Page 1 of 1

"በአብይ ጭምብሎች ትግራይ አትደፈርም..." ዶር ደብርጽዮን ገብረሚካኤል!!

Posted: 21 Sep 2024, 03:33
by Wedi
"በአብይ ጭምብሎች ትግራይ አትደፈርም..."
_______________________________
እነ ኣይተ ጌታቸው የሰኔ ዶሮ መሆንን ለምን መረጡ❓️

(ቅድመ ማስታወሻ፦ ይህ ፅሑፍ የአንድን ወገን አቋም በመደገፍ የተፃፈ ነው❗️)

ኣይተ ጌታቸውና ቡድኑ በሃሳብ ተለይቶም ቢሆን ራሱን ችሎ የቆመ ቢሆን ኖሮ እኮ ችግር አልነበረውም። ግን የትግራይን ህዝብ በጅምላ ከጨፈጨፈው ከአብይ አህመድ አምባገነን መንግሥት ጋር ተዳብሎ (ተለጥፎ) ነው ሌሎቹን አንንበረከክም ያሉትን ጓዶቹን ለማስወገድና ለማስመታት የቆመው።

ኣይተ ጌታቸው ያላወቀው አንድ ነገር፣ አረመኔው አብይ አህመድ ጠንካራ አቋም ያላቸውን የህወኀት ሰዎች (እነ ዶክተር ደብረፅዮንን) በእነ ኣይተ ጌታቸው አማካይነት ካስወገደ በኋላ፣ ትግራይን በእጁ አስገብቶ መጫወቻ ነው የሚያደርጋት።

አብይ አህመድ በእነ ኣይተ ጌታቸው በኩል ተጠቅሞ ህወኀትን የማንበርከክና ከጨዋታ ውጪ የማድረግ ዓላማው ከተሳካለት፣ በአማራና በኦሮሚያ የተተከሉት ዓይነት የምስለኔ (አሻንጉሊት) አስተዳደሮች ናቸው በትግራይም የሚተከሉት። ከዚያ በኋላ "ዝም ብለሽ ተቀበይ፣ የሰጡሽን ብቻ" ይሆናል ጨዋታው ሁሉ።

አብይ አህመድ በትግራይ ውስጥ፣ የውስጥ ባንዳ ካላገኘ በስተቀር ግን ይህንን ማድረግ የሚችልበት መንገድ የለውም። በትግራይ ሕዝብ ምርጫና ፍላጎት መሐል ገብቶ መፈትፈትና ነገር ማቡካት፣ እርስበርስ ማጋጨትና ማተራመስ አይችልም።

አውቆም ይሁን ሳያውቅ፣ የእነ ኣይተ ጌታቸው ቡድን ለአብይ አህመድ የሰጠው ዕድል ይሄንን የትግራይን ሕዝብ በራሱ ሰዎች በኩል ተከልሎ ገብቶ ከውስጡ የማተራመስ ዕድልን ነው።
ከይቅርታ ጋር፣ ባጭሩ፣ የእነ ኣይተ ጌቾ... ቡድን፣ የአብይ አህመድ መሸፈኛ ጭምብል (ኮንዶም) ሆኖ የትግራይ ሕዝብ በደሙና በከፍተኛ መስዋዕትነት ያገኘውን ነፃነቱን ለማስደፈር እያገለገለ ነው።
የህወኀት ሰዎች ይሄንን በጊዜያዊ አስተዳደር ስም የተጠለለና፣ ራሱን የአብይ አረመኔ መንግሥት ተላላኪ ያደረገ ቡድን፣ አደብ ግዛ ብለው መክረው፣ ለምነው፣ አግባብተው ሲያቅታቸው፣ የቀራቸው አማራጭ ምንድነው?

