Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
OBANG
Member
Posts: 770
Joined: 17 May 2013, 21:21

በሁለት አቅጣጫ ወደ ፋኖ ያመራው ወራሪው የምርኮኛው ብርሀኑ ጁላ የመከላከያ አራዊት ሰራዊት ቡድን በአናብስቶቹ እርምጃ ተወሰደበት።

Post by OBANG » 30 Oct 2024, 14:12

በሸዋ ጠቅላይ ግዛት መርሀቤቴ አውራጃ ወደ ሚዳ ወረዳ ተጨማሪ ወራሪ ሀይል ለማስገባት በተደረገው እንቅስቃሴ ዛሬ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:30 እስከ ቀኑ 7:30 ድረስ የሸዋ አናብስቶች የአርበኛ መከታው ሞሞ ልጆች ወራሪውን የጠላት ሀይል ሲያስጨንኩት መዋላቸውን ለኢትዮ 251 ሚዲያ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

በዚህ ድንቅ ኦፕሬሽን የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የአፄ ዳዊት ክፍለ ጦር በፋኖ ሞገስ መስፍን የሚመራው የቀስተ ንህብ ብርጌድ እና በፋኖ መንፈስ ፀጋው የሚመራው የክፍለ ጦሩ ልዩ ተወርዋሪ ጦር ባደረጉት አውደ ውጊያ ጠላት ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳት ደርሶበታል።

መነሻውን አለም ከተማ ያደረገው የወራሪው ሀይል ተጨማሪ ሀይል ወደ ሚዳ ወረዳ ለማስገባት ባደረገው እንቅስቃሴ በአፄ ዳዊት ክፍለ ጦር ልዩ ተወርዋሪ ዘመቻ በንስሮቹ አይን ላይ የወደቀው የጠላት ሀይል ከዋሶ ጨበሬ እስከ ጨለሚት ድረስ ሲገረፍ ውሏል።

በሌላኛው አቅጣጫ የመጣውን የጠላት ሀይል ለመቀበል እና ሽፋን ለመስጠት መነሻውን መራኛ ከተማ ያደረገው የምርኮኛው ብርሀኑ ጁላ ሰራዊት በቀስተ ንህብ ብርጌድ አባላት "በግ ስርጥ" እና በ "ሾላ ሜዳ " አቅጣጫ በክንደ ነበልባሎቹ የደፈጣ ጥቃት ተፈፅሞበታል።

ዛሬ በተካኼደው አውደ ውጊያ በጠላት ሀይል ላይ ከፍተኛ አካላዊ እና ቁሳዊ ጉዳት ሲደርስበት፣ ወራሪው ሀይል ከባድ ቁስለኛውን ወደ ጃሞ ደጎሎ ሆስፒታል የጫነ ሲሆን ፤ ቀላል ቁስለኛውን መራኛ ከተማ በሚገኘው ሆስፒታል ማስገባቱን የውስጥ አርበኞቻችን መረጃውን አድርሰውናል ሲል የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የአፄ ዳዊት ክፍለ ጦር የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አስታውቋል። #MerejaTv