ፋኖ እንደ ታጠቀ በጀግንነት በመዝለቁ የአማራ ክፍለ ሀገራትን ክብር አስጠበቀ። የአዲስ አበባ ህዝብ ክብራቸውን ለሆዳቸው አሳልፈው በሰጡ ዜጎች በመታጨቁ ኦነግ-ኦሮሙማ ሽቅብ ይቀዝንበታል።
Posted: 03 Nov 2024, 11:54
ፋኖ እንደ ታጠቀ በጀግንነት በመዝለቁ የአማራ ክፍለ ሀገራትን ክብር አስጠበቀ። የአዲስ አበባ ህዝብ ክብራቸውን ለሆዳቸው አሳልፈው በሸጡ ዜጎች በመታጨቁ ኦነግ-ኦሮሙማ ሽቅብ ይቀዝንበታል። ጀግንነት ያላወጣውን ፍርሃት አያወጣውም። ይህ እውነት ነው። አብይ አህመድ አማራ ፍኖ ትጥቅ ፈትቶለት ቢሆን ዛሬ አማራ የሚባለው ክልል እንኳን አይኖርም ነበር። ኦሮሙማ በአማራ ክፍለ ሀገራት ላይ ሽቅብ ይቀዝንበት ነበር። አገው፤ ቅማንት፤ ወዘተ አዳዲስ ጎሳዎች በመፍጠር ያጠፋው ነበር። ፋኖ በመታጠቁ የሚልከውን የኦነግ መንጋ በየጢሻው እንደ ድንች ጠብሶ ሲጥለው የአማራን ክንድ ሲቀምስ አማራን ማንበርከክ አልቻለም- አማራም ከነክብሩ እየተሰዋ ብክብር አለ። በጣም አሳፋሪ ምናልባት እስከ አሁን በአለም ዙሪያ ተሰምቶ በማይታወቅ መልኩ የፍርሃት እና የተንበርካኪነት አልፎ የሆዳምነት አረንቋ ውስጥ ያለው አሁን በመጥፋት ላይ ያለው አዲስ አበባ ነው። አዲስ አበባ በጋጥ (ጉረና) ውስጥ እንዳለ በግ ኦሮሙማ በቡድን በቡድን እያወጣ ይነዳዋል፤ ቤቱን እያፈረሰ አከንባሎ እና ዘንቢል አሸክሞ መንገድ ላይ ይነዳዋል። አያት እና ቅድምያቱ ከሰሩት ቤት እና ከደገበት ሰፈር እንደ በግ እየተነዳ ግር ብሎ ይባረራል፤ ከባሌ፤ወለጋ፤ አሩሲ ወዘተ ኦሮሞ እየመጣ ከእርሱ ትውልድ ሰፈር ይሰፍርበታል። አዲስ አበባ አንድ ሞት ብቻ ሳይሆን ሦስት አራት ሞት እየሞተ የሚኖር ፈሪ ህዝብ ነው። ፍርሃት መለኪያ ከጠፋበት መለካት ያለበት በአዲስ አበባ ህዝብ ነው። አዲስ አበባ ህዝብ የፍርሃት መለኪያ ሪኬት ስኬል (Richet Scale) ነው::