ወይ በሠላም ከድርጅታቸው ማባረር ነው። አሊያ ደሞ እንደ ማንኛውም ባንዳ ሌላ ከፍ ያለ አደጋ ሳይጋብዝ የሚወገድበትን መላ መፈለግ ነው። የእነ ደብረፅዮን ውሳኔ ሠላማዊውን መንገድ የመረጠ ነው። ተላላኪዎቹን ከድርጅቱ ማባረር፣ እና ከፈለጉ የራሳቸውን ድርጅት እንዲመሠርቱ መተው ነው። ተገቢና የተጤነ ውሳኔም ነው።

አሁን የአብይ ጭምብሎች የሚቀራቸው ነገር፣ የራሳቸውን ተቃዋሚ ወይም ተቀናቃኝ ድርጅት፣ በራሳቸው አዲስ መጠሪያ ስም መመሥረት ብቻ ይሆናል። እንጂ በህወኀውስጥ ገብተው ሕዝብ የሚያምሱበት ዕድል አይኖራቸውም።

በመሠረቱ የገዛ ህዝባቸው ጉባዔ ተሰብስቦ፣ ኑ እንነጋገር ሲላቸው፣ የአብይ ቡራኬ ካልተሰጠን አሻፈረኝ ያሉ ምስለኔዎች፣ ከገዛ ህዝባቸው ይልቅ ህዝባቸውን በመቶ ሺህዎች የጨፈጨፈውን ፋሺስት ማክበርን የመረጡ ሰዎች፣ እንዴት ለነፃነቱ አልንበረከክም ብሎ ከሕዝቡ ጋር ደሙን ያፈሰሰ ድርጅት መሪዎች ሊሆኑ ይችላሉ?

ፈሪዎች፣ ተጣጣፊዎች፣ ተንበርካኪዎችና ከሃዲዎችስ እንዴት የጀግና ሕዝብ መሪ ሆነው መዝለቅ ይቻላቸዋል? አይመስለኝም። አይችሉም። የሞራል ኃይላቸውን አጥተዋል።

ህሊናቸውን ለጥቅም ሸጠው፣ ሌሎችንም ይመጣብናል ያሉትን መከራ እያሳዩ ወደእነርሱ የተንበርካኪነት መንገድ ሊመሩ የሚፈልጉ ናቸው። የመሪነትና የጀግንነት ክብር ጎድሏቸዋል። ሕዝባቸውን አላከበሩም።
በበኩሌ በግሌ የህወኀቶች ፖለቲካ ደጋፊ ባልሆንም፣ ነገር ግን ማንም ሰው ቢሆን፣ አምስት ሆነው አምስት መቶ ሺህ ሠራዊት ያለውን አምባገነን መንግሥት የገረሰሱት የህወኀት ታጋዮች ከመጠን ያለፈ ጀግንነትና ቁርጠኝነት ማንኛውንም የሰው ልጅ ሊያስደንቅ የሚገባ ይመስለኛል።

ብዙ የዓለማችን ሰዎችኮ ከአሜሪካና ከአውሮፓ ታሪክ እየፈለፈሉ፣ የጀግንነት መንፈስን ለመበደር ይታትራሉ። ከዚሁ ከቅርባችን ያለው፣ የእነዚያ ቆራጥ ሰዎች ተራራን የሚያህል የገዘፈ ልብ፣ ለማንም ለሚሰማሰው የጀግንነትን መንፈስ የሚያበድር ነው።

የእነ ኣይተ ጌታቸውን ነገረሥራ ሳየው፣ በዚያ ተራራ የሚያህል የሕዝባቸው ጀግንነት ሥር ባዳ ሆነው የቆሙ ትናንሽዬ ዶሮዎች መስለው ይታዩኛል አንዳንዴ። ዶሮዎች ያልኳቸው የልባቸውን አናሳነት በማሰብ ብቻ አይደለም። የሰኔ ዶሮዎች መሆናቸውን አለማወቃቸው እየገረመኝ ነው እንጂ።

