Re: መርካቶን ማዘመን እንዴት?
ጭልፊቱ aka ዲዲቲ - መጀመሪያ መቼ አቃጥላችሁ ጨረሳችሁት?
Re: መርካቶን ማዘመን እንዴት?
ስለ መርካቶ ዜና ከሰማሁ ወዲህ ስለ ምርት እና መርካቶ እያሰላሰልኩኝ ነበር። የድሮ መርካቶን በመጠኑ ኣዉቃታለሁ።
እኔ የድሮ መርካቶን እንደ መሄድ ኣሰልቺ እና የማይናፍቅ ብዙ ኣላዉቅም።
ከመርካቶ ርቆ የሚኖር ቤተሰብ ከኣንድ ግዜ በላይ ታክሲን ፈልጎ መርካቶ ይደርሳል።
ለምሳሌ ኮተቤ የሚኖር ቤተሰብ ከቀናዉ ከኮተቤ መገናኛ አከባቢ፣ ከመገናኛ ለገሃር ወይም አራት ኪሎ፣ ከዛ መርካቶ ብሎ ባገኛቸዉ ታክሲዎች ዉጥንቅጡ የወጣ መርካቶ ይደርሳል።
ክረምት ከሆነ ጭቃዉ ኣያስኬድም።
ዕቃ ለመግዛት ዋጋ ስትጠይቅ ነጋዴዉ ትክክለኛ ዋጋዉን ኣይነግርህም። ለእኔ እንደዛ ዐይነት ንግድ ብልግና ነዉ።
እኔ ያደኩበት አከባቢ ባህል እንኳን በልተህ ቦርጭ ማሳየት ይቅር እና ስትበላ ጉንጭ ኣሳብጦ መታየት ኣሳፋሪ ነዉ። ኣንተ ሆዳም ማለት ዘለፋ ነዉ።
በሽታ የሚመስሉትን ቦርጮች መርካቶ ነዉ ተደንቄ በደንብ ያየኋቸዉ። ቦርጭ በሽታ ሊሆን እንደሚችል ሰንብቼ ነዉ ያወኩኝ።
ሳሰላስል መርካቶ አዲስ አበባ ዉስጥ የገበያ ቦርጭ ከመሆን ለምን ዘርዘር ብላ ሸንቀጥ ኣትልም እላለሁ።
የኣሁኗ መርካቶ ተሻሽላ ወደ አምስቱ በሮችም ሸንቀጥ ብትል የገበያ ኢኮኖሚዋ በጣም የተሻለ ኣይሆንም?
ሾላ ገበያ ሸንቀጥ ብትል ከቦሌ እስከ ኮተቤ ለምን ወደ መርካቶ ይጎርፋል?
ከጎተራ በታች የሚኖሩ ነዋሪዎች ለምን የአድኣ ጤፍ በደጃቸዉ ኣልፎ መርካቶ ድረስ ሄደዉ ገዝተዉ ኣሸክመዉ ይመለሳሉ?
እነዚህ ቀላል ምሳሌዎች ናቸዉ።
አዲስ አበባ ዩኒቨርዚቲ የኦፕሬሽንስ ሪሰርች ወይም እንደስትርያል እንጅነሪንግ ምሁራን ካሉ ግምታዊ ጥናት ማድረግ ይችሉ ይሆናል።
የአለም ባንክ ለዚህ ዐይነት ጥናት የሚሆን ጋምስ የሚባል የሞዴሊንግ ፕሮግራም ኣለዉ።
ምሁራኑ ተግባራዊ ባይሆንም ብያንስ ለአካዳሚ የሚሆን ጥናት ማድረግ ይችላሉ።
እነ አለን ግሪንስፓን ለአሜሪካ ኢኮኖሚ እንተረስት ሬት ማስተካከያ የኦፕሬሽንስ ሪሰርች ሞዴል የነበራቸዉ ከሆነ የአዲስ አበባ ዩኒቨርዚቲ ምሁራን ለአዲስ አበባ የመርካቶ ገበያ ኢኮኖሚ ሞዴል መስራት ይችላሉ።
እነ አለን ግሪንስፓን ስለነበራቸዉ ሞዴል ኣንድ የአሜሪካ ፕሮፌሰር ስያስተምር ጠቅሶት ነዉ የሰማሁኝ።

Last edited by Naga Tuma on 20 Nov 2024, 17:09, edited 1 time in total.
