ኩሳ አቧራዉን ኣራግፎ ሲነሳ
Posted: 27 Aug 2024, 17:02
እንኳን ኢትዮጵያ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ፣ እስከ ምስራቅ ኣፍርካ ዉቅያኖስ ደምበል ደምበል ነዉ። ማዕበላዊ ይሆናል ማለት ነዉ። የረጅም ግዜ ደምበል ደምበል ወይም ማዕበል።
ብዙዎቻችን ኢትዮጵያ ጥንታዊ ሃገር ናት ስንል ያለ ምክንያት ኣይዴለም።
ከብዙ ዓመታት በፊት፣ እዚህ ፎረም ላይ መሳተፍ ሳልጀምር በፊት ለመጀመርያ ግዜ በኦሮምኛ እና እንግልዘኛ ቋንቋዎች ዉስጥ ተመሳሳይነታቸዉን ካስተዋልኩኝ ቃላት መካከል ኩት እና ከት ኣንዱ ነዉ።
እንግልዘኛን የማያዉቅ ከት የሚለዉን ኩት ብሎ ይሳሳት ይሆናል። ምናልባትም ጥንታዊዉን ቃል በትክክል ተናገረ ማለት ይቻላል።
የሁለቱን ቃላት ተመሳሳይነት ብዙ ግዜ እያስታወስኩኝ አማርኛ ዉስጥ እንዴት እንደሌለ እንቆቅልሽ ሆኖብኝ ሰነበተ።
ይህ እንቆቅልሽ ከጥቂት ቀነት በፊት የተፈታልኝ ይመስለኛል።
ቁረጥ የሚለዉን ቃል ኣስታዉሼ፣ የቀ እና የከ መለዋወጥን፣ እንዲሁም የተ እና የጠ መለዋወጥን ኣስታዉሼ ጉድ ነዉ ኣልኩኝ። በቀላሉ ቁረጥ መሠረቱ ኩረት ሊሆን ይችላል ወይ ብዬ እራሴን ጠየኩኝ። ከሆነ ከኩረት ዉስጥ ረ ቢቀር ኩት ይሆናል። ይህ ማላት ቃሉ ወደ መሠረቱ ገባ ማለት ነዉ ወይ ብዬ ተደነኩኝ።
እኔ የዚህ ጥናት መስክ ባለሙያ ኣይዴለሁም። አቤ አብረሃም እና ሆረስ የመስኩ ልሂቃን መሆናችሁን እዚህ መድረክ ላይ ኣንብቤኣለሁ።
ምን ይመስላችኋል?
ኩት፣ ቁረጥ፣ እና ከት መሠረታቸዉ ኣንድ የሆነ ቃል ሊሆን ይችላል? መሆን ከቻለ ቃሉ የማን ነዉ የሚባለዉ? የኦሮምኛ ተናጋሪ ነዉ? የአማርኛ ተናጋሪ ነዉ? የእንግሊዘኛ ተናጋሪ ነዉ?
በትግርኛ ቁረጽ የሚል ቃል የሰማሁኝ ይመስለኛል። በጉራግኛስ ቁረጥ ምንድነዉ የሚባለዉ?