የሰኔ ዶሮ የቅዱስዮሐንስ ዶሮ ሲታረድ አይጨንቀውም። የመስቀል ዶሮ ሲታረድም አኩኩሉውን ይቀጥላል። የጥምቀት ዶሮ፣ የፋሲካ ዶሮዎች ሁሉ ሲታረዱ ደንታው አይደለም። ማረጃው ሲደለደል፣ ቢላዋው ሲፋጭ፣ ውሃ ሲጣድ ቀጣዩ ተረኛ እሱ የሚሆን አይመስለውም። በመጨረሻ ሁሉንም አስበልቶ እሱም ተራውን ጠብቆ ይበላል። እነ ኣይተ ጌታቸውን ሳያቸው፣ የሰኔ ዶሮዎች የሚመስሉኝ ለዚያ ነው።
የአሁኑ የህወኀት እነ ኣይተ ጌታቸውን የማባረር ውሳኔ ግን፣ በተለያየ ጊዜ የራሱን ምስለኔዎች እየሾመ ሕዝቡን መግዛት ያቃተው አብይ አህመድ፣ በእነ ኣይተ ጌታቸው ተጠቅሞ የትግራይን ህዝብ ረግጦም ሆነ ከፋፍሎ አሊያም አጭበርብሮ መግዛት እንደማይችል በማያሻማ መንገድ የተነገረ አቋም ነው።

የህወኀት ውሳኔ ያረጋገጠው የጨቋኝ መንግሥትንና ተላላኪዎቹን ሳይሆን፣ የሕዝብን የበላይነት ነው። ሥልጣን የሚገኘው ከሕዝብ እና ለሕዝብ እንጂ በባለጊዜ ሹመት አይደለም ነው።

ህዝብን በባጀት ድጎማ አፉን ሸብቦ ጠምጄ ልጋልብብህ ማለት አይቻልም። ህዝብን በጦርነት እያስፈራሩ አናትህ ላይ ተፈናጥጬ ልግዛህ ማለት አይቻልም - እያሉት ነው።

ተቀጣሪ አይደለንም። ተላላኪ አይደለንም። ራሳችን በመረጥናቸው መሪዎች፣ ራሳችንን እናስተዳድራለን፣ ትግላችን ሁሉ ለዚሁ ነው - ነው እያሉ ያሉት! የእጃዙር ቅኝ አገዛዝን እንቃወማለን ነው የማይዛነፍ አቋማቸው። ይሄ ደሞ መሠረታዊ የዜግነት መብት ነው! ይሄ ደሞ ህወኀት ለዝንተ ዓለሙ አነግቦት የቆየው መስመሩ ነው።

መድፍና አውሮፕላን መንፈሱን ያልሰበረው ሕዝብ፣ ጥቂት የአረመኔው ተላላኪዎች የሚፈጥሩት ይሉኝታ-ቢስ ግርግር ጥንካሬውን ሊሰብረው የሚችል አይመስለኝም!

ደግሞ እነዚህን የህወኀት ሰዎች የማደንቃቸው ረግተው የሚራመዱ በመሆናቸውም ጭምር ነው። ትዕግሥተኞችና ጀግኖች ናቸው። ልባሞች ናቸው። የሚያደርጉትን ያውቃሉ። አስተውለው፣ ተጠንቅቀው፣ ተማክረው ነው የሚራመዱት። ለእጀ-ረዥም አምባገነን፣ መድኃኒቱ ይኸው ነው! አደንቃቸዋለሁ።

ብዙ ጊዜ የተለያየ ትርጉም ሲሰጠባይም፣ በበኩሌ ያ የጥንቱ የጠዋቱ "መስመር እዩ ሓይልና" የተሰኘ መዝሙር፣ የሚገርም የፅናትና የአርበኝነት መንፈስ የያዘ ሆኖ አገኘዋለሁ።
በዚህ መዝሙር ስንኞች ውስጥ፣ የህወኀቶችን ለምንምና ለማንም የማይበገር የጀግንነት መንፈስ አያለሁ። አንድ ሕዝብ ራሱን አጀግኖ ያሰበበት ለመድረስ፣ እነዚህን የቁርጠኝነት ቃሎች አንግቦ መነሳት፣ እና ለዘለዓለም አለመርሳትም የግድ ነው።

እነዚህን ለማንኛውም ኢትዮጵያዊ የጀግንነትንና የአልንበረከክምጰባይነትን ፅኑ መንፈስ የሚያበድሩ የመዝሙሩን ስንኞች በትግርኛም፣ በአማርኛም አቅርቤ ተለየሁ።

