Page 1 of 1

Galla-Abiy Back stabs Getchew Reda.(((HAHAHA))).!!! WEEY GUUD !!!

Posted: 13 Aug 2024, 10:39
by tarik


አወዛጋቢው የህውሓት ድርጅታዊ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ ፡፡

በአወዛጋቢ ሂደቶች የተሞላው የህወሃት ድርጅታዊ ጉባኤ በመቀሌ መካሄድ ጀምሯል፡፡
በሊቀመንበሩ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል(ዶ/ር) የሚመራው ቡድንም ጉባኤውን በመቀሌ ሰማእታት የሃወልት አዳራሽ „ ጉባኤ ድሕነት የመዳን ጉባኤ „ በሚል መሪ ቃል መክፈቻውን እያካሄደ ይገኛል፡፡

ጉባኤው ከዚህ ቀደም በወጣለት መርሀ ግብር መሰረት ከነሀሴ 7 – 12 2016 ዓ.ም እንደሚቆይ ነው የተነገረው።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እና የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ እና ሌሎች በርካታ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በተለያዩ ምክንያቶች ከጉባኤው እራሳቸውን ማግለላቸው ይታወሳል፡፡

የጉባኤውን መከናወን ሲያወግዙ የቆዩት አቶ ጌታቸው ረዳ ከደቂቃዎች በፊት ባወጡት መግለጫ ጉባኤው „ በችኮላና የጋራ መግባባት ሳይደረስበት ፤ በማደናገርና በአቋም አልባነት አሰባስበናቸዋል በሚሉት ኔትወርክ ‚ ይቃወሙናል ‚ የሚሉዋቸው የተወሰኑ አመራሮች ለማስወገድ በማለም የሚካሄድ ጉባኤ ነው „ ብለውታል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለህውሀት በጻፈው ደብዳቤ በፓርቲው መተግበር ካለባቸው ተግባራት መካከል ፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ከማድረጉ ከ21 ቀን በፊት ለቦርዱ ማሳወቅና ፖርቲው በሚያደርገው ጠቅላላ ጉባኤ የቦርዱ ታዛቢዎች መገኘት በዋናነት የተገለፁ ግዴታዎች አለሟሟላቱን ተከትሎ ለጉባኤው እውቅና እንደማይሰጥ አስታውቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከሳምንታት በፊት ህወሃት ከምርጫ ቦርድ እውቅና ሳያገኝ ጉባኤው የሚያከናውን ከሆነ ክልሉን ወደ አላስፈላጊ ግጭት ዳግም ይከተዋል ሲሉ ማሳሰባቸው አይዘነጋም፡፡