Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 8598
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

በድረስ ሰሃሉ የሚመራው የብአዴን ክንፍ እጅ ወደላይ ተብሏል!!

Post by Wedi » 29 Sep 2024, 17:49

በድረስ ሰሃሉ የሚመራው የብአዴን ክንፍ እጅ ወደላይ ተብሏል!!
*********
በብአዴን ቤት ሁለት አይነት ብአዴን ነበረ፣ አለም። ይሄም የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ የብአዴን ክንፍ (በአህመዲን አህመድ የሚመራ) እና ሌላኛው የብአዴን ክንፍ (ይህ የሚመመራው በድረስ ሳህሉ ነው) እነዚህ አካላት ለረጅም ጊዜ ለመገዳደል ሲደባቡ የነበሩ ናቸው።

አህመዲን አህመድ የድረስ ሳህሉ ቡድን ይገለኛል በሚል ወደ ባህር ዳር አልሄድም ብሎ በአዲስ አበባ፣ በሸዋ (ጌትቫ ሆቴል) እና ደሴ ተወስኖ የተለያዩ ሴራዎችን ሲጎነጉን ከርሞ በዛሬው እለት ከአብይ አህመድ፣ ከሽምልስ አብዴሳ እና ከሬድዋን ሁሴን ጋር በመሆን በዋነኝነት በአህመዲን ፊታውራሪነት የአማራ ተወላጅ የሆነውን የብአዴን ክንፍ በመለቃቀም ወደ እስር ቤት እያጋዘው ይገኛል።

የኦህዴዱ ታማኝ ሰው አህመዲን አህመድ በታሰሩት ምትክ አመራሮች ከከሚሴና ከወሎ ለኦህዴድ ታማኝ የሆኑና ለአስር ወር ያህል ሲሰለጥኑ የነበሩ አመራሮችን እንደሚተካ ለማወቅ ተችሏል።

ግራም ነፈሰ ቀኝ ብአዴን ዳግም እግር የሚተክልበት እድል የለውም፣ ፋኖም ይሄን መከፋፈልና ትርምስ ተጠቅሞ ብአዴንን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከአማራ ሕዝብ ጫንቃ ላይ ለማውረድ በጋራ መስራት አለበት!
ድል ለአማራ ሕዝብ!

#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
ድል ለሰፊው ህዝብ ለአምሓራ ‼️
አፍቃሪው የድሃ ልጅ እንደከተበው

Please wait, video is loading...