Re: መርካቶን ማዘመን እንዴት?
መርካቶ መዘመን የምትችለው ኢትዮጵያ መዘመን ስትችል ብቻ ነው። ኢትዮጵያ ዛሬ ጥቁር ጨርቅ ለብሳ፤ ጠጉሯን ተላጭታ፤ ልጆቿን በጦርነት ተነጥቃ ሀዘን ላይ እያለች ኦሮሙማ አብይ አህመድ ሀዘንተኛዋ ኢትዮጵያ ላይ የውሸት ቀሚስ ቢያጠልቅላት የሀዘኑ ማድያት እንባ የትም አይሄድም - የበለጠ ጎልቶ ይወጣል። ዛሬ የኢትዮጵያ በግምት 2/3ኛው መንግስት ዐልባ ፤ ህዝብ ከህክምና እና ከትምህርት አገልግሎት ውጭ ነው። አገር ያለ ትውልድ እንደት አገር ይሆናል? ሱቅ እና ህንጻ አገር ሊሆን አይችልም። ሰላም ከሌለ ድንጋይ በድንጋይ ላይ የፈራርሳል። የተራበው፤ የተገፋው፤የተፈናቀለው፤ ወዘተ ህዝብ የተሰራው የእርሱ እና ለእርሱ አለመሆኑን ጠንቅቆ ስለሚያውቅ። አድስ አበባ ከባሌ፤አሩሲ፤ወለጋ፤ሀረር የሚመጡ እንግዶችን እንጅ ከሌላ የሚመጡ ሁሉ በሯ ዝግ ነው - እነርሱ መጤዎች ናቸው።
ጭራቅ አብይ አህመድ የዳበረ የጉራጌዎች እና ሌላ ኦሮሞ ያልሆኑ ጎሳዎችን ሱቅ እያፈረሰ የኑሮ ዋስትናቸውን እያጠፋ ነው ያለው። ሰው የት ሂዶ መኖር እንደሚችል ተቸግሯል። ለምሳሌ፤ ጉራጌዎች ክልል መሆን እንፈልጋለን እራሳችንን እናስተዳድር፤ ሌላ ከተሞችን ገንዘብ አፍስሰን ለኛ ከተማ የለንም ሲሉ የተባሉት " ጉራጌ የትም ነው አገሩ - አያስፈልገውም>። የብር የትም ነው አገሩ ይባላል አይደል። ታዲያ አዲስ አበባ እንኳን ሰርተው መብላት አልቻሉም - የቄሮ እንጅ የጉራጌ አይደለም። That means, OLF-PP has effectively blocked the social and economic mobility of Gurage as it did other non-Oromos. Entrepreneurial mobility from the micro-business ( a simple non-formal activity of street vending) to ownership of big businesses is now an impossibility if one is not a member of Orommuma.

-
ethiopianunity
- Senior Member
- Posts: 10461
- Joined: 30 Apr 2007, 17:38
Re: መርካቶን ማዘመን እንዴት?
Don’t forget since Derg till pp, they are destroying everything Ethiopian which is consecutive leaders since Derg use ISM as a cover to follow pro colonialist agenda working with them. Look at the U.S it is still proud of its history posting all former presidents and heroes on U.S dollar and building statues while these pro colonial Ethiopian leaders have been destroying history, cultures, arbegnoch, regions such as Amara, our independence flags, you name it. The so called Shabia and Tplf may deceive Ethiopians by pretending to be anti pp but it is distraction and destruction. This is the moment they have been waiting for from their partners Olf. People like DDT, they name Ethiopia while destroying every asset of Ethiopia.
-
ethiopianunity
- Senior Member
- Posts: 10461
- Joined: 30 Apr 2007, 17:38
Re: መርካቶን ማዘመን እንዴት?
Abere,
Don’t be fooled, pp in fact makes it #1 enemy of Ethiopia in fact more than Shabia and Tplf, that is under the arm pit of Ethiopia acting like Ethiopian while waging war against Ethiopia, descendants of arbegnoch, etc. this is passive aggressive which such act is always successful globally targeting Ethiopians.

