Page 1 of 1

አዲስ ሙላትና ልዑል ሲሳይ የጭፈራ ውድድር!!

Posted: 23 Nov 2024, 21:00
by Horus

Re: አዲስ ሙላትና ልዑል ሲሳይ የጭፈራ ውድድር!!

Posted: 23 Nov 2024, 21:06
by Horus

Re: አዲስ ሙላትና ልዑል ሲሳይ የጭፈራ ውድድር!!

Posted: 23 Nov 2024, 21:14
by Horus

Re: አዲስ ሙላትና ልዑል ሲሳይ የጭፈራ ውድድር!!

Posted: 23 Nov 2024, 21:24
by Horus

Re: አዲስ ሙላትና ልዑል ሲሳይ የጭፈራ ውድድር!!

Posted: 23 Nov 2024, 22:01
by Horus

Re: አዲስ ሙላትና ልዑል ሲሳይ የጭፈራ ውድድር!!

Posted: 25 Nov 2024, 06:48
by Naga Tuma
ሆረስ፥

እኔ እንደ አዲ ሙላት መደነስን በቀላሉ የሚችሉበት ብዙ ኢትዮጵያዊያንን ኣላየሁም።

ኣሁን ያለበት ስራ እና የሙያ ዝንባሌዉ ምን እንደሆነ ባላዉቅም ሲደንስ ባየሁኝ ቁጥር ኢትዮጵያ ዉስጥ የዳንስ አካዳሚ በጀመረ እላለሁ።

እንደሚመስላኝ ወልቅጤ ዩኒቨርዚቲ ጉራግኛ ዳንስን ለማበልጸግ ምቹ ማዕከል ነዉ። ለአዲስ ሙላት ዳንስ ችሎታዉ ዩኒቨርዚቲዉ የክብር ማዕረግ እና በጀት ካለዉ ዳንስ አካዳሚን ብያስጀምር ኣስደሳች ዉጤት ማሳየት የሚችሉ ይመስለኛል።

ለእኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ የዳንስ አካዳሚ ኣስፈላጊነት ወጥ የሆኑ አደናነስን ማግኘት እና ማስተማር ይሆናል።

ልክ እንደ ወጥ አሰራሩ፣ ጠላ አጠማመቁ፣ እርጎ ማርጋቱ፣ ወዘተ፣ የኢትዮጵያ ዳንሶች ባህላዊ ናቸዉ። አስር ቤት ገብተህ ዶሮ ወጥ ብትበላ አስር ዐይነት ዶሮ ወጥን ትቀምሳለህ።

ከዛ ሁሉ ኣንደኛ ጣፋጩን እንዴት እንደተሰራ ኣዉቀዉ የተቀሩት ዘጠኙ ቤቶች ቢደገሙ ተመሳሳይ ጣፋች ዶሮ ወጥ ታገኛለህ። ይህ ሬሲፒዉን ማዉጣት ማለት ነዉ። ምናልባት ኣሁን ወጥቶ ይሆናል። እኔ ድሮ ስለማዉቀዉ ነዉ እዚህ የጻፍኩኝ።

ዳንሱንም ብታይ አስር ሰዎች የጉራግኛ ዳንስ ቢደንሱ የተለያዩ አደናነሶችን ታስተዉላለህ።

የአዲስ ሙላት ዳንስ አካዳሚ ጉራግኛ የሚደነሰዉ እንዲህ ነዉ ብሎ ያስተምራል ማለት ነዉ።

ወልቅጤ ባይቀመጥ የዳንስ ማዕከሉን እየጎበኘ ማንቀሳቀስ የሚችል ይመስለኛል።

ኣንድ የአቡሽ ዘለቀን የቦረና ባህል ዘፈን ስሰማ ለእሱ ደግሞ የቦረና ዩኒቨርዚቲ የአንደበተ ርቱዕነት የክብር ማዕረግ ሰጥቶት የሊትሬቸር ማዕከል እንዲመራ ብያደርግ ብዬ ኣስባለሁ። የሰማነዉን የቦረና አንደበተ ርቱዕነት በሰፊዉ እንዲጠና ማድረግ ነዉ።

ኣንድ ወጥ ነዉ ከምለዉ የአቡሽ ዘለቀ የባህል ዘፈን ጋር ማወዳደር የምችል ሌላ ይህ ነዉ ለማለት ይቸግረኛል።

ኣንድ ግዜ የጉራግኛ ባህል ማስተርፒስ የምትለዉን ወደ አማርኛ ተተርጉሞ እናንብበዉ ብዬ ነበር። የጉራግኛ ባህል ጥልቀትን ለመማር።

የኢትዮጵያ ዩኒቨርዚቲዎች እንደዚህ ዐይነት ማዕከሎችን ብያስፋፉ ከተጨናነቀችዉ አዲስ አበባ ወጣ ወጣ ማለትም በሰፊዉ ይለመድ ይሆናል።

