Page 1 of 1

በመቐለ ዙርያ ካሉት የእንደርታ ገጠር አካባቢዎች በሺዎች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮች መሬታቸው እየተነጠቁ፣ ከአንድ ሺህ በላይ ለሚሆኑ የቀድሞ የጦር ጉዳተኞች ሊሰጠ

Posted: 07 Nov 2024, 14:58
by Za-Ilmaknun
ሕገወጥ የመሬት ወረራ፣ በሴቶች ላይ የሚደርስ ጥቃት እና ሌሎች ወንጀሎች አሳሳቢ ሆነዋል ሲል ትንሳኤ ሰብዓ እንደርታ የተባለው ተቃዋሚው ፓርቲ ዐሳወቀ ። ፓርቲው ሕገወጥ የመሬት ወረራ በመቐለ እየተፈፀመ ነው ብሏል ።

ትንሳኤ ሰብዓ እንደርታ ትላንት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው፥ ሕገወጥ ያለው የመቐለ ከተማ አስተዳደር ከአንድ ሺህ በላይ ለሚሆኑ የቀድሞ የጦር ጉዳተኞች ሊሰጠው ያቀደው የመኖርያ መሬት እንዲታገድ ጠይቋል ። በመቐለ ዙርያ ካሉት የእንደርታ ገጠር አካባቢዎች በሺዎች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮች መሬታቸው እየተነጠቁ፣ ለከፍተኛ ችግር ሲዳረጉ ለዓመታት መዝለቃቸውን የሚገልፀው ይህ ፓርቲ፥ የዚህ ተቀጥያ የሆነ ተግባር ደግሞ አሁንም ተስፋፍቶ መቀጠሉን በመጥቀስ የክልሉና እና የመቐለ ከተማ አስተዳደር በግልፅ በመሬት ወረራ እና ሕገወጥ የመሬት ማደል ሥራ ላይ መጠመዳቸውን በማንሳት ወቅሷል።

የትንሳኤ ሰብዓ እንደርታ ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አብርሃም ፅጌ "በመቐለ የተሰጠ ሁሉም መሬት በማጭበርበር የተወሰደ፣ ከመሬቱ ለሚነሳ ገበሬ ተገቢ ካሳ ያልተከፈለበት፣ በርካታ አባቶች እና እናቶች አይናቸው እያዩ መሬታቸው በእንቁላል ዋጋ እየተሸጠ ለስደት እና ልመና እየተዳረጉ ያሉበት ሁኔታ ነው ያለው። አሁን እየተናገርን ያለነው፥ የምንተነፍስበት ሁኔታ ተፈጥሮ እንጂ ከዚህ በፊት ይህ ያጋለጡ ወንድሞቻችን የት እንደገቡ አይታወቅም፣ ፀረ ሕዝብ ተብለው መብታቸው ተገፏል" ብለዋል።

የመቐለ ከተማ አስተዳደር በክልሉ ላሉ ለ1028 የጦር ጉዳተኞች በመቐለ ቤት መሥርያ መሬት ለማደል ማቀዱን ከቀናት በፊት ዐሳውቆ የነበረ ሲሆን፥ ትላንት የተሰራጨው የአስተዳደሩ ደብዳቤ እንደሚያሳየው ደግሞ የተያዘው እቅድ ላልተወሰነ ግዜ መራዘሙ አመልክቷል።

https://www.dw.com/am/%E1%88%98%E1%89%9 ... a-70726177