Page 1 of 1

በደቡብ ኢትዮጵያ የመንግሥት ሠራተኞች ደሞዝ ክፍያ መቅረት እና ያስከተለው ቀውስ

Posted: 03 Sep 2024, 11:20
by Za-Ilmaknun
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ውስጥ በሚገኙ 21 ወረዳዎች ተቀጥረው በማገልገል ላይ የነበሩ የመንግሥት ሠራተኞች የወር ደሞዛቸው ለረዥም ጊዜ በመቁረጡ ለኢኮኖሚያዊ እና ማሕበራዊ ችግሮች ተጋለጣቸውን አስረድተዋል::ወላይታ ዞን የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ ስለማይከፈላቸው አንዳንድ መምህራን የተማሩባቸውና ሲያገለግሉበት የነበረውን ሞያ ትተው በግብርና ሥራ መሰማራታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ::

በዳሞት ወይዴ ወረዳ ብቻ ከ3ሺህ በላይ ሠራተኞች ለወራት ደመወዛቸው ባለመከፈሉ ቤተሰቦቻቸውን ማስተዳደር እንደተሳናቸውና ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውን ዘርዝረዋል::

ከደሞዝ አለመከፈል ጋር በተያያዘ በዳሞት ወይዴ ወረዳ ያሉ አራት ጤና ጣቢያዎች እና አንድ ሆስፒታል በመሉ አቅሙ አገልግሎቶችን እየሰጡ አለመኾናቸው እና በዚህም የተነሳ የአከባቢው ማህበረሰብ የጤና እና ትምህርት አገልግሎቶችን የማግኘት መብት መጣሱን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በትላትናው ዕለት ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል::

https://amharic.voanews.com/a/7768782.html

Re: በደቡብ ኢትዮጵያ የመንግሥት ሠራተኞች ደሞዝ ክፍያ መቅረት እና ያስከተለው ቀውስ

Posted: 03 Sep 2024, 13:21
by sesame
Abiy is more interested in building a $10 Billion palace and corridors in Addis! He can't be bothered about paying wages to his poor people!