Page 1 of 1

የኢትዮጵያ አጀንዳና የአረንጓዴነት ባህል

Posted: 22 Aug 2024, 14:14
by Horus
እኔ ሆረስ ከ1992 ዓም ጀምሮ የአገሬን ፖለቲካ የምመለከትበትና አቋሜን የምመራበት የራሴ የሆነ የኢትዮጵያ አጀንዳ አለኝ። ይህም አጀንዳ የሚከተለው ነው ።
1
ኢትዮጵያ የምትባለው ሕዝብና አገር ብሄራዊ አንድነቷ የጸና፣ ጠንካራና የተረጋጋች (እስቴብል) አገር ማድረግ፤
2
ኢትዮጵያዊ የተባለው ሕዝብ እንደ አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ (Political Community) ፍትህ (እኩልነት)፣ ነጻነት እና ዴሞክራሲ የሰፈነባት አገር ማድረግ፤
3
ኢትዮጵያዊያን የሚባሉት ሕዝብን፣ ዜጋዎችን የበለጸጉ፣ ያደጉ፣ የለሙ፣ የተማሩ እና ጤንነታቸው የተጠበቀ ሕዝብ ማድረግ፤
4
4ኛው የኢትዮጵያ ብሄራዊ አጀንዳ የሚፈጥር፣ ችግር የሚፈታ፣ የሚራመድ፣ ከከባቢውና ኢኮሎጂው ጋር የታረቀ፣ አፈሩን፣ ዉሃውን፣ እንሳሳውን፣ እጸዋቱን፣ አየሩን በሃላፊነት የሚንከባከብ ፣ መንፈሳዊ ፣ በፈጣሪ ኃይል የሚያምን በሞራልና ስነ ምግባር ምርሆዎች የተለጎመ ካልቸር መፍጠር፣ መገንባት እና መጠበቅ ነው።

የዚህ አጀንዳ 4ኛ ክፍል ኢትዮጵያ ምን አይነት ባህል ወይም ካልቸር ይኑራት የሚለው ነው። የሚፈጥር ፣ አረንጓዴ፣ ኤቲካል (መልካም ስነ ምግባር) አንድ መንፈሳዊ ካልቸር ያስፈልጋታል የሚለ ነው ።

የኢትዮጵያ ካልቸር ፈጣሪ ፣ ፍለሳፊ ከመሆኑ ቀጥሎ ያለው የአረንጓዴነት ካልቸር ነው ። ይህ የአረንጓዴነት ካልቸር እኛ ሰዎች ከምንኖረበት አለም ጋር በፍቅርና መደጋገፍ የምኖርበት ችሎታ ነው። ይህም ማለት የአገራችንን እንሰሳዎች፣ እጸዋቶች፣ አፈር፣ ዉሃዎች፣ አየር፣ መጠበቅ ፣ መንከባከብ ማለት ነው።

ኢትዮጵያን አረንጓዴ ማልበስ አንድ እጅግ ግዙፉ የኢትዮጵያ ክላቸርና ያገር አጀንዳ ነው።

ኢትዮጵያ የ21ኛ ዘመን የዉሃ ስልጣኔ ትሆናለች ። በታሪክ ውስጥ በእርሻ፣ ኢንዱስትሪና ቴክኖሎጂ ላይ ግዙፍ ስልጣኔ ያቆሙ አገሮች አሉ ። በአለም ላይ ግዙፍ የማዕድን ፣ የነዳጅና የደን ጥሬ ሃብት ያላቸው አገሮች አሉ ።

የኢትዮጵያ ዘላለማዊ የማያልቅ ግዙፍ ጥሬ ኃብቷ ዉሃ ነው። ዉሃ ለሰው ልጅ ሕይወትና ለአገር ልማት ያለው ወሳኝነት እዚህ መዘርዘር አያስፈልግም። የነጥቡ ቁም ነገር ኢትዮጵያ የወንዞችና ውሃዎች ኔትወርክ ወይም መረብ ነች ፣ መላው ምስራቅ አፍሪካና ቅርብ ምስራቅን እስከ ሰሜን አፍሪካን የምታጠጣ ስልጣኔ ትሆናለች ።

ይቺ ዛሬ አረጓዴ የምትለብሰዋ ኢትዮጵያ አፈሯን በ እጸዋት ሸፍና በዝናብ ከመታጠብ መጠበቅ ብቻ ሳሆን ኢትዮጵያ እራሷ በውሃ ተትረፍርፋ ይህን የዘመናችን ነጭ ወርቅ ለአለም ገበያ ታቀርባለች ።

ስለዚህ የአረንጓዴነት ካልቸር ወደ ዉሃ ጥሬ ሃብት ተለውጦ የዘመናችን ነጭ ወርቅ ይሆናል!

አረንጓዴ ኢትዮጵያ ከአባይ ግድብ እኩል የምደግፈው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም አጀንዳ ነው!

viewtopic.php?f=2&t=337752

Re: የኢትዮጵያ አጀንዳና የአረንጓዴነት ባህል

Posted: 22 Aug 2024, 14:22
by Horus

Re: የኢትዮጵያ አጀንዳና የአረንጓዴነት ባህል

Posted: 22 Aug 2024, 14:27
by Horus

Re: የኢትዮጵያ አጀንዳና የአረንጓዴነት ባህል

Posted: 22 Aug 2024, 14:45
by Horus
እና ኢትዮጵያ ምን ብትመስል ጥሩ ነው?

አረንጓዴ ባላገርና የተዋበ ከተማ! በቃ!



Re: የኢትዮጵያ አጀንዳና የአረንጓዴነት ባህል

Posted: 22 Aug 2024, 16:14
by Horus
አረንጓዴ ፤ የተቀደሰ ካልቸር! ኢትዮጵያን ምርጥ አገር የሚያደርጋት የጤንነት ችሎታ ! አረንጓዴነት ጤነኝነት :idea: :idea:


Re: የኢትዮጵያ አጀንዳና የአረንጓዴነት ባህል

Posted: 22 Aug 2024, 17:20
by Horus

Re: የኢትዮጵያ አጀንዳና የአረንጓዴነት ባህል

Posted: 22 Aug 2024, 18:39
by Horus
ኢትዮጵያ ምን ትምሰል?

አረንጓዴ ባላገርና ውብ ከተማ! በቃ!


Re: የኢትዮጵያ አጀንዳና የአረንጓዴነት ባህል

Posted: 22 Aug 2024, 18:54
by Horus
የአፍሪካ ቀንድንም እንደ ለጋሃር ፈርሶ መገምባት አለበት ! ባህር አልባ ኢትዮጵያ ክንፍ አልባ ወፍ ማለት ነው!


Re: የኢትዮጵያ አጀንዳና የአረንጓዴነት ባህል

Posted: 24 Aug 2024, 17:12
by Horus

Re: የኢትዮጵያ አጀንዳና የአረንጓዴነት ባህል

Posted: 24 Aug 2024, 17:20
by Horus

Re: የኢትዮጵያ አጀንዳና የአረንጓዴነት ባህል

Posted: 24 Aug 2024, 17:37
by Horus