አንድ መንግስት ያውም አንድ አምባገነን መንግስት (refer to the Dictator's Handbook) ቁጥር አንድ ገፊ ፍላጎቱ ገንዘብ ነው ። አሁን መርካቶ ያለው ያዳነችችና የመርኬ ጦርነት ገንዘብ አምጡ ነው፣ ቀረጥ ተባለ ግብር! It is all about money.
መርካቶን ለማዘመን ያሉት አማራጮች ጥቂት ናቸው ።
የመርካቶ መሬት የተለካ የተወሰነ ነው። በዙሪያው ያሉት መኖሪያ መንደሮች ይፍረሱና ይስፋ ቢባል እንኳ በደቡብ ከአብነት አያላፍም፣ በምራብ ከአማኑኤል አያልፍም፤ በሰሜን ከነፍጠኛ ሰፈርና በምስራቅ ከሃብተ ጎርጊስ ሰፈር/ካሜሪካ ግቢ አያልፍም። እነዚህ አራት ወሰኖች ዛሬ ላይ እንኳ ግጥግጥ ብለዋል።
በአጭሩ ማድረግ የሚቻለው 4 ነገሮችን ነው፡
(ሃ) መንገዶቹን ሰፋ ሰፋ አድርጎ አስፍላት ወይም ኮብል ድንጋይ ማድረግ፣
(ለ) በመሰረቱ የመኪና ትራፊክ ማስወገድ (ከመጫንና ማራገፍ ውጭ)
(ሓ) እስከ 70% የሚሆኑትን ሱቆች 10 ፎቅ ባላቸው ብዙ የገበያ ማዕከሎች ማስገባት
(መ) እስክ 30% የሚሆኑት መደብሮች በትናንሽ ተነቃናቂ ጋሪዎች (carts) የድንኳን መደብሮች በታቀደ መልክ ማደራጀት ነው።
ከዚያ በተረፈ ከመላ ኢትዮጵያ አዲስ ንግድ ጀማሪና አዲስ ትውልድ እንደ ድሮ መርካቶ መጥቶ ከታች ለመጀመር እያንዳንዱ ግለሰብ የራሱን ፈጠራ መፈልሰፍ ይኖርበታል። ይህ ማለት ደሞ ወጣቱ በተወለደበት አካባቢና ሌላ እድል ባለባቸው ከተሞች ተመሳሳይ መርካቶን መቆርቆር ልኖርበታል። The land in Merkato is finite.
አንድ አዲስ መጪ ጀማሪ ነጋዴ ወይ ካለው ጋር መዳበል፣ ወይም ያለን ሱቅና መደብር ከሌላው መግዛት፣ እንጂ አዲስ መደብ፣ አዲስ ጉሊት፣ አዲስ ተራ መፍጠር ከማይችልበት ውጥረት ደርሷል ። ለዚህም ነው መቆሚያ መተላለፊያ የሌላው ።
ይህን መሰሉ የመርካቶ ችግርና መንግግስት ከነጋዴን በርብሮ ገንዘብ ለመሰብሰብ ያቀደውን የቀረጥና የግብር ጦርነት ለይተን መመልከት አለብን።
ለማንኛውም ሕዝብ ሁልግዜ ዘዴና ብልሃት አለው! መርካቶ እንዲያው በቢሮክራሲ ግርግር ፈርሳ የምትበተን ነገር አይደለችም!

