Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 6847
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

አብተዉ ከበደ ፉፋ ምን እና ስለማን ኣስቦ ነበር ይህን እንጉርጉሮ ያንጎራጎረዉ?

Post by Naga Tuma » 27 Nov 2024, 11:59



በጣም ኣሳዛኝ እንጉርጉሮ ነዉ።

በደንብ ካዳመጡት ምን እና ማንን ኣስቦ ነበር ያንጎረጎረዉ ያስብላል።

ለነፃነት ግንባር ታጋይ ነዉ እንዳይባል የነፃነት ግንባር ታጋይ ማለት ግንባርን ኣጋፍጦ ግንባር መድፈር ማለት ነዉ። ያዋጣል ከተባለ ይህ ታዉቆ ነዉ እንደዛ ዐይነት ትግል የሚጀመረዉ። ሳያስተዉሉ ወይም ሳይጀምሩ ገብተዉበት ወይም መሸሻ ኣድርገዉት ያልተደናገሩ ካልሆነ።

የነፃነት ግንባር ታጋይ መራራ ትግል በጋ ያልፍልኛል ብዬ፣ ክረምት ያልፍልኛል ብዬ ብሎ የማይተኛ ስለሆነ የነፃነት ግንባር ታጋይን ኣስቦ ነዉ ከተባለ ኣስታዘበዉ እንጂ ኣወደሰዉ ማለት ኣይቻልም።

በተጨማሪ ስ ህን አመኑ ያ ዱዓ ማለት ግንባርን ኣጋፍጦ ግንባር መድፈር ማለት ኣይዴለም። ስ ህን አመኑ ያ ዱዓ የማዉቃትን ዱዓ ብዬ ኛዹን ያስታዉሰኛል።

ጀግናዉን አብዲሳ አጋ ኣስቦ ከሆነ እስር ቤት ዉስጥ ያልፍልኛል ብሎ የተኛ ሳይሆን ሰብሮ ወጥቶ ጦር የመራ ነበር። ያዉም ከሃገሩ ርቆ አዉሮፓ ዉስጥ።

ጄኔራል ታደሰ ብሩ የተከበበ ግዜ ኣስቦ ከሆነ ጄኔራሉ የከበቡት ይሄዳሉ ብሎ የጠበቀ ሳይሆን ትጥቁን ኣንስቶ ከበባዉን ሰብሮ የወጣ ነበር።

ስለዚህ አብተዉ ከበደ ፉፋ ምን እና ማንን እያሰበ ነበር ይህን እንጉርጉሮ ያንጎራጎረዉ?