Page 1 of 1

በተማፅኖ እና ምልጃ ወደ ክልል ስልጣን ለመመለስ የሚንከራተተው የትህነጉ ደብረፂ፣ በቀድሞ ተላላኪው ወግድልኝ በመባሉ፣ ለሌላ ተማፅኖ እየተዘጋጀ ነው!

Posted: 06 Dec 2024, 12:18
by Za-Ilmaknun
ሲያልቅ አያምር አሉ 😂 ተራሮችን አንቀጠቀጥኩ እያለ በፈጠረው ቅዠት ራሱን አግዝፎ ለከፋ ውድቀት የተዳረገው የ ትህነግ ግባሶ፣ አሁን ደሞ ዘር ማጥፋት ፈፀሙብኝ ያላቸውን የ ኦህዴድ መኳንንቶች አባካችሁ፣ የ ክልሊቱን እንኳን ስልጣን ስጡኝ እያለ ለመለመን እግሩ እስኪቀጥን ወደ አዲስ አበባ እየተመላለሰ ነው፣፣ ጥጋብ ሲተነፍስ እንዲህ ነው :mrgreen:

በደብረጽዮን የሚመራው የህወሓት ቡድን በትግራይ እየተከሰተ ላለው ችግር የጊዜያዊ አስተዳደሩን ደካማነት በመግለጽ ለዚህም ፕሬዝዳንቱ ጌታቸው ረዳ ምክንያት መሆናቸውን በመግለጽ "ጌታቸው ተነስቶ ምክትሉ ጄኔራል ታደሰ ወረደ" ቦታውን እንዲይዙ ሃሳብ ማቅረባቸውን ጉዳዩን በቅርብት የተከታተሉት ተሳታፊ ተናግረዋል።

"ለጊዜያዊ አስተዳደሩ ሥራዎች እንቅፋት የሆናችሁት እናንተ [በደብረጽዮን የሚመራው የህወሓት ቡድን] ናችሁ" በማለት ምላሽ የሰጡት ጌታቸው ረዳ፣ በጦርነቱ የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ ቀያቸው እንዳይመለሱ አድርገዋል ሲሉም ከሰዋቸዋል።

በድርጅቱ አባላት እና አመራሮች እንዲሁም በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅናን ያላገኘው የህወሓት ጠቅላላ ጉባኤ ተካሂዶ አቶ ጌታቸው እና ሌሎችም ከፍተኛ አመራሮች ከፓርቲው ከተባረሩ በኋላ ደብረጽዮን የሚመሩት ቡድን የጊዜያዊ አስተዳደሩ መሪዎች ሥልጣን ላይ ጥያቄ ሲያነሳ ቆይቷል።

አቶ ጌታቸው የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንትነትን ቦታ የያዙት በህወሓት ውክልናቸው ነው በሚልም ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ የፌደራል መንግሥቱን ሲጠይቁ ነበር። አሁን ውዝግቡ እየተባባሰ ባለበት ጊዜም ችግሮችን ለመፍታት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በተደረገው ስብሰባ ደብረጽዮን ይህንኑ ጥያቄ አንስተዋል።

https://www.bbc.com/amharic/articles/cy47n39n7lyo


Re: በተማፅኖ እና ምልጃ ወደ ክልል ስልጣን ለመመለስ የሚንከራተተው የትህነጉ ደብረፂ፣ በቀድሞ ተላላኪው ወግድልኝ በመባሉ፣ ለሌላ ተማፅኖ እየተዘጋጀ ነው!

Posted: 06 Dec 2024, 12:28
by Za-Ilmaknun
"ጊዜያዊ አስተዳደሩ ሥራውን እንዳያከናውን 'የትግራይ ሠራዊት' ከጎናችን ነው' በማለት ሕዝቡን ግራ እያጋባችሁት ነው" በማለት የደብረጽዮን ቡድንን የወቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ "በስመ ምክር ቤት በሚል ሕዝቡን እየረበሻችሁት ነው" በማለት ወቅሰዋቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጨምረውም መንግሥታቸው የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር ሙሉ ለሙሉ ድጋፍ አድርጌለታለሁ እንደማይል በማንሳት፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ክልላዊ ምርጫ እስኪደረግ ድረስ የሚጠበቅበትን እያከናወነ እንሚቆይ ማሳወቃቸውን ስለውይይቱ ለቢቢሲ የተናገሩት ምንጭ ገልጸዋል።

በዚህ ሀሳብ ያልተደሰተው በደብረጽዮን (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ቡድን፣ አቶ ጌታቸው ከጊዜያዊ መንግሥቱ መሪነት እንዲወርዱ በያዘው አቋም የጸና መሆኑን ስማቸውን መጥቀስ ያልፈቀዱት ምንጭ ለቢቢሲ ትግርኛ ተናግረዋል።

ለወራት በዘለቀ አለመግባባት ውስጥ ያሉት የህወሓት አመራሮች ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ከፌደራል መንግሥቱ ባለሥልጣናት ጋር ቢነጋገሩም፣ የፌደራል መንግሥቱ ግን ቡድኖቹ ችግራቸውን በጋራ እንዲፈቱ በመምከር መመለሱን ምንጩ ተናግረዋል።

በዚህ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ውስጥ ቀን ሙሉ በተካሄደው ስብሰባ ላይ በክልሉ እየተካሄደ ነው በሚል በስፋት ስለሚነገረው ሕገወጥ ማዕድን ማውጣት የተነሳ ሲሆን፣ ሕዝብ እና አገርን በሚጠቅም ሁኔታ በሕጋዊ መንገድ መካሄድ አለበት ተብሏል።