Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Za-Ilmaknun
- Member
- Posts: 4486
- Joined: 15 Jun 2018, 17:40
Post
by Za-Ilmaknun » 18 Nov 2024, 19:11
የደብረ ጽዮንቡድን ወደ ለየለት ሥርዓት አልበኝነት ተሸጋግሯል በማለት የገለጸው የፕሬዚዳንቱ ጽሕፈት ቤቱ፣ ‹‹በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች በሚገኙ መንግሥታዊ መዋቅሮች ላይ ሕገወጥ ምደባዎችን በማካሄድና ጫና በመፍጠር የጊዜያዊ አስተዳደሩን ሥራዎች በማደናቀፍ ላይ ተጠምዷል፤›› ብሏል፡፡
ሁኔታው ተባብሶ በመቀጠሉ ምክንያት፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩ መሰል ሥርዓቱ አልበኝነት ከአቅሙ በላይ በመሆኑ የትግራይ ፀጥታ ኃይል፣ የፍትሕ አካላትና ባንኮች እየታየ ያለውን ሕገ መንግሥቱን የጣሰ አካሄድ ተገንዝበው ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስቧል፡፡
በደብረ ጽዮን (ዶ/ር) የሚመራው ሕወሓት ከሁለት ወራት በጊዜያዊ አስተዳደሩ የሚደረገውን ሹም ሽር በተደጋጋሚ ሲቃወም ቆይቷል፡፡ በታችኛው መዋቅር የሚገኙ ምክር ቤቶች ስብሰባ በማካሄድ አዳዲስ ምደባዎችን እንደማይቀበልና አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ በካቢኔያቸው ውስጥ ያሉት አምስት ሰዎች በድርጅቱ መባረራቸውን በተደጋጋሚ ቢገልጽም፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ጽሕፈት ቤት ግን ‹‹በግላጭ መፈንቅለ መንግሥት እየተካሄደብኝ ነው፤›› በማለት በተደጋጋሚ በሚያወጣቸው መግለጫዎች እየገለጸ ነው፡፡
https://www.ethiopianreporter.com/135505/
-
Za-Ilmaknun
- Member
- Posts: 4486
- Joined: 15 Jun 2018, 17:40
Post
by Za-Ilmaknun » 18 Nov 2024, 19:16
ከአንድ ሚሊዮን በላይ የትግራይ ክልል ሕፃናት ከትምህርት ገበታ ርቀው እንደሚገኙ በሪፖርት ተገለጸ
በትግራይ ክልል ከ1.24 ሚሊዮን በላይ ትምህርት ቤት መግባት የነበረባቸው ሕፃናት ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የትምህርት ቢሮ ሪፖርት ጠቆመ።
የቢሮው ሪፖርት እንደሚያሳየው በተያዘው የትምህርት ዓመት ይመዘገባሉ ተብለው ከተጠበቁ 2.48 ሚሊዮን ተማሪዎች፣ ትምህርት ቤት የሄዱት 48 በመቶ ያህሉ ብቻ ናቸው።
የጊዜያዊ አስተዳደሩ የትምህርት ቢሮ ተዘግተው ከቆዩ 2,492 ትምህርት ቤቶች 2,105 ያህል መልሶ መክፈቱንና የተቀሩትን 387 ትምህርት ቤቶች በፀጥታ ችግሮች፣ በትምህርት ግብዓትና በመምህራን እጥረት፣ እንዲሁም ለመልሶ ግንባታ አቅም በመታጣቱ ምክንያት መክፈት እንዳልቻለ ተገልጿል።
በአሁኑ ወቅት በክልሉ ያለው
ኢኮኖሚያዊ ጫናና ረሃብ ብዙ ቤተሰቦች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ከመላክ ይልቅ፣ ለመኖር የሚያስፈልጉ መሠረታዊ ጉዳዩችን ማሟላት ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ እያስገደዳቸው መሆኑን የቢሮው መረጃ ያሳያል፡፡
https://www.ethiopianreporter.com/135464/