የእነ ደብረፅዮን የአሁን አቋምም ይሄን በመዝሙሩ የተገለፀውን ስለሚመስለኝም ነው ያስታወስኩት! አቋማቸው ለአረመኔ የማይንበረከክ፣ የጀግና አቋም ሆኖብኝ ነው ግጥሙን መጋበዜ።
በተረፈ በሬ ለአስተያየት ክፍት ነው። ማንኛውንም ዓይነት አስተያየት መስጠትም መብት ነው። አከብራለሁ።

ግጥሙን ተጋበዙልኝ እያልኩ፣ ሰናይ ጊዜን ተመኝቼ ተለየሁ!

መስመር እዩ ሓይልና
_______________
«ዘይንድይቦ ጎቦ ዘይንሰግሮ ሩባ
መንጉሕ… ፍፁም ወይ ከ የለን፣
መስመርዩ ሓይልና ህዝቢ’ዩ ሓይልና
ወይ ከ ኣይንምብርከኽን፣
ሃሩር ፀሓይ ነዳድ ህቦብላ ማይ በረድ
ማይ ማይ ትበል ነብሲ ኣብ ጀቕጀቕ ንረግረግ፣
ደንጎላ ንትርኣስ በዓቲ ይኹን ቤትና
ለይትን ቀትርን ጉዕዞ ንድከም ይጥመየና፡፡
መስመር’ዩ ሓይልና ህዝቢ’ዩ ሓይልና ወይከ ኣይንሰዓርን
ዘይንድይቦ ኀቦ ዘይንሰግሮ ሩባ
ፍፁም ወይ ከ የለን፣
መስመር’ዩ ሓይልና ህዝቢ’ዩ ሓይልና
ወይ’ከ ኣይንብርከኽን፣
ንከበብ በዛብእ መሬት ትፅበበና
ኣብ ስጋና ይቀርቀር ኣስናን ፀላእትና፣
ስጋና ንኣሞራ ደምና ውሕጅ ይኹን
ኣዕፅምትና ይድቀቕ ሕሩጭ ኮይኑ ይበተን፡፡
መስመር’ዩ ሓይልና ህዝቢ'ዩ ሓይልና ክባታት ፀላኢ ክንፍንፅሖ ኢና
ዘይንድይቦ ኀቦ ዘይንሰግሮ ሩባ
ፍፁም ወይ ከ የለን፣
መስመር’ዩ ሓይልና ህዝቢ’ዩ ሓይልና
ወይ ከ ኣይንብርከኽን፣
ናይ መድሓርሓርቲ ጋዝ ፋሽሽታዊ ንዳድ
ሚልዮን ቁምቡላታት ኣብ ቅድሜና ይንጎድ፣
መስዋእትን መቑሰልትን ክሳራታት ንኽፈል
ዝኽፍኦ መከራ ውዲታት ይፍተልተል፡፡
መስመር’ዩ ሓይልና ህዝቢ'ዩ ሓይልና ክባታት ፀላኢ ክንፍንፅሖ ኢና»
🥀🥀🥀🌺🌺🌺🌼🌼

