Page 1 of 1

ሰካራሟ አዲስ አበባ! አፍርሳ ትሠራለች፤ ሰርታ ታፈርሣለች።ለነገሩስ ሰካራም ቤት አይሰራም ይባላል እኮ። እስክንድር ነጋ የረገማት አዲስ አበባ ገና ትፈርሳለች፤ አፍርሳ የሰራችውም ይፈርሳል።

Posted: 05 Oct 2024, 08:46
by Abere
ሰካራሟ አዲስ አበባ! አፍርሳ ትሠራለች፤ ሰርታ ታፈርሣለች።ለነገሩስ ሰካራም ቤት አይሰራም ይባላል እኮ። እስክንድር ነጋ የረገማት አዲስ አበባ ገና ትፈርሳለች፤ አፍርሳ የሰራችውም ይፈርሳል።በሰከነ አእምሮ የተደረገ ሁሉ እየሮጡ የታጠቁት ሲሸሹ(ሲሮጡ) ይፈታል ስለሆነ። አዲስ አበባ ከተቆረቆረች ስንት አመት ሆናት ቢባል መልሱ ሁልግዜ ገና ዕድሜዋ እንደ ህጻን ዜሮ ነው ምክንያቱም የዕድሜ መገለጫ አሻራዎቿ ዘወትር እየሰከረች በዕብደት ፍርስርሱን ስለምታወጣው። የእብድ እራስ ቅቤ (አሙካ ) አይዝም ይባላል - አድስ አበባን የማይችለውን የእግር ኳስ እያሳየኸው ብትገርፈው ወይም ጭብጦውን ብትቀማው ሙት ድንዝዝ ነው።

መጀመሪያ ቀይ፤ቢጫ አረንጓዴ ሰንደቅ አላማ ታስይዝ እና እንባውን እያፈሰሰ ታስጨፍረዋለህ። ከዚያም በቃህ ልብህ እስኪ ወልቅ ጨፍረህበታል፤ አሁን ባዶ እጅህን ወጥተህ የመጨፈር ብልግና ኦሮሙማ መሆን ትችላለህ - ጥቁር እና ቀይ ነጨ በላው የአባገዳይ አርማ መያዝ ያቻላል ሲሉት አሜን ይላል። ቀሚስ፤ ጋቢ፤ነጠላ ከበሮ ላይ ጽናጽን ላይ አረንጓ ቀይ ቢጫ ሳይታሰብ ከተገኜ ና! ቁም እነኝህ ቀለማት ተቦጭቀው እስኪ ቀደዱ ይባላል - እሽ ኦሮሙማ ጎፍታ ይላል ሰካራም ድንዝዝ አዲስ አበባ። ቀጥሎም አዲስ አበቤ አይደላችሁም የአዲስ አበባ አሻራ ይፈርሳል - ይህም እሽ ነው። በሰፈር በሰፈር ሶርያ አሌፓ ከተማ ይሆናል - አሁንም እሺ። ያደግህበት ሰፈር አንዳች ምልክት የልጅነት ትውስታ እንዳይኖረው ሁኖ ይፈራርሳል ተነስ ፊሽካ ተነፋ! እሽ ጎፍታ ኦሮሙማ። ቀጥሎ ደግሞ ለእሬቻ ባህር ውስጥ ትጣላለህ ቢሉት እሽ! ቆሪጥ ጎፍታ ነው። እስክንደር ነጋ ወንድ አይጣብሽ ብሎ የረገማት አዲስ አበባ ዕብደት እባ ሰካራምነት መሄጃ መዳረሻዋ የጠፋት የፈሪዎች ሰው ሰራሽ አሌፓ።

ሰው እንጅ ከተማ የድንጋይ የጡብ ክምር መቸ ከተማ ይሆናል። ጡቡ የእንቧይ ካብ ነው በእብደት በድንገት የሚከመር መልሶ የሚፈርስ።