Page 1 of 1

ከአዲስ አባባዉ የኮሪደር ልማቱ ምን አገኘን?

Posted: 19 Aug 2024, 09:10
by DefendTheTruth
በመሬት ላይ የምናያቸዉ የመሰረተ ልማት ክዉኖች ፡ መንገድ፣ ድልድዮች፣ የዉሃ ና የማብራት መስመሮች፣ የቆሻሻ ማስወገጃ ቱቦዎች፣ መናፈሻዎች፣ ና ሌሎች የመሳሰሉ መሰረተ ልማቶች ና ከተማዋን ለወደፊት በዘላቂነት የምለዉጡዋት ልማቶች።

በመሬት ላይ የማናያቸዉ ና ለአገሪቷ እንዲያዉም የበለጠ ፈይዳ የላቸዉ አቅሞችን አካብተናል።

- የወደ ፊት የመስራት አቅም፣ የማቀድ ና የመፈፀም አቅም፣ የስራ ክሎት ና ባሕል፣ በአገር ዉስጥ አቅም ከዉጪ ስመጡ የነበሩትን ግብዓቶችንና ምርቶችን የመቀየር ና ለአገር እኮኖሚ ትልቅ አቅም የመፍጠር አቅም።

- ከሁሉም በላይ ደግሞ የወጣቶቻችንን የስራ ክሎት ያደበርንበት ና ወደ ፊት ለምናቅዳቸዉ የስራ አላማችን ትልቅ አቅም ፈጥረናል። በዚህ ረገድ የህ ችሎታ ለአገር ብቻ ሳይሆን ወጣቶቻችንን በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ያደርጋቸዋል። ምን ጊዜም የምፈለግ የእጅ ሙያ አግኝቶዋል። የትም አገር ሄዶ ልኖሩበት ይችላሉ። አዉሮፓም ሆነ ሌሎች አገሮች ብሄዱ ተወዳዳሪ የሙያ ክሎት አላቸዉ፣ የወዳደቀ ስራ ሳይሆን በደንምብ ልያስከፍላቸዉ የምችል ሙያ አግኝቶዋል። ትልቅ ትርፍ።

በአዲስ አበባ ላይ የቀሰምናቸዉ ልምዶች ወደ ሌሎች የክልል ከቶሞች መሰራጨት ጀምሮዋል፣ በባሕርዳር፣ በጎንደር፣ በደሴ፣ በአዋሳ፣ በሻሸመኔ፣ በአዳማ፣ በሮቤ ባሌ፣ በአርባ ምንጭ ና ሌሎች ከተሞች ተመሳሳይ ስራዎች ተጀምሮዋል። ግፋ ብል እስከ 10 አመት (በእኔ ግምት ማለቴ ነዉ፣ ከዚያም በፊት ልሆን ይችላል) ዉስጥ ኢትዮጵያ ሌላ አገር ትሆናልች፣ የበለፀገች፣ የምታምር፣ አየሯ የምስብ፣ ሕዝቧ የምመቹ ና እንግዳ ተቀባዮች፣ የአፍሪካ ና ሌሎች አገሮች ዜጎች ለእረፍት ወደ ሷ የምመጡባት አገር ትሆናልች።

ከምያምረዉ ከተማ ም በላይ ይህ ለወደ ፊት የከበትነዉ አቅም ትልቅ ቦታ ይኖረዋል።


Re: ከአዲስ አባባዉ የኮሪደር ልማቱ ምን አገኘን?

Posted: 19 Aug 2024, 09:17
by DefendTheTruth
እኔን ሳይደክመኝ፣ አንተን እንዳይደክምህ፣ ሰርቶ የማሰራት አቅም!

Re: ከአዲስ አባባዉ የኮሪደር ልማቱ ምን አገኘን?

Posted: 19 Aug 2024, 09:26
by DefendTheTruth
አገልግሎትን ከእጅ ማንሻ ነፃ የማድረግ አላማ በአዲስ አባባ!


Re: ከአዲስ አባባዉ የኮሪደር ልማቱ ምን አገኘን?

Posted: 20 Aug 2024, 01:44
by Tadiyalehu
ተባረክ!
እንዳንተ ያለ ለሀገሩ ቀና የሚያስብ ዜጋ ነው የሚያስፈልገን።
ኢትዮጵያን ተባብረን ሀያል እናደርጋታለን።


ጀምረናል!!! ይቀጥላል!!! ይቻላል!!!

Re: ከአዲስ አባባዉ የኮሪደር ልማቱ ምን አገኘን?

Posted: 20 Aug 2024, 15:13
by DefendTheTruth
ሌላዉ የዚህ ልማት ትልቅ ጥቅም ደግሞ የጤና ትሩፋት ነዉ፣ አሁን መንገዱ በላቀ ሁኔታ አመቺ ስለሆነ፣ ሰዎች ይበልጥ ዎክ ያደርጋሉ፣ ወጪ ላይ ይቆያሉ፣ በታክሲ ለትንሽ ርቀት ብሎ አይጋፉም፣ ይህ ደግሞ ለሰዉነትቸዉ ትልቅ ትርፍ አለዉ፣ ይበልጥ ጤነኛ ያደርጋቸዋል፣ የሕይወት ዘመናቸዉ እንድራዘም ያደርጋል፣ ጤነኛ ዚጎችን እናፈራለን፣ ጤነኞች ደግሞ ይበልጥ ይሰራሉ፣ ለአገር እድገት ይበልጥ ያዋጣሉ።

ይህም በቀላሉ የምታይ አይደለም። አመቺ መንገድ አመቺ ኑሮ ይዞ ይመጣል።