Horus wrote: ↑28 Nov 2024, 15:14
ፈረንጆች ሶለም የሚሉት የሴም ቋንቋ ተናጋሪዎች ሰላም እንለዋለን።
Horus:
እንኳን ኣደረሳችሁ ሲባል ዐመት ዐመት ያድርስልን ነዉ የሚባለዉ፣ በዓል ሲደርስ?
ይህ ስለ በዓሉ ሳይሆን እዚህ ስለ ጻፍከዉ የተለመደ ቃል ነዉ፥ ሠላም።
የሴምም የእንግሊዘኛም ቃል ከሆነ የማን ቃል ነዉ?
እኔ መልሱን የለኝም። ጥናት የምያስፈልገዉ ነዉ ባይ ነኝ።
የእኔ የተደጋገመ ሂስ እኛ የሴም ቋንቋ የምንናገር የምትለዉ ነዉ።
እንግሊዘኛ የሴም ቋንቋ ነዉ ማለት ኣትችልም። ትችላለህ?
ማን ሴም እና ኩሽ ብሎ ክፍፍል እንደጀመረ ባላዉቅም ክፍፍሉ ኣዙሪት ከሆነብን ሰንብቷል።
ሂሴን የምደጋግመዉ ያለ ምክንያት ኣይዴለም። በጥናት ላይ የተመሠረተ ነዉ።
በዚህ ጥናት መሠረት ስህተን ትደጋግማለህ።
ሁለት ዐረፍተ ነገሮች ኣንዱ ትክክል፣ ኣንዱ ስህተት ከሆኑ ሁለቱንም ትክክል ናቸዉ ማለት ኣትችልም። ትክክለኛዉን ለይተህ በዛ መጽናት ኣስፈላጊ ነዉ።
ሁለቱ ዐረፍተ ነገሮች፥
ካህኑ ግብጣዊ ነበረ።
ካህኑ እስራኤላዊ ነበረ።
የትኛዉ ነዉ ትክክለኛዉ?
ትክክለኛዉ መልስ ከኣዙሪት ያላቅቃል። እስራኤላዊያንም ከጥንት ግዜ ጀምሮ የፍጥረት በር ቤተሰብ ኣልነበሩም ወይም ኣይዴሉም ለማለት ሳይሆን ቀጣይ ታሪካችን ከስደት በፊት ጀምሮ ነዉ ወይስ ከስደት በኋላ የሚጀምር ነዉ ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል ለማለት ነዉ። ገባህ?
ለካ ኣንተ ነህ ያለዉ ሎሬት ጥናት ግልጽ የምያደርገዉ ከስደት በፊት መጀመሩን ነዉ። የእሱን ጥናት ሳላዉቅ እኔም ያደረኩኝ ጥናት ይህንኑ ያመለክታል።
ወጣት ሆኜ የገዳ ስርዓት በተረኞች ሲከበር ኣይቻለሁ። ተራቸዉ የደረሰ ለበርካታ ቀናት በአከባቢዉ እየተዘዋወሩ ስርዓቱን ያወድሳሉ።
በጣም የገረመኝ ሌላ ግዜ አደባባይ ወጥቶ መናገር የምያሳፍሩ ቃላትን ነፃ ሆነዉ እየተዘዋወሩ ያሰማሉ። ያየሁኝ ኣብረዉ ማክበር “ፍራተርኒቲ ኢን ዘ ኦፕን ፊልድ” ማለት የሚቻል ይመስለኛል። የአሜሪካን ፍራት ሃዉስ ከዶርሜ ባሻገር ነበር ያየሁኝ።
የሚቀጥለዉ ዙር የሎሬቱም ተራ ነበር። መጥቶ ያከብራል ተብሎ ነበር። ወሬዉ ምን ላይ እንደ ደረሰ ኣላዉቅም።
ለምርምር ከሆነ ብቻ የሚከተሉትን ኣባባሎች በደንብ ኣስታዉሳለሁ።
ያ ፎሌ ፎሌ ፎሌ …
ሰልም ሀማን በሪ ኬሰ
ቃሉን እዚህ የማልደግመዉ ሀይለኛዉ ሊነጋጋ ሲል ነዉ ማለት ነዉ።
ከሠላም እና ሶለም ጋር ስለ ተመሳሰለ ይገናኛል ማለት ኣይዴለም። ቃለቱን ግን ለየብቻ ማጥናት ይቻላል።
የወደፊት የቋንቋ ጥናት ብዙ ያሳየናል። ለምሳሌ ሰባ ሰገል እና ሰግለን ያኢ ቦረና ለየብቻ ቢጠኑ ድምዳሜዉ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት ያስቸግረኛል።
ሁለት ሳይንሳዊ ርዕሶችን ኣስቀምጫለሁ።
ኣንደኛዉ ስለ ቋንቋን መናገር ኣጀማመር ነዉ። ሀሳቡን ከተለምኩኝ ሰንብቻለሁ።
ሁለተኛዉ ቃላት እና ቁሳት ወይም ቁሶች ነዉ። ይህኛዉን በቅርቡ ነዉ ያስተዋልኩኝል። ኣንዳንድ የጥንት ቃላትን በቁሳት መግለጽ ትችላለህ። ለምሳሌ ሰዴ። ፊዝካል ኦብጄክትስ ናቸዉ። ዘዴ ስትል ጽንሰ ሀሳብ ወይም ኮንሰፕት ብቻ ይሆናል።
በዚህ መንገድ ሶስቱን የኦሮምኛ፣ የሴም ያልከዉ፣ እና የእንግሊዘኛ ቃላትን ከተዛማጅ ቃላት ጋር በደንብ ማጥናት ይቻላል። ከሠላም ጋር ተዛማጅ ቃላትን ኣላስታዉስም። ይህ ማለት ዬሉም ማለት ኣይዴለም። ጥናቱን ለባለሞያዎች እተዋለሁ።
ሌላ ምክር፥ ስለ ሜይፍላወር መርከብ ታሪክ ኣነበብኩ እንጂ ኣጠናሁ ማለት ኣያምርብህም።