የመዝሙሩ የአማርኛ ትርጉም ቀጥሎ የቀረበው ነው፡-
________________________________
«መስመራችን ኃይላችን
’ማንወጣው ተራራ፣ ’ማንሻገረው ወንዝ
ፍጹም የትም የለም!
ዓላማ ግባችን፣ ሕዝብ ነው ኃይላችን፣ ከቶ አንሸነፍም!
የፀሐዩዋ ንዳድ፣ የበረዶ ወጀብ፣ ይዝነብ ከላያችን
በጥም እንቃጠል፣ ረግረግ ይያዘን፣
ድንጋይ እንንተራስ፣ ዋሻ ቤት ይኹነን
በሌት ተቀን ጉዞ፣ እንድከም ይራበን፡፡
ዓላማ ግባችን፣ ሕዝብ ነው ኃይላችን፣ ከቶ አንሸነፍም!
ዓላማ ግባችን፣ ሕዝብ ነው ኃይላችን፣ ከቶ አንሸነፍም!
’ማንወጣው ተራራ፣ ’ማንሻገረው ወንዝ
ፍጹም የትም የለም!
ዓላማ ግባችን፣ ሕዝብ ነው ኃይላችን፣ ከቶ አንሸነፍም!
በጅቦች ተከበን፣ መውጫ መግቢያ እንጣ
የጠላታችን ጥርስ፣ ከሥጋችን ይግባ፣ እንደሾኽ ጋሬጣ፣
ሥጋችን ላሞራ፣ ደማችን ወንዝ ይሁን
አጥንታችን ይድቀቅ፣ በነፋስ ይበተን፣
መስመር ነው ኃይላችን፣ የጠላት ከበባን ፣ መሐሉን ሰንጥቀን
አይቀር ማለፋችን!
’ማንወጣው ተራራ፣ ’ማንሻገረው ወንዝ
ፍጹም የትም የለም!
ዓላማ ግባችን፣ ሕዝብ ነው ኃይላችን፣ ከቶ አንሸነፍም!
የአድሃሪያን ጋዝ፣ ፋሺስታዊ ንዳድ፣ ሺ ሚልዮን ፈንጂ፣
ይፈንዳ ከኛ ፊት፣
እንክፈል ኪሣራ፡- ሞት፣ ቁስለት፣ እንግልት
የከፋ መከራ፣ ሤራም ይጥፋ፣ ይሙት፣
መስመር ነው ኃይላችን፣ የጠላት ከበባን ፣
መሐሉን ሰንጥቀን አይቀር ማለፋችን!
አይቀር ማለፋችን!»
መልካም አዲስ ዓመት!🙏💙
አበቃሁ።
_________________







Re: "በአብይ ጭምብሎች ትግራይ አትደፈርም..." ዶር ደብርጽዮን ገብረሚካኤል!!

Posted: 21 Sep 2024, 12:10
by Wedi
ዶር ደብረፅዮን ከህዝብ ጋር እየተወያየ ነው!

ድል ለዶር ደብረጽዮን!!


Please wait, video is loading...
Please wait, video is loading...

Re: "በአብይ ጭምብሎች ትግራይ አትደፈርም..." ዶር ደብርጽዮን ገብረሚካኤል!!

Posted: 21 Sep 2024, 12:47
by Affable
እንዴት ያለ ነገር ነው። Wediን መቼ ትግሪኛ አስተማሩት ? ደሞስ ምንአገባው በትግራይ የውስጥ ፓለቲካ። ልክ እንደ አድዋ ሰው የደብረፅዪን ቲፎዞ መሆኑ ምን የሚሉት ነው። ዝም ብሎ በ “አማራነቱ” የ ፋኖ ቼ በለውን መደለቁን ይልቅስ ቢቀጥልበት አይሻልም።

Re: "በአብይ ጭምብሎች ትግራይ አትደፈርም..." ዶር ደብርጽዮን ገብረሚካኤል!!

Posted: 21 Sep 2024, 17:21
by Right
Getachew will be killed. The Adwa boys are waiting for the right time. It is possible Debrit may start talking to the clown on his own terms.
The fat boy is trusting the clown. A big mistake.

Re: "በአብይ ጭምብሎች ትግራይ አትደፈርም..." ዶር ደብርጽዮን ገብረሚካኤል!!

Posted: 21 Sep 2024, 23:18
by Right
ኣይተ ጌታቸው ያላወቀው አንድ ነገር፣ አረመኔው አብይ አህመድ ጠንካራ አቋም ያላቸውን የህወኀት ሰዎች (እነ ዶክተር ደብረፅዮንን) በእነ ኣይተ ጌታቸው አማካይነት ካስወገደ በኋላ፣ ትግራይን በእጁ አስገብቶ መጫወቻ ነው የሚያደርጋት።

Re: "በአብይ ጭምብሎች ትግራይ አትደፈርም..." ዶር ደብርጽዮን ገብረሚካኤል!!

