Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Educator
Member
Posts: 2370
Joined: 03 Jun 2021, 00:14

To DDT and PP demods

Post by Educator » 07 Oct 2024, 08:33

አብይ ፦"ኢሱ፣ኢሱ" ሲል - "በኤርትራ ፍቅር- ተቃጠልን" ሲሉን የነበሩ ካድሬዎች፤አለቃቸው ከኤርትራ ጋር የተኳረፈ ሲመስላቸው፤ ፍሬቻ ሳያሳዩ ከመቅጽበት ታጥፈው ኤርትራን ሲራገሙ ሰንብተዋል።
ዛሬም፦"ክብርት ፕሬዚዳንታችን"እያሉ ሲያቆላምጧቸውና ሲጎነበሱላቸው የከረሙት ሳህለወርቅ ዘውዴ ሥርዓቱን ሜዳ ላይ ሲያሰጡት ከመቅጽበት ፍሬቻ ሳያሳዩ ታጥፈው ፦"እንዴት አጉራሻችንን ብልጽግናን አሳጡብን?"ብለው ይዘልፏቸው ጀምረዋል።

"ያንን ገለባ ልብ ከደጅ የወደቀው፣

አድራሻህ ወዴት ነው ብለህ አትጠይቀው፣

የነገው ነፋስ ነው መንገዱን የሚያውቀው።" በውቄ

ጋዜጠኛ፦ ወዴት እየሄድክ ነው?

ካድሬ፦ ወደ ነፋሱ አቅጣጫ።

Educator
Member
Posts: 2370
Joined: 03 Jun 2021, 00:14

Re: To DDT and PP demods

Post by Educator » 07 Oct 2024, 08:36

አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ በእጩነት ቀረቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው፡፡

በዚህም የፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ የሥራ ጊዜ መጠናቀቁን ተከትሎ አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ በእጩነት ቀርበዋል፡፡

አምባሳደር ታዬ በአሁኑ ወቅት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት በማገልገል ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡

Educator
Member
Posts: 2370
Joined: 03 Jun 2021, 00:14

Re: To DDT and PP demods

Post by Educator » 07 Oct 2024, 08:53


Post Reply