Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

የሰዉ ጎሳዎች ፉክክር ችግርን መለስ ዜናዊ በኣንድ ቀን ኢትዮጵያ ዉስጥ ማስቆም ኣይችልም ነበር?

You may select 1 option

3
100%
0
No votes
0
No votes
 
Total votes: 3
 

Naga Tuma
Member+
Posts: 6848
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

የሰዉ ጎሳዎች ፉክክር ችግርን መለስ ዜናዊ በኣንድ ቀን ኢትዮጵያ ዉስጥ ማስቆም ኣይችልም ነበር?

Post by Naga Tuma » 31 Oct 2024, 14:35

የፌዴራል መንግስት ባለስልጣን የሆነ ቀን ሃገር ዉስጥ የጎሳዎች ፉክክር ላይ መሳተፍ ኣድሎኣዊ ስለሚሆን ከዛሬ በኋላ ለፌዴራል መንግስት መዋቅር ብቻ ነዉ የምሰራዉ የሚል አጭር መግለጫ ኣሰምቶ የሰዉ ጎሳዎች ፉክክር ችግርን መቅረፍ ወይም ማስቀረት ኣይችልም ነበር?

Abere
Senior Member
Posts: 14835
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የሰዉ ጎሳዎች ፉክክር ችግርን መለስ ዜናዊ በኣንድ ቀን ኢትዮጵያ ዉስጥ ማስቆም ኣይችልም ነበር?

Post by Abere » 31 Oct 2024, 15:09

ጎሳ የሚለው ስያሜ እኮ ለሰው ልጅ ብቻ የሚሰራ ነው። ስለዚህ የሰው ጎሳዎች የሚል አባባል ሌሎች እንሰሳዎች ጎሳ አላቸው የሚያስብል ነው። ጎሳ ባህላዊ እንጅ ተፈጥሮአዊ አይደለም። ለእሰሳዎች ለምሳሌ የዝንጀሮ መንጋ፤ የአንበሳ መንጋ (lion pride)፤ የዝሆን መንጋ ይባላል። የሰው መንጋ የሚባል ስያሜ አልሰማሁም እስከ አሁን፡ ምናልባት ግብታዊ ስብስብ ወይም (ክራውድ ካልሆነ):: የጎሳ ፉክክር በሚል አስበን ወደ ጉዳዩ ስንመለስ፤ በኢትዮጵያ መሰረታዊ የጎሳ ቃራኔ የለም። የነበረው የመደብ ቅራኔ ነው። ህዝብ የስልጣን ምንጭ ሁኖ አያውቅም እስከ አሁን ድረስ የኢትዮጵያ ህዝብ የስልጣን ምንጭ የመሆን ዕድል አላገኘም። ግለሰብ ወይም ቡድን ( ወያኔ፤ኦነግ፤ደርግ) ወዘተ እየተባለ ሰፋ ሲል በህዝብ ስም ሲጠብ ደግሞ የአንድ ጎሳ ስም በመያዝ በአገር እና በህዝብ ጊዜ ላይ መቀለድ ነው።
የመጨረሻው አዋጭ መፍትሄ የጎሳ ክልል የሚባል እስር ቤት ማፍረስ፤ የጎሳ ፌደሬሽን የሚባል ከነ አካቴ ማጥፋት ነው። ላይጥምህ ይችላል ግን ይኸ ብቻ ነው ምፍትሄው። ክልል አገርህ ከሆነ እንደት ኢትዮጵያዊ ልትሆን ትችላለህ? ለአንተ ክልል ሌላው እንደት መስዋዕት ሊሆን ይችላል? አንተ ክልሌ ነው፤ ሌላው መኖር፤መመረጥ፤ መስራት አይችልም በምትለው "ክልልህ" ላይ ሌላው መጥቶ የለኡላዊነት ማስከበር በሚል የህይወት መስዋዕት አይከፍልም። አገር የጋራ መሆን አለበት። የፌደራል መንግስት የሚባል እስከ አሁን የለም -ይዞ የሚያስደበድብ ለኦነግ ወይም ለወያኔ የቆመ ወንበደ ነው።

Naga Tuma wrote:
31 Oct 2024, 14:35
የፌዴራል መንግስት ባለስልጣን የሆነ ቀን ሃገር ዉስጥ የጎሳዎች ፉክክር ላይ መሳተፍ ኣድሎኣዊ ስለሚሆን ከዛሬ በኋላ ለፌዴራል መንግስት መዋቅር ብቻ ነዉ የምሰራዉ የሚል አጭር መግለጫ ኣሰምቶ የሰዉ ጎሳዎች ፉክክር ችግርን መቅረፍ ወይም ማስቀረት ኣይችልም ነበር?

Naga Tuma
Member+
Posts: 6848
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: የሰዉ ጎሳዎች ፉክክር ችግርን መለስ ዜናዊ በኣንድ ቀን ኢትዮጵያ ዉስጥ ማስቆም ኣይችልም ነበር?

Post by Naga Tuma » 31 Oct 2024, 18:02

የሰብል ጎሳዎች እንዳሉ ስለማዉቅ ነዉ የሰዉ ጎሳዎች ያልኩኝ።

የክልል አስተዳደር የመለስ ዜናዊ ኦርፋን ነዉ ካልኩኝ ዓመታት ተቆጥረዋል።

ኣዎ ልክ ነህ የነበረዉ የመደብ ቅራኔ ነዉ። ካስተዋልከዉ የጎሳዎች ፉክክር ችግርን ማቆም ወደየት ነዉ የሚወስደዉ?

Post Reply