Posted: 22 Sep 2024, 02:58
by Wedi
Right wrote:
21 Sep 2024, 23:18
ኣይተ ጌታቸው ያላወቀው አንድ ነገር፣ አረመኔው አብይ አህመድ ጠንካራ አቋም ያላቸውን የህወኀት ሰዎች (እነ ዶክተር ደብረፅዮንን) በእነ ኣይተ ጌታቸው አማካይነት ካስወገደ በኋላ፣ ትግራይን በእጁ አስገብቶ መጫወቻ ነው የሚያደርጋት።
This woman is really Sharpshooter!


Re: "በአብይ ጭምብሎች ትግራይ አትደፈርም..." ዶር ደብርጽዮን ገብረሚካኤል!!

Posted: 22 Sep 2024, 06:59
by Right
መድፍና አውሮፕላን መንፈሱን ያልሰበረው ሕዝብ፣ ጥቂት የአረመኔው ተላላኪዎች የሚፈጥሩት ይሉኝታ-ቢስ ግርግር ጥንካሬውን ሊሰብረው የሚችል አይመስለኝም!
Quote and quote.

Re: "በአብይ ጭምብሎች ትግራይ አትደፈርም..." ዶር ደብርጽዮን ገብረሚካኤል!!

Posted: 22 Sep 2024, 07:08
by Wedi
Right wrote:
22 Sep 2024, 06:59
መድፍና አውሮፕላን መንፈሱን ያልሰበረው ሕዝብ፣ ጥቂት የአረመኔው ተላላኪዎች የሚፈጥሩት ይሉኝታ-ቢስ ግርግር ጥንካሬውን ሊሰብረው የሚችል አይመስለኝም!
Quote and quote.

Right, listen to this sharpshooter woman:

"ጌታቸው ረዳ በረሃብ እየተሰቃየ ላልው የትግራይ ህዝብ ይዞለት የመጣው የአብይ አህመድን የአዲስ አበባ የኮርደር ልማት ወደ መቀሌ የኮሪደር ልማት ብሎ ነው፡፡ ከዚህ የበለጠ ተላላኪነት ከየት ይገኛል" :oops: :oops:



Re: "በአብይ ጭምብሎች ትግራይ አትደፈርም..." ዶር ደብርጽዮን ገብረሚካኤል!!

Posted: 22 Sep 2024, 10:37
by Right
What is Getachew Reda looking for? Death. If Abiye the clown betrayed Issias Afeworki, Amhara Liyu, Fano and the Amhara people as soon as he felt he pinned down the TPLF then what did Getachew thinks the clown would do to him.
What a fool.
Debretsion has no choice but to pull the trigger and finish off the fat boy.

Re: "በአብይ ጭምብሎች ትግራይ አትደፈርም..." ዶር ደብርጽዮን ገብረሚካኤል!!

Posted: 22 Sep 2024, 10:52
by Right
Wedi,
Corridor is a lipstick on an ugly pig. No food in Tigray and they are talking about corridor development a.k.a.Abiye’s pet project. A distraction. The lady is right.
Hey she also thinks that the Pretoria deal was worked out between two separate governments as equal participants.
What a load of crap. After a loss of one million souls and half of Tigray’s land Getachew and co didn’t figure out the clown.
Mark my word, Getachew will be killed. Who will do it first? Debretsion or the clown remains to be seen.

Re: "በአብይ ጭምብሎች ትግራይ አትደፈርም..." ዶር ደብርጽዮን ገብረሚካኤል!!

Posted: 22 Sep 2024, 16:24
by Right


Quote and quote

Re: "በአብይ ጭምብሎች ትግራይ አትደፈርም..." ዶር ደብርጽዮን ገብረሚካኤል!!

Posted: 22 Sep 2024, 16:29
by Right
ጌታቸውና ቡድኑ በሃሳብ ተለይቶም ቢሆን ራሱን ችሎ የቆመ ቢሆን ኖሮ እኮ ችግር አልነበረውም። ግን የትግራይን ህዝብ በጅምላ ከጨፈጨፈው ከአብይ አህመድ አምባገነን መንግሥት ጋር ተዳብሎ (ተለጥፎ) ነው ሌሎቹን አንንበረከክም ያሉትን ጓዶቹን ለማስወገድና ለማስመታት የቆመው።
Quote and quote