
#NewsAlert
“ ቀድሞ የገባውን ግዴታ ሲሸራርፍ የመጣው ህወሓት ዛሬ በተጨባጭ ተግባር ደምስሶታል። ... ይህ ድርጊቱም የትግራይ ህዝብ ያገኘውን አንጻራዊ ሰላም እንደመንጠቅ ይቆጠራል !!
“ - ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)
በሊቀ መንበሩ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ቡድን ጉባኤውን መጀመሩ ይፋ በተደረገበት በዚህ ሰዓት ላይ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) አጭር ግን ጠንካራ መልእክት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አሰራጭተዋል።
በዚህም “ በየትኛውም የዓለም ጥግ ያለ አገር የሚመራው በህግና በስርዓት ነው “ ብለዋል።
“ ህግና ስርዓት ከማንኛውም ሰው፣ ተቋም፣ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ፣ ቡድን፣ ስብስብ በላይ ነው። “ ያሉት ለገሰ (ዶ/ር) “ እነዚህ ሁሉ ከህግ እና ስርአት በታች ናቸው፤ ህግና ስርዓትን አክብሮ የማይንቀሳቀስ የትኛውም አይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ የመጨረሻ ግቡ ጥፋት ነው “ ሲሉ አስገንዝበዋል።
ለገሰ (ዶ/ር) ፥ “ የህወሓት ያለፉት ዓመታት የግትርነት ባህሪም የዚሁ ምሳሌ ነው “ ያሉ ሲሆን “ ህወሓት ደጋግሞ እንደመሸሸጊያ የሚያነሳው የፕሪቶሪያ ስምምነት የፌደራል ተቋማትን አሰራሮች፣ ህጎችና አካሄዶች በጥብቅ ሊያከብር ግዴታ ጥሎበታል “ ብለዋል።
“ ቀድሞ የገባውን ግዴታ ሲሸራርፍ የመጣው ህወሓት ዛሬ በተጨባጭ ተግባር ደምስሶታል፡፡ “ ሲሉ አሳውቀዋል።
“ ድርጊቱ የትግራይ ህዝብ ያገኘውን አንጻራዊ ሰላም እንደመንጠቅ ይቆጠራል፡፡ “ ያሉት ለገሰ (ዶ/ር) “ አንዴ፡ ሁለቴ፡ መሳሳት ያለንና የነበረ ነው፡፡ በተመሳሳይ መንገድ ተመሳሳይ ስህተት ሶስቴ መፈጸም ግን የመጨረሻው የጥፋት መንገድ ነው “ ሲሉ አስንገብለዋል።
“ ለዚህ ደግሞ ብቻኛ ተጠያቂ እራሱ (ህወሓት) ይሆናል “ በማለት ጠንካራ መልዕክት አስተላልፈዋል። See less