በባህል የኖረ ሕዝብ ዘዴዉን እና ብልሃቱን የሚፈልገዉ ባህሉ ዉስጥ ነዉ።
በእግሮቹ መጓዝን የምያዉቅ ሕዝብ የከተማ ጭቃ እንዳይነካዉ እያየ እንጣጥ እንጣጥ እያለ ይራመዳል። መርካቶ ዉስጥ እኔ ብዙ ግዜ እንደዛ ተረማምጃለሁ። በደንብ ኣስታዉሳለሁ።
ያንን ዐይነት መርካቶ ነዉ ያለቦታዋ የምትገኝ ተብላ የነበረችዉ።
ሰምቼ የማላዉቀዉን የሎሬቱን ስለ መርካቶ ቅኔ ኣሁን ስሰማ ለብቻዬ በጣም ደነቀኝ። አፈ ጮሌዉን፣ ከርሳሙ ያለዉን ኣስታዉሼ።
መኪና ከአከባቢ ዘዴ ወይም ብልሃት የወጣ ኣይዴለም። መኪኖች ከዉጪ ገብተዉ ብያገለግሉም ሕዝብ ላይ ጫናን ይፈጥራሉ።
ባለሃብቶች ቁጭ ብለዉ ማየት ሳይሆን ብድግ ብለዉ ማስተካከል ይችላሉ።
መርካቶ መቼ እና ማን እንደቆረቆራት ማስታወስ ኣስቸጋሪ ኣይዴለም።
ስያሜዋን ይዛ ሰንብታለች።
ከዛ በኋላ አዲስ አበባ አከባቢ ጨምሮ ሌሎች ተመሳሳዮችን መቆርቆር ይቻል ነበር።
ይህን ማድረግ የሚቻለዉ ዉጥንቅጡ የወጣ ኣንድ ገበያን ሁሌ ማወደስ ሳይሆን ሌሎች እንዴት ኣልተቆረቆሩም ብሎ መጠየቅ ሲጀምር ነዉ።
ባህል ዉስጥ ያለ ዘዴ እና ብልሃት በቂ ቢሆን ትምህርት ቤት በተጨማሪ ባላስፈለገ ነበር።
የተለያየ ነገር ተምረን በርካቶቻችን ስለ ሃገራችን ሁኔታ እና ፖለትካ እናወራለን።
ኣሁን ደግሞ ስለ መርካቶ ኢኮኖሚ እንወያያለን።
የኢኮኖሚ ትምህርት በቀላሉ ፍንትዉ ኣድርጎ የምያሳይን ችግር እየተመለከትን እናወድሳለን።
ይህ የግብይት ችግር የመርካቶ ብቻ ኣይዴለም።
የድሬ ደዋ ገበያንም በመጠኑ ኣዉቃለሁ። ኣንዳንዴ የእህሉ እና የአቧራዉ ድንበር የማይታወቅ ይመስላል። የቅቤዉም፣ የዘይቱም እንደዛዉ።
ኣንዳንዴ ብያንስ የሚበሉ ነገሮች ከአቧራዉ ሰፈር ወጣ ማለት ይችላሉ ብዬ ኣስባለሁ። የሐረር እና ድሬ ደዋ መገንጠያ ላይ አቧራ የማይበዛበት ከፍ ያለ ቦታ ኣለ።
ድሬ ደዋ ዉስጥ ከአቧራ ጋር የሚጋፉ የሚበሉ ነገሮችን ወዲህ ኣምጡ የሚል ይመስላል። ለሐረርም ሆነ ለድሬ ደዋ ለነዋሪ ብዛታቸዉ አማካይ ስፍራ ይመስላል።
የከተማ ነዋሪዎች አስቤዛ የሚገዙት በብዛት በሳምንት ኣንድ ቀን ቢሆን ነዉ።
ይህ ማለት የገበያ ቀን ትራፊክ መቀነስ ይቻላል ማለት ነዉ።
ይህን የማነሳዉ የእኔ አስተሳሰብ ትክክል ነዉ ለማለት ሳይሆን ለብሬይንስቶርሚንግ የሚባለዉ ያህል ነዉ።
ብሬይንስቶርሚንግ የመጣልህን ሁሉ ለሰሚዎች መወርወር ማለት ነዉ። ኣንዳንዱ ወድያዉ ዉድቅ ይሆናል። ኣንዳንዱ ለተሻለ አስተሳሰብ መንገድ ይከፍታል። ኣንዳንዱ ስራ ላይ ማዋል የሚቻል ይሆናል።
የመንግስት ተቋማት በብሬይንስቶርሚንግ የሚወረወሩትን የኢኮኖሚ ጉዳይ ለማበጠር ዐቅም ያላቸዉ ከሆነ።

ጭልፊቱ - 60ዎቹ ላይ ቆመህ ለመቅረትህ ምልክቱ ሁልጊዜም መፍትሄህ አስፋልት ማንጠፍና ፎቅ መጠፍጠፍ ነው።