Page 1 of 1

የህወሐት ሰዎች የጭካኔያቸው ጥግ እዚህ ደርሷል

Posted: 07 Sep 2024, 12:11
by Digital Weyane
የህወሐት ሰዎች የጭካኔያቸው ጥግ እዚህ ደርሷል



ሰሓርቲ ሳምረ ወረዳ ውስጥ ማርያም ሞቐና ዓዲ ሽሻን የሚባሉ ሑለት ሰፋ ሰፋ ያሉ የገጠር ቀበሌዎች አሉ፡፡ በነዚሁ ሑለት ቀበሌዎች የዛሬ ወር ገደማ "እርዳታ ውሰዱ" ተብሎ ሕዝቡ ይጠራል፣ እርዳታ ወደሚሰጥበት ማእከልም ይሰባሰባል፡፡

የሚከፋፈለው 15 ኪሎ እህል እና 4 ሊትር ዘይት ለያንዳንዱ ቤተሰብ ነው።

እህልና ዘይት እናገኛለን ብሎ ተስፋ አድርጎ የመጣው ሕዝብ ዱብ ዕዳ ሆነ ትእዛዝ ከወረዳዋ ሐላፊ ይመጣበታል፡፡

“ይህንን እርዳታ መውሰድ የምትችሉ አሁኑኑ 200 ብር የማዳበርያ ግዢ፣ 142 የጤና መድሕን ክፍያ (በአጠቃላይ 342 ብር) ከከፈላችሁ ነው” ብሎ ህዝቡን ኩም አደረገው፡፡

ሕዝቡ ያልተዘጋጀበት ጉዳይ ነበር፡፡

ሕዝቡ “እኛ በዚች ቅጽበት 342 ብር ከየትም አናገኝም፣ ደግሞም አሁንን ነፍሳችንን ለማትረፍ የመጣ የእርዳታ እህልና ክፍያው አንዳች የሚያገናኛቸው ነገር የለም፡፡ እርዳታውን ስጡን፣ ክፍያውን ግን ቀስ ብለን አፈላልገን እንክፈል” አለ፡፡

የወረዳው ሐላፊ “ካልከፈላችሁ የሚሰጥ አንዳች እርዳታ የለም” ብሎ ቁርጡን ተናገረ፡፡

ሕዝቡም ወደ ቀየው ተበታተነ፡፡

ለሕዝብ ተብሎ የመጣው እህልና ዘይት ግን አንድ ክፍት ሜዳ ላይ በዘበኛ እየተጠበቀ ነበር፡፡ ይህ ከሆነ ከሶስት ቀን በኃለ ከፍተኛ ዝናብ በመጣሉ ለእርዳታ የመጣው እህል በዝናቡ ተበላሸ፣ ከጥቅም ውጪ ሆነ፡፡


ጆ ባይደን ኡኡኡኡኡኡኡኡኡ ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ :cry: :cry: :cry: :cry: