አንድ ጊዜ በኳታር የእግር ኳስ የአለም ዋንጫን አስመልክቶ ስለ ጀርመን ተጫዋቾች አንድ ሰዉ የሆነ ቦታ ላይ የፃፈዉ ትዝ አለኝ።
የጀርመን ተጫዋቾች ኳታር ሄዱ ና ገና ጨዋታዉን በቅጡ ከመጀመራቸዉ አስቀድሞ ስለ ሆሞ ጉዳይ ፕሮቴስት ማድረግ ጀመሩ፣ የሰማቸዉ ያለ አይመስለኝም። ዳሩ ግን ተጫዋቾቹ ጨዋታዉንም ተቀዉሞንም እንቀጥላለን ብሎ ተስፋ አድርጎ ነበር፣ በነበር ቀረ ና በመጀመሪያዉ ዙር ወደ አገራቸዉ ተሸኙ እንጂ። ይህን የተዘበ ሰዉ ደግሞ፣ አስተያየቱን አከለበት ና፣ "በሉ አሁን ሂዱና በደምብ ፕሮቴስት አድርጉ እንግዲህ" ብሎ በመልዕክቱ አፌዘባቸዉ።
ክብርቷም አሁን ሄዶ ፋንዶቻቸዉን ይቀላቀሉ ና ዝምታቸዉን በደምብ ያቃዉጡት እንላለን እኛም በበኩላችን።
ይመቾት፣ የቀድሞዋ ክብርት ፕሬዝዳንት!
Please wait, video is loading...