በመሬት ላይ የማናያቸዉ ና ለአገሪቷ እንዲያዉም የበለጠ ፈይዳ የላቸዉ አቅሞችን አካብተናል።
- የወደ ፊት የመስራት አቅም፣ የማቀድ ና የመፈፀም አቅም፣ የስራ ክሎት ና ባሕል፣ በአገር ዉስጥ አቅም ከዉጪ ስመጡ የነበሩትን ግብዓቶችንና ምርቶችን የመቀየር ና ለአገር እኮኖሚ ትልቅ አቅም የመፍጠር አቅም።
- ከሁሉም በላይ ደግሞ የወጣቶቻችንን የስራ ክሎት ያደበርንበት ና ወደ ፊት ለምናቅዳቸዉ የስራ አላማችን ትልቅ አቅም ፈጥረናል። በዚህ ረገድ የህ ችሎታ ለአገር ብቻ ሳይሆን ወጣቶቻችንን በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ያደርጋቸዋል። ምን ጊዜም የምፈለግ የእጅ ሙያ አግኝቶዋል። የትም አገር ሄዶ ልኖሩበት ይችላሉ። አዉሮፓም ሆነ ሌሎች አገሮች ብሄዱ ተወዳዳሪ የሙያ ክሎት አላቸዉ፣ የወዳደቀ ስራ ሳይሆን በደንምብ ልያስከፍላቸዉ የምችል ሙያ አግኝቶዋል። ትልቅ ትርፍ።
በአዲስ አበባ ላይ የቀሰምናቸዉ ልምዶች ወደ ሌሎች የክልል ከቶሞች መሰራጨት ጀምሮዋል፣ በባሕርዳር፣ በጎንደር፣ በደሴ፣ በአዋሳ፣ በሻሸመኔ፣ በአዳማ፣ በሮቤ ባሌ፣ በአርባ ምንጭ ና ሌሎች ከተሞች ተመሳሳይ ስራዎች ተጀምሮዋል። ግፋ ብል እስከ 10 አመት (በእኔ ግምት ማለቴ ነዉ፣ ከዚያም በፊት ልሆን ይችላል) ዉስጥ ኢትዮጵያ ሌላ አገር ትሆናልች፣ የበለፀገች፣ የምታምር፣ አየሯ የምስብ፣ ሕዝቧ የምመቹ ና እንግዳ ተቀባዮች፣ የአፍሪካ ና ሌሎች አገሮች ዜጎች ለእረፍት ወደ ሷ የምመጡባት አገር ትሆናልች።
ከምያምረዉ ከተማ ም በላይ ይህ ለወደ ፊት የከበትነዉ አቅም ትልቅ ቦታ ይኖረዋል።