ዕድገት ከመሰለህ
Posted: 01 Oct 2024, 20:28
ዕድገት ከመሰለህ፦
ሀገር ጫፍ እስክ ጫፍ ተጠብሳ በማዳት፣
አራት ኪሎ አጠገብ ብሽክሊሊት መንዳት፣
ዕድገት ከመሰለህ፦
መሰረትህ ፈርሶ ወደ ሽቅብ መዝለል፣
ሰው እያፈረሱ ድንጋይን መቆለል፣
ዕድገት ከመሰለህ፦
ቤትን አጨልሞ አደባባይ ማፍካት፣
ሞሰበ ሲሚንቶን በለሚ መተካት.....
ከሁለቱ በአንዱ ዕይታህ ተምታቷል፦
ወይ ቡለንህ ላልቷል ፤ወይም ሆድህ ሰፍቷል። (ደረጀ ሀ.)
ሀገር ጫፍ እስክ ጫፍ ተጠብሳ በማዳት፣
አራት ኪሎ አጠገብ ብሽክሊሊት መንዳት፣
ዕድገት ከመሰለህ፦
መሰረትህ ፈርሶ ወደ ሽቅብ መዝለል፣
ሰው እያፈረሱ ድንጋይን መቆለል፣
ዕድገት ከመሰለህ፦
ቤትን አጨልሞ አደባባይ ማፍካት፣
ሞሰበ ሲሚንቶን በለሚ መተካት.....
ከሁለቱ በአንዱ ዕይታህ ተምታቷል፦
ወይ ቡለንህ ላልቷል ፤ወይም ሆድህ ሰፍቷል። (ደረጀ ሀ.)