አዲ ያልኩኝ እዴሳ ወይም ህዳሴን ወይም የዚህ ዘመን ሬይነሳንስን ለማስታወስ ነዉ።

አዲ ወይም ሀዲ ዋይት ማለት ነዉ። ቀመዲ ዊት ማለት ነዉ። ዋይት እና ዊት የምታዉቃቸዉ የእንግሊዘኛ ቃላት ናቸዉ።

የመጀመርያዉ ሬይነሳንስ መሠረቱ አቴና ከተባለ የዚህ ዘመኑ መሠረቱ አክናተን ይሆናል። የማርቲን በርናል መጽሓፍን ያስታዉሳል። ብላክ አቴና ከማለት ካህን አተን ቢል የበለጠ ይገባን ነበር።

የመጀመርያዉ ሬይነሳንስ ሮናልድ ሬገንን ሻይኒንግ ሲቲ ካስባለ የዚህ ዘመኑ በጣም የላቀ እንደሚሆን ለእኔ ታልሞ የተፈታ ነዉ። ዉጤቱ ኣሁን ከምንሰማቸዉ የኮሪደር ልማቶች እጅግ የበለጠ እንደሚሆን እገምታለሁ።

ሻይን ማለት ደግሞ ሻሾ ማለት ነዉ።

ሻሾ፣ አዲ፣ ቀመዲ እያለ ቦግ ሲል ጉዲ ሰዲ ያስብላል።

Re: አዲስ ሙላትና ልዑል ሲሳይ የጭፈራ ውድድር!!

Posted: 26 Nov 2024, 22:33
by Naga Tuma
ይህን ኣስደሳች የወላይትኛ ዳንስ በአጋጣሚ ነዉ ያየሁኝ።

የኢትዮጵያ ሕብረ ትርዕትን ኣስታወሰኝ። በተለየይ ኮሌጅ ሆነን ወላይትኛ እና ጉራግኛ ዳንሶች ያስደስቱን ነበር።

እኔ የኢትዮጵያ እዴሳ ወይም ህዳሴ ለምለዉ ይህ ዘፈን እና ዳንስ ኣንድ ጉልህ ምሳሌ ነዉ።

ባህል ይቅር ብላችሁ የባህል ህዳሴ ያስባላችሁን እስቲ እዚህ አስደሳች የባህል ጫወታ ምን ሃጥኣት አለዉ?


Re: አዲስ ሙላትና ልዑል ሲሳይ የጭፈራ ውድድር!!

Posted: 26 Nov 2024, 23:36
by Horus
ዳንስ የሚለው የእንግሊዝና ቃል በኢትዮጵያ አንድ ወጥ ስም የለውም። ውዝዋዜ (ወ ወዝ ወዝ) የሚባል አለ። ይህን ቢሆን ሁሉንም አይነት ዳንሶች አያመለክትም ። እሰከስታ ፣ መውረግረግ የተለየ አይነት ንቅናቄ ነው። ወረብ ሌላ ነው ።

በጉራጌኛ ዳንስ አንድ ቃል ነው ያለው ፣ መርገጥ (ወርግጥ) ይባላል። የሸዋ ኦሮሞች ረገዳ የሚሉት አላቸው። ረገጣ ከሚለው አንድ ነው ።

ዳንስ ያንገት፣ የትከሻ፣ የወገብ፣ የእግር ንቅናቄዎች አሉት ። ሲቀጥል የነዚህ ድብልቅ የሆኑ አሉት። ብዙ የጉራጌ ዳንስ ትከሻ፣ ወገብና እግር አንድ ላይ የሚነቀንቅ ነው።

ጉራጌ ዘፈን የሚባል ቃል የለውም። ለዘፈኖች ለዜማዎች ሁሉ ያለው ቃል አንድ ነው፤ እሱም ደርስ ይባላል። ማለትም ዜማ ወይም ዘፈን ከድርሰት ጋር አንድ ነው ። ደርስ ግጥምን በዜማ መድረስ ማለት ነው!

ከዚያ በተረፈ ከአዲስ ሙላት እኩል የሚረግጡ ብዙ ብዙ የግልና የሙያ አርቲስቶች አሉ።

ዳንስ በኢትዮጵያ ውስጥ እንደ አርት፣ እንደ ኪነት ይጠናል ፣ ይከወናል ። የዳንስ አርት እንደ ሌለ አድርገው የምታወራው አይገባኝም።

ኧዲ ማለት በጉራጌኛ እኔ ማለት ስለሆነ አንተ ምን እያልክ እንደ ሆነ አይገባኝም

ኧዲ = እኔ
ደኧ = አንተ
ኩዋ = እሱ
ደሽ = አንቺ
ኪያ = እሷ
ኧኛ = እኛ
ደህም = እናንተ
ክነም = እነሱ
ክነማ = እነሱ ለሴቶች
በስረ ቃላቸው (in their etymology) ብዙዎቹ ከላቲን ጋር አንድ ናቸው ምክንያቱም ከ30% በላይ ግዕዝ የላቲን ኢቴማ ጋር አንድ ስለሆነ!!!
example - 'edi' is 'id' !

Re: አዲስ ሙላትና ልዑል ሲሳይ የጭፈራ ውድድር!!

Posted: 26 Nov 2024, 23:49
by Horus

Re: አዲስ ሙላትና ልዑል ሲሳይ የጭፈራ ውድድር!!

Posted: 27 Nov 2024, 00:06
by Horus
የድሮና ዘመናዊ ቅልቅል