Hospitals in Addis Ababa are reporting that, more and more desperate people are arriving at the Hospitals offering to sell their kidneys so that they can make some money to pay for their groceries.
It was only a few years ago that government media in Ethiopia were reporting about a similar situation in Afghanistan, where an entire village of desperate people had to sell their kidneys, including that of their childrens', to make ends meet. The news was meant to provide comfort to the Ethiopian people heading in the same direction. Did it help?
የአፍጋኒስታኗ 'ባለአንድ ኩላሊት መንደር' ኑሮን ለመግፋት አካላቸውን የሸጡ አፍጋናውያን መኖሪያ መንደር
ሸንሻያ ባዛር የሚል መጠሪያ ያላት መንደሯ በርካታ ነዋሪዎቿ አንድ ኩላሊታቸውን ሸጠዋል
ኑሮ የከበዳቸው ነዋሪዎቹ “ህይወታችንን ለማቆየት ስንል ነው ኩላሊታችንን የሸጥነው” ይላሉ
በአፍጋኒስታኗ ሄራ ከተማ አቅራቢያ የምትገኘው ሸንሻያ ባዛር የገጠር መንደር በሀገሪቱ ውስጥ “ባለ አንድ ኩላሊት መንደር” በሚል መጠሪያ እየታወቀ መምጣቱ ተነግሯል።
መንደሩ ይህንን መጠሪያ እንዲያገኝ ምክንያት የሆነው ኑሮ የከበዳቸው በርከታ የመንደሩ ነዋሪዎች ገንዘብ ለማገኘት ኩላሊታቸውን በህገ ወጥ መንገድ መሸጣቸውን ተከትሎ እንደሆነም ታውቋል።
በጦርነት ስትታመስ የኖረችው አፍጋኒስታን የኢኮኖሚ ሁኔታዋ በእጅጉ የተጎዳ ሲሆን፤ ታሊባን ባሳለፍነው ዓመት ስልጣኑን መቆጣጠሩን ተከትሎ ኢኮኖሚው የበለጠ በመውደቅ በርካቶች ለቤተሰቦቻቸው የሚያቀርቡትን ምግብ እስኪያጡ አድርሷል።
ነገሮች የከፉባቸው አካባቢዎች ደግሞ ሰዎች በህይወታቸው ላይ አደገኛ ውሳኔን እስከመወሰን እንዲደርሱ ያደረገ ሲሆን፤ በዚህም ኩላሊታቸውን በመሸጥ ምግብ ለመግዛትና እዳቸውን ለመክፈል እየተጠቀሙ ነው ተብሏል።
ይህንን ተከትሎም በሄራት ግዛት የምትገኘው አንድ አነስተኛ መንደር “ባለ አንድ ኩላሊት መንደር” የሚል ስያሜ እስከማግኘት የደረሰች ሲሆን፤ ይህ የሆነውም በርካታ የመንደሯ ነዋሪዎች ኩላሊታቸውን በጥቁር ገበያ ላይ በመሸጣቸው ነው ተብሏል።
የ32 ዓመቱ ኑረዲን የልጆች አባት ሲሆን፤ ለኤ.ኤፍ.ፒ በሰጠው ቃሉ፤ “ይህንን ያደረጉት ለልጆቼ ስል ነው፤ አሁን ግን ይቆጨኛል፤ ምክንያቱም ከዚህ በኋላ ስራ መስራትም ከባድ ነገር ማሳት አልችልም፤ በከፍተኛ ህመም ውስጥ ነው የምኖረው” ብሏል።
አንድ ኩላሊቷን የሸጠች አፋጋኒስታዊት እናትም፤ “ኩላሊቴን በ250 ሺህ የአፍጋኒ ገንዘብ (2 ሺህ 900 የአሜሪካ ዶላር) ነው የሸጥኩት” ያለች ሲሆን፤ “ይህንን ማድረግ ግዴታዬ ነበረ፤ ምክንያቱም ባለቤቴ ስራ የለውም፤ የምንከፍለው እዳም ነበረብን” ብላለች።
አዚዛ ተባለችው የሶስት እናትም፤” ልጆቼ የሚበሉት አጥተው መንገድ ላይ እየለመኑ ነው፤ ኩላሊቴን ካልሸጥኩ የአንድ ዓመት ሴት ልጄን መሸጥ ይጠበቅብኝ ነበረ፤ ለዚህም ነው ኩላሊቴን የሸጥኩት” ሰትል ተናግራለች።
https://am.al-ain.com/article/residents ... to-survive