ከራስ በላይ የሕይወት ዘመን ታጋይ የአማራ ፋኖ ራስ፤ አርበኛ ደረጀ በላይ (አባ ናደው)‼️‼️
Posted: 27 Sep 2024, 13:56
ከአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት አማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ዘምቻ መምሪያ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ ..

ከራስ በላይ የሕይወት ዘመን ታጋይ
የአማራ ፋኖ ራስ፤ አርበኛ ደረጀ በላይ (አባ ናደው)
በተመለከተ የተሰጠ የክብር መግለጫ!
የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ በታሪኩ የመጀመሪያ የሆነውን ይህን የክብር መግለጫ ሲያወጣ ዋና ዓላማው ለትግሉ እየተከፈለ ያለውን ዋጋ፣ ወዳጅ እና ጠላቶቻችን እንዲውቁት አይደለም፡፡ የትግሉ ባለቤት መላው የአማራ ሕዝብ የሚከፈለውን ዋጋ ያውቀዋል፤ የአማራ እውነተኛ ወዳጆችም ይረዱታል፡፡ ጠላቶቻችን ትርጉሙ ባይገባቸውም የቆራጥነታችንን መጠን የሚቀኑበት ፀጋችን ነው፡፡ ይልቁንም እንደወርቅ በእሳት ተፈትነው ነጥረው የወጡ የትግል መሪዎቻችንን፡- መላ ሰራዊታችንና የትግሉ ባለቤት የሆነው የአማራ ሕዝብ ሁሌም እንደሚያከብራቸው፣ በየትኛውም ጊዜና ሁኔታ ውስጥ በፅናት አብሯቸው እንደሚጓዝ ዳግም ለማረጋገጥ ነው፡፡
በተዋረድ ለታሪክ ፀሐፍትና የትግሉ አጥኝዎች ከራስ በላይ ለሕዝብ የተኖረ አርበኝነት ጠባይና ግብሩ ምን እንደሚመስል ቀረብ ብለው እንዲያጠኑት፣ እጅግ በጥቂቱ ጓዳዊ ምስክርነት ከፈረሱ አፍ ማሰማት የጊዜው እውነት በመሆኑ ነው!!
ይህ የክብር መግለጫ የሕዝባዊ ትግል ዓላማ፣ የመርህ ሰው፤ አርበኝነትን በተግባር እየኖረ ያለ የዘመናችን ‹የፈለገ-ቴዎድሮስ ምልክት› ለሆነው የአማራ ፋኖ ራስ አርበኛ ደረጀ በላይ ነው፡፡
ይህ በአማራ ፋኖ ትግል ታሪክ ውስጥ ከፍ ብሎ የሚቀመጥ፡- መሪ አርበኛችን እና መላ ቤተሰቡ ለአማራ ሕዝብ ነጻነት ለከፈሉት እና እየከፈሉት ላለው ውድ ዋጋ የተሰጠ የላቀ ክብር መግለጫ ነው፡፡
እናመሰግናለን መሪያችን!!
የሩቅ፣ የመካከለኛው እና የቅርብ ዘመን ታላላቅ የኢትዮጵያ ታሪክ ሁነቶችን ባስተናገደው የጎንደር ደምቢያ መስክ፡- ኃያል ነገሥታት፣ የረቀቁ ሊቃውንት፣ የጦርና የሕይወት ጥበበኞች ፈልቀዋል፡፡ የአምደ ፂዩን ቀስት መልሶ የተነሳው፣ የገላውዲዩስ ልዩ ድል የተቆጠረው፣ የሰርፀ ድንግል ጋሻ የሰፋው፤ ዓለም ሰገድ… ነገሥታት የነገሡባት፣ ምስጢራቸውን ያከማቹባት፣ በመይሣው ካሣ ክንድ የዘመነ መሳፍንት የመጀመሪያው አከርካሪ የተሰበረው በጎንደር ደምቢያ መስክ ላይ ነው፡፡
በዚህ መስክ አያሌ ጀግኖች ተነስተው ታሪክ ሰርተዋል፤ ዛሬም የማይሞት ታሪክ መስራታቸውን ቀጥለዋል፡፡ አርበኛ ደረጃ በላይ (አባ ናደው) የፈለቀው ከጣና እግር ስር በዚህ ምድር ነው፡፡ ዓመቱን ሙሉ ማምረት፤ ዓመቱን ሙሉ መዋጋትን እኩል የሚያውቀው አርበኛችን የተንጣለለ የመስኖ ልማት ባለቤት፣ ቆላ መዘጋ አራሽ አንደፋራሽነቱ የተመሰከረለት ነው፡፡
አርበኛችን፡- ፊት ለፊት በጀግንነት መግጠምን ከአጤ ቴዎድሮስ፤ የማረከውን ሰራዊት ቁስል የማጠብን ርኅራኄን ከእምዬ ምኒልክ፤ ሕዝባዊነት ላለው ለትግል ዓላማ በልጅ መወሰንን የሚያህል ከባድ ውሳኔ የተጋፈጠው ከደጀዝማች በላይ ዘለቀ ታሪክ ነው፡፡ መሪያችን የአባቶቹ ዓላማ ወራሽ ነው። ጭልጥ ባለው የደምቢያ መስክ እንደንጉሥ ሚካኤል ተወርዋሪ አዋጊ፣ ወደኋላ የማያውቅ ከፊት ተሰላፊ የውጊያ መሐንዲስ ነው!!
