Page 1 of 1
እታማዦር ሹሙ ለምን ብሎ ይሁን ቤኒ ሻንጉል ጉምዝ የሄዱት?
Posted: 23 Aug 2024, 16:26
by DefendTheTruth
እታማዦር ሹሙ ለምን ብሎ ይሁን ቤኒ ሻንጉል ጉምዝ የሄዱት? አለን ለማለት ይሁን?
ሰሞኑን እንደዚሁ ኦጋዴን አከባቢም ታይቶ ነበር፣ ጠረፍ ጠረፉን እየቃኙ ናቸዉ ማለት እንችላለን?
Posted: 23 Aug 2024, 16:37
by eden
ድንቄም የገፅታ ግንባታ - ሰዉን ነፃ ልቀቁትና ዳቦ ቤት አይደለም ሌላ ግድብ ይሰራል
በ1 ዳቦ ቤት የሚደነቅ መንግስት lol
የገፅታ ግንባታዉን ሆረስን ታታልልበት እንደሆን እንጂ ሰዉ ከባነነ ሰነባበተ
Re:
Posted: 23 Aug 2024, 16:53
by DefendTheTruth
eden wrote: ↑23 Aug 2024, 16:37
ድንቄም የገፅታ ግንባታ - ሰዉን ነፃ ልቀቁትና ዳቦ ቤት አይደለም ሌላ ግድብ ይሰራል
በ1 ዳቦ ቤት የሚደነቅ መንግስት lol
የገፅታ ግንባታዉን
ሆረስን ታታልልበት እንደሆን እንጂ ሰዉ ከባነነ ሰነባበተ
eden,
እኔ እኮ አንቺን ንቄ ከተዉኩሽ ቆየሁኝ፣ ዝም ብለሽ የመጣልሽን ወርዉረሽ ዞር ነዉ ከዚያ ቦኋላ። የሰብዕና ጉድለት አለ በግልፅ።
አንድ ዳቦ ቤት ሳይሆን፣ 12 ዳቦ ቤቶች ተሰርቶዋል፣ እስከአሁን። አይ ይህ ብዙ አይደልም ከልሽ ደግሞ እስኪ መስረጃሽን አቅርብ ና እንማመርበት፣ ዳሩ ግን ዝር አትይም!
12 ዳቦ ቤቶች ብቻ ሳይሆን፣ 30 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እስከ አሁን ተመርቆ ስራ ጀምሮዋል፣ አይ ይህም ብዙ አይደልም ከልሽ ደግሞ፣ እስኪ 30 ይቅርና 15 የሰራዉን የቀድሞ ቀዳማዊት እመቤት ጥቀሺ፣ ዳሩ ግን ዝር አትይም! ጊዜዬን አታባክኝብኝ!