በሃገር ዉስጥ እኩልነት ማለት እና የሃገር ወገን ላይ መነሳት መካካል ጥልቅ ልዩነት ኣለ።
ይህቺን ልዩነት ማስተዋል ጥልቅ ዕዉቀት ወትም የረቀቀ ኣዕምሮ ኣያስፈልግም።
ጀማሪ ወታደር እንኳን ወገን ከተባለ ሌላ ማብራርያ ኣያስፈልገዉም።
የሃገር ዜጋ ወገን ነዉ ከተባለ ሌላ ማብራርያ ኣያስፈልገዉም።
ምስራቅ እና ዩንየን ይህቺን ባለማስተዋል ነዉ ድሮ ፋኖ ለሃገር ይቆማልን ሰምተዉ የሃገራቸዉ ወገን ላይ የተነሱት?
ለዓመታት የሃገር መሠረት የሆኑ እሴቶች ላይ የማሳነስ ዘመቻ ሰነበተ።
የኢትዮጵያ ተዋህዶ ላይ ዘመቻ ነበረ።
የኢትዮጵያ ደብተራዎች ላይ ዘመቻ ነበረ።
የኢርዮጵያ ፊደል ላይ ዘመቻ ነበረ።
የኢርዮጵያ ባህል ላይ ዘመቻ ነበረ።
የዐደዋ መሪ አፄ ምኒልክ ላይ ዘመቻ ነበረ።
በዐደዋ ዋዜማ ኢትዮጵያን ተባብረዉ ባቆሙት ራስ ጎበና ላይ ዘመቻ ነበረ።
ሸዋን ለብቻ የመኮነን ዘመቻ ነበረ።
ሸዋ ዉስጥ ኣዕምሮ ፍጹም ተወልዶ ኣያዉቅም ብለዉ እስከ መሳለቅ ደርሰዉ ነበረ።
በቅርቡ ግንቦቴዎች ባሉት ላይ ዘመቻ ነበረ፣ ሆረስን ፖለትካ ኣታዉቅም እና ከመስኩ ገለል በልልን እስከማለት ደርሰዉ ነበረ።
ኣሁን ደግሞ የኣንድ ግለሰብን ስም ከኣንድ የኢትዮጵያ ጎሳ ጋር በማያያዝ ዘመቻቸዉን ቀጥለዋል።
ጥላሁን የሚሉት ማን ወይም የትኛዉ ግለሰብ እንደሆነ ኣላዉቅም። የሚገርመኝ ኣዲሱ ዘመቻቸዉ በግለሰብ ኣመካኝተዉ የቱለማ ጎሳ ላይ መሆኑ ነዉ።
በደንብ ባላዉቅም እነ ራስ ጎበና፣ አቡነ ጴጥሮስ፣ ራስ አበበ አረጋይ፣ የኢትዮጵያ የፊደል ሰራዊት መሪ፣ የማንዴላ ኣሰልጣኝ እና በኋላ የኦነግን መመስረት ስብሰባ የመራዉ ጄኔራል ታደሰ ብሩ ከዚህ ጎሳ የወጡ ይመስለኛል።
የሚወቅሱት ግለሰብ ወይም የምወቀስበት ምክንያት ይህ ነዉ ማለት ኣልችልም። ስለማላዉቅ። ኮሌጅ እያለሁ ለተማሪ መብት መከራከሬ ማንዴላ ብያስብለኝም በዉል ስለማላዉቀዉ ግለሰብ ወይም ምክንያት ልከራከር ለማለት ኣይዴለም።
የእኔ አጭር ጥያቄ ይህ ሁሉ የኢትዮጵያ እሴቶች ላይ ዘመቻ ብልህነት ነዉ ወይስ ማስተዋል የምያዳግት ጅልነት ነዉ?
ይህ ኢትዮጵያን ተባብሮ ያቆመ፣ ከማንም ያላነሰ የቆመላት፣ የተሰዋላት የኢትዮጵያ ጎሳ ግለሰብን ምክንያት በማድረግ በሃገሩ ዉስጥ ለመቅበር ይህን ያህል መጣር ምንድነዉ?
መልሶ መላልሶ መምከር በጣም ይሰለቻል። ዐመል ያለበት እኩልነት ስትላዉ አናታችሁ ላይ ካልሸናሁ ይላል።