እናመሰግናለን መሪያችን!!
አማራን ከወያኔ ወረራ ለመከላከል በወሎ፣ ሸዋና ጎንደር የነበሩ ዘመቻዎችን በግንባር የመራው አርበኛ ደረጃ በላይ በ2008 የነበረው የትግል ሚናው ሳይዘነጋ፣ ያለምንም እረፍት ያለፉት አምስት ዓመታትን በውጊያ ሜዳ ላይ ነው፡፡ ለአማራ ሕዝብ ሕልውና ወደትግል ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የቆላ መዘጋ እርሻውን ተነጥቆ፣ ዘመናዊ ቤቱ በሞርታር ወድሞ፣ ከብት ንብረቱ፣ መኪና ሆቴሉ በጠላት ብአዴን-ብልጽግና ተዘርፏል፡፡ አባ ናደው ግን "ሀብቴ አማራ ነው" በሚል ለአማራ ነጻነት ከነ መላ ቤተሰቡ ውድ ዋጋ እየከፈለ ዛሬም እንደፈነነ አለ።
እናመሰግናለን መሪያችን!!
መስዋዕትነት መክፈል በትግሉ ውስጥ የነበረ፣ ያለና የሚቀጥል ነው። በዚህ በርካታ የሰራዊታችን መሪዎች፣ ተዋጊዎች ከነቤተሰባቸው ዋጋ ከፍለዋል እየከፈሉም ነው፡፡ የአርበኛ ደረጀን የተለየ የሚያደርገው… አንድም ሳይሰስት ሁሉ ነገሩን ለአማራ ኀልውና ትግል የሰጠ መሆኑ ነው። ቤተሰብ፣ ሀብት፣ ንብረቱን ያለአንዳች ስስት ለአማራ ሕዝብ ነጻነት ገብሯል፡፡
ቀዳሚው ሰማዕት ፋኖ አማኑኤል ደረጀ፡- ዕድሜ 24፣ የተሰዋበት ቀንና ቦታ ሚያዝያ 15/2016 ዓ.ም. ደንቢያ ጉራምባ ሚካኤል ልዩ ቦታው "መገጭ አፋፍ" ላይ በጀግንነት ተሰውቷል፡፡ ሁለተኛው ሰማዕት ፋኖ ዋሲሁን ደረጀ፡- ዕድሜ 30 የቆሰለበት ቀንና ቦታ መስከረም 5 ደንቢያ ‹ሳንኪሳ› ልዩ ቦታው "ቆንገር" ሲሆን፤ የተሰዋው ደግሞ ከሁለት ቀናት በኀላ መስከረም 7/2017 ዓ.ም. ነበር፡፡
እኒህ ጀግኖች ከፀረ-ወያኔ ወረራ ጀምሮ በበርካታ አውደ ውጊያዎች ተሰልፈው ትልልቅ ጀብዱዎችን እንደአባታቸው ሰርተዋል፡፡
ከዕድሜቸው ቁጥር በላይ አውደ ውጊያዎችን በድል መርተዋል፡፡ በርግጥ መሪያችን በዚህ ትግል የከፈለው ዋጋ ከቃላት በላይ ነው፡፡ ከእነኝህ የማይሞት ታሪክ ባለቤት ከሆኑ ጀግኖች በተጨማሪ በርካታ የቅርብ ቤተሰቦቹ ለአማራ ሕዝብ ነጻነት የማይተካ የሕይወት ዋጋ ከፍለውልናል!!
እናመሰግናለን መሪያችን!! እናመሰግናለን ጀግኖቻችን!!
ጎንደር ደምቢያ ምድር ያለእረፍት ውጊያ የቀጠለው በዕዛችን የዘመቻ መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ደረጀ በላይ ቆራጥ አመራር፤ በትግል ወንድሞች የውጊያ ቅንጅት፤ በሕዝባችን ጥንካሬ ነው!!
ከአዕምሮ በላይ የጀብድና የውጊያ ጥበብ ባለቤት የሆነው አርበኛችን ለከፈልክልንና እየከፈልክልን ላለው ውድ ዋጋ ባለዕዳዎችህ ነን። ታሪክ አዋቂው አማራ ሁሉንም እየመዘገበ ነው።
ከራስ በላይ የሕይወት ዘመን ታጋይ አርበኛ ደረጀ በላይ፡-
መሪ ነው፡- ከነመላ ቤተሰቡ ለአማራ ሕዝብ ነጻነት ትግል ሜዳ ቀድሞ የወረደ፡፡ ባለ ራዕይ ነው ሩቅ ዓላሚ፡፡ ቆራጥ ነው፤ የውሳኔ ባለቤት፡፡ ከግለሰብ ሩጫ ይልቅ ለተቋማዊ ትግል የታመነ፤ ለጋራ ድል የቆመ፤ ለሕዝብ ነጻነት የመነነ የትግል መሪያችን ነው!!
