረጥ መጨመር ጋር ተያይዞ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ተቀማጭ ገንዘቦች እየወጡ ነው ተብሏል። በተለይ ነጋዴዎች ገንዘባቸውን በብዛት ማውጣታቸው በመንግስት አካላት ጭምር ትኩረት ተሰጥቶት ውይይት እየተደረገበት እንደሆነ ታውቋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ ከአንድ ቅርንጫፍ ማውጣት የሚቻለው የገንዘብ መጠን ላይ እቀባ ሊደረግ እንደሚችል ተገምቷል።

(#ከዜናዎቻችን በሳምንቱ በቪድዮ ዩትዩብ ላይ ያቀረብናቸውን የተመረጡ መረጃዎች ቆየት ብለን በድጋሜ በፅሁፍ የምናቀርብበት አምድ ነው)

መረጃን ከመሠረት!


https://www.facebook.com/permalink.php? ... 2533862014

Warms my heart to see Ethiopian PM Abiy warn local banks to prepare for foreign competition. That was one of my big 3 policy disputes with PM Meles when I was U.S Ambassador to Ethiopia - along with opening telecom and allowing private land ownership.






The brain behind the opening of Ethiopian banking sector to foreign banks.



https://x.com/yeshegerelite/status/1848726912589566125