Page 1 of 1
አልራበንም ስንላቸዉ፣ አሯ ርቧችዋል ይሉናል፣ አሉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር፣ ይሄዉ መስረጃዉ።
Posted: 27 Nov 2024, 17:16
by DefendTheTruth
የኢትዮጵያን ስም ተጠቅሞ፣ ኢቦላን መዋጋት ለምን ተፈለገ?? ኢቦላ ኢትዮጵያ ዉስጥ ገብቶዋል?
ከልገባ፣ የአንድን አገር ስም ከመጠቀም በፊት፣ መስማማቱን መጠየቅ ግድ ይላል።
https://www.dailymail.co.uk/news/articl ... eeran.html
Re: አልራበንም ስንላቸዉ፣ አሯ ርቧችዋል ይሉናል፣ አሉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር፣ ይሄዉ መስረጃዉ።
Posted: 27 Nov 2024, 18:18
by Za-Ilmaknun
“እየተራብኩ አላስተምርም” - ሲዳማ ክልል ደራራ ወረዳ
“ተከራይ ነኝ፤ የቤት ኪራይ አልከፈልኩም። ሌሎች ወጪዎች አሉኝ፤ መሸፈን አልቻልኩም። ለምግብ ራሱ ሌላ ቦታ ከሚሠሩ ጓደኞቼ ተበድሬ ነው እየኖርኩ ያለሁት። ለመኖር በጣም እየተቸገርን ነው” ሲሉ አንድ መምህር ያሉበትን ሁኔታ ገልጸዋል።
“አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ነን” ያሉ ሌላ ደሞዝ ያልተከፈላቸው መምህር “ሰው ሳይበላ አይሠራም” ብለዋል።
“መብቴን እየሠራሁ ስጠይቅ ቆይቼ ባለፈው ሳምንት ግን ሰው ሳይበላ አይሠራምና በጣም ስላቃተኝ [ትምህርት ቤት] መሄድም ስላልቻልኩ ሥራ አቁሜ ሌላ ቦታ ከምትኖር እህቴ ጋር ተጠግቼ ነው ያለሁት” ብለዋል።
[
size=150]“እስር ቤቱን የሞሉት መምህራን ናቸው”- ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን[/size]
“ንብረታችንን እየሸጥን ነው” ያሉ አንድ የመሰናዶ ትምህርት ቤት መምህር ሁኔታውን “ፈታኝ” ብለውታል።
“ያለንን ንብረታችንን ሸጠናል። አልጋ ሸጠናል፤ ወንበር ሸጠናል፤ ቴሌቪዥን ሸጠናል። ጓደኞቼ የትዳር ቀለበታቸውን እስከ መሸጥ ደርሰዋል። . . . በዚያ ላይ ኑሮ ውድነቱ አለ። አንድ ኩንታል ጤፍ 11 ሺህ ብር ገብቷል። በቆሎ አራት ሺህ፤ አምስት ሺህ ነው የሚሸጠው” ይላሉ የሁለት ልጆች አባት የሆኑት መምህር።
“ያለው አማራጭ ወደ ተለያየ ቦታ መሰደድ ነው” ያሉ ሌላ መምህር፣ ቤተሰባቸውን ለማስተዳደር መምህራን የቤት እቃቸውን እየሸጡ መሆኑን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
“አልጋውን የሸጠ መምህር አውቃለሁ። . . . ” በማለት መምህራኑ ለልጆቻቸው ዳቦ ለማቅረብ ሲሉ ዋጋ የሚያወጡ ንብረቶቻቸውን እየሸጡ ነው ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/ce89r941785o