ህልም ሳይንስ ኣለዉ?
Posted: 02 Dec 2024, 11:21
እኔ ኣልፎ ኣልፎ ነዉ ህልም የማየዉ። ካየሁ ኣብዛኛዉን ግዜ ግልጥ ብሎ ነዉ የሚታየኝ።
ኣፕሪል ኣስራ ዘጠኝ ወይም እዝያ አከባቢ ለሊት ኣንድ ግልጽ ህልም ኣየሁ።
ህልሙ ማይክ ታይሰን ከሌላ ሰዉ ጋር ቦክስ የሚገጥምበት ቦታ ከሌሎች ሰዎች ጋር ተቀምጬ ይጀምራል።
ግጥምያዉን እያየሁኝ ማይክ ታይሰን ግንባሩን በሀይል ሲመታ ኣስተዋልኩ።
ደነገጥኩለት እና ድምጼን ከፍ ኣድርጌ ተናገርኩለት። ሲንገዳገድም ኣየሁ።
ያዩት እና የሰሙኝ የእስፖርት ጫወታ ነዉ ብለዉ ማየት ቀጠሉ።
ብዙም ሳይቆይ ከአናቱ ጀርባ ከመሃል ወደ ቀኙ የቡጢ የምያክል እስኩዌር ክፍት ብሎ ደሙ መፍሰስ ሲጀምር ኣየሁ።
ደንግጬለት ያዉ ያዉ እያልኩ ሌላ ተመሳሳይ ቅርጽ ከጉሮሮዉ ጀርባ በተጨማሪ ተከፍቶ ደሙ በዛ በኩልም ሲፈስ ኣየሁ።
የበለጠ ደንግጬ ከእንቅልፌ ነቃሁ።
የዛን ቀን ወይም የዛን ቀን አከባቢ ስለ ኣዕምሮ አስተሳሰብ እና ስለ ቋንቋ እንደመከርኩኝ ኣስታዉሳለሁ። ምክሮቹ ተስተዉለዉ ይሁን ተቀባይነት ማግኘታቸዉን እስከዛሬ ኣላዉቅም።
ህልሙን ብዙ ግዜ እያስታወስኩኝ ህልም ሳይንስ ኣለዉ ወይ እላለሁ።
የሰዉን ትዕግስት ህልም ያገነፍለዋል ወይ እላለሁ።
ስለ ህልም ከመላ ምት ያለፈ ይህ ነዉ የሚባል ሳይንስ ኣለ?