
***********
ፌደራል ፖሊስ ነሀሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከአዲስ አበባ መቀሌ ለጉዞ በተዘጋጀ አውሮፕላን ውስጥ የአቪዬሸን አሰራርን በጣሰ መንገድ ግርግርና ወከባ በፈጠሩ 6 ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብር ወንጀል ምርመራ መጀመሩን አስታወቀ።
ተጠርጣሪዎቹ፦
• ዮሀንስ ዳንኤል በርሄ፣
• አማኑኤል መውጫ አብርሃ፣
• ናትናኤል ወንድወሰን ሹሜ፣
• ኤልያስ ድሪባ በዳኔ፣
• ይዲድያ ነጻነት አበበ እና
• እሌኒ ክንፈ ተክለአብ ናቸው።