አባት ነው፡- ጀግኖችን የወለደ፤ ጀግኖችን ያሳዳገ፤ በትግል ሜዳ ጀግና ፈጣሪ፤ ጀግና አክባሪ ነው፡፡ ሰራዊቱን በትህትና፣ ትግሉን በጥበብ የሚመራ፤ በዕዝ፣ በክፍለ ጦሮች፣ በየ አሀዱ ቅራኔዎች ሳይውሉ ሳያድሩ በትኩሱ የሚሽር፣ አስታራቂ ዳኛ የትግሉ አባት ነው!!
ለጋስ ነው፡- ለአማራ ሕዝብ ሕልውና ትግል ቤት ንብረቱን ያጣ፤ ትላንት በገንዘቡ ገዝቶ ያስታጠቀ፣ ዛሬ ማርኮ ሸላሚ ነው! በትግሉ አባ ናደውን አምኖ የተከተለ ወጣት ሁሉ ታጥቋል፤ ትጥቁ የብረት ብቻ ሳይሆን የአማራነት ጭምር ነው። አማራዊ የውጊያ ሥነ-ልቦና ከብረት ጋር የሚያስታጥቅ፤ ደሙንም ሀብቱምን የሚሰጥ ለጋስ ነው!!
አዋጊ ነው፡- በውስን የሰው ኃይል የመሬት እርባና (ገጽታ) ተጠቅሞ ጠላትን የእንብርክክ የሚነዳ፤ በምርኮ ናዳ ወገንን በድል ቁንጣን የሚያጨናንቅ! ለጠላት እሳት፤ ለወዳጅ ድል አጉራሽ ነው፡፡
ዘመቻ ማቀድ፣ መከወን፣ መገምገም፣ ማረም፣… መክሊቱ የሆነለት የድል መሪያችን አባ ናደው ለከተማ ውጊያ ‹ሰርጂካል ኦፕሬሽን› የውጊያ ዕቅድ በማውጣት የሚመራ፣ የዐቢይ አሕመድ የግል ጀኔራሎችን እንቅልፍ የነሳ፣ የብልፅግናን አራዊት ሰራዊት አሰልፎ የነዳ የውጊያ ፈላስፋ ነው
ይህ የሕይወት ዘመን ታጋይ መሪ አርበኛችን የፋኖ ራስ፡- ሙስሊም ክርስቲያን አክባሪ የትግልም የሞራልም አባት ነው፡፡ ለከፈለው ዋጋ ካህን ሼኹ የሚፀልይለት፣ እናቶች የሚሳሱለት፣ አባቶች በምክር ያልተለዩት፣ ወጣቶች የሚከተሉት፣ እረኞች የሚቀኙለት፣ … ከራስ በላይ ለሕዝብ የኖረ የሕይወት ዘመን ታጋይ ነው፡፡
የአማራ ፋኖ ራስ፣ አርበኛ ደረጀ በላይ እኛ አማራዎች ለከፈልክልን ውድ ዋጋ ሁሉ ከፍለነው የማንዘልቀው ባለዕዳዎችህ ነን። አንተ የአማራ ትግል ቀንዲል፤ የአማራ የብረት አጥር፤ የዕዛችን ኩራት ነህ፤ መሪያችን ነህና እስከ ቀራኒዩ እንከተልሃለን!!
በሞት ሸለቆ ሳይታለፍ ታሪክ መቀየር እንደማይቻል ቤዛ ሆነው ያሳዩን ወንድሞቻችን ሁሌም በልባችን ይኖራሉ፡፡ የወንድሞቻችን መስዋዕትነት የአማራን የህልውና ትግል ለዘላቂ ድል ለማብቃት የአብዮቱን ባቡር ያፈጥነዋል እንጅ ከቶውንም አያዘገየውም፡፡ የታጋዮቻችን ሰማዕትነት በአማራ ፋኖ ዘንድ ከፍተኛ የትግል መነሳሳት፣ እልህና ቁጭት በመፍጠር የአገዛዙን ሥርዓተ ቀብር አይቀሬ ያደርገዋል፡፡
አርበኛ ደረጀ በላይ (አባ ናደው) ይህን ሁሉ ዋጋ የከፈልከው ለአማራ ህልውና በመሆኑ በትውልዱ ልብ ውስጥ በታሪክ ስትዘከር ትኖራለህ!! በትግሉ ሜዳ የፀናህ ነህና ባንተ መሪነት በሚሊዮን ልጆችህ ታጋይነት የአማራ ሕዝብ ነጻነት ይረጋገጣል!!
እናመሰግናለን መሪያችን!! እናመሰግናለን ጀግኖቻችን!!
ከአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት
የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ዋና አዛዥ
አርበኛ ሀብቴ ወልዴ
ጎንደር፣ አማራ፣ ኢትዮጵያ
መስከረም 14/2017 ዓ.ም.