ቀባሪ ያጣ ሬሳ (ፍረዝጊ የዕብዮ – ከ አዲስ አበባ)
August 7, 2024
ፍረዝጊ የዕብዮ
አዲስ አበባ
ህወሓት የትጥቅ ትግል ሲጀምር ሁለት መጫወቻ ካርዶች ነበሩት፡፡ አንደኛው ካርድ የትግራይ ሪፐብሊክ መመስረት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የፊደዋል ስርአት ለመታገል ነበር፡፡ ለዚህ ማሳያ ደግሞ የመጀመርያ ዘፎኖቹና ፕሮግራሞቹ ማየት በቂ ነው፡፡
ይሁንና በተለይ ሁለተኛው ካርዱ ሳይጀምር ተቃጠለበት፡፡ ደርግ መሬት ለአራሹ አውጆ አንደኛው ካርዱ ከህወሓት እጅ አስጣለው፡፡ ሁለተኛው ካርዱ ይዞ ለተወሰነ ዓመታት የተተጋለ ቢሆንም የትግራይ ሪፐብሊክ የሚል ካርድ ብዙ ርቀት ሊወስደው አልቻለም፡፡ አንደኛ ከፈጣሪው የኤርትራ ነፃ አውጪ ግንባር አጋጨው ፣ሁለተኛ ደግሞ ከሱ በፊት በአብዛኛው የምስራቅ ትግራይ ተወላጆች በሆኑ በጣም የተማሩ የመሰረቱት ተጋድሎ ሓርነት ትግራይ የሚባል ድርጅት ዓላማ ጋር ግጭት ፈጠረ፡፡ ህዝቡም ነፃ ትግራይ ሪፐብሊክ የምትሉ ከሆነ ከተጋድሎ ሓርነት ትግራይ ተቀላቀሉ የሚል ጥያቄ አቀረበላቸው፡፡
ይሁንና ከኤርትራ ነፃ አውጪ ግንባር ያጋጨው ጉዳይ እና በትግራይ ህዝብ የተነሳበት ከተጋድሎ ሓርነት ትግራይ ተቀላቀሉ ጥያቄ በሁለት መርዛማ እና ድብቅ አካሄዶች ለመፍታት መኮረ፡፡ አንደኛው ከሻዓብያ የገጠመውን ተቃውሞ ለማስታገስ ነፃ ሪፐብሊክ ትግራይ የሚል ዓላማ ትቻለሁ አለ፡፡ ሁለተኛ በህዝብ ለቀረበለትን ጥያቄ ለማለዘብ ከጋድሎ ሓርነት ትግራይ ለመወሃሃድ እነጋገራለሁ ብሎ በሽምግልና ተደራድሮ አንድ ለመሆን ተስማምተው ድግስ ተደግሶ እርቅ ተፈፀም ኣንድ ሆንን ብለው የሰላም እንቅልፍ በተኙ የተጋድሎ ሓርነት ትግራይ አመራሮች በተኞበት አረድዋቸው፡፡ አንበጣ በመከላለከልና በማጨድ የዛለውን ጉልበቱን ለማሳረፍ አገር ሰላም ብሎ በተኛው የመከላከያ ሰራዊት ያደረጉት ተግባር ገና ሲወለዱ የጀመሩት ነው፡፡ እዚህ ላይ በጣም ታሪክ ለወደፊቱ የሚመለከተው ጉዳይ የምስራቅ ትግራይ ተወላጆች የነበሩ ሁሉም ታጋዮች ሲገደሉ የተሓት ሊቀመንበር ጨምሮ ሌሎች የዓድዋና አከባቢዋ ተወላጆች ሳይገደሉ መቅረታቸው ነው፡፡ ታሪኩ ማወቅ ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው የገብሩ አስራት እና አስገደ ገብረስላሴ መፅሃፍቶችን ማንበብ በቂ ነው፡፡
ህወሓት ተሓት ካጠፋ በኋላ ግራጫ ካርድ ይዞ ብቅ ኣለ፡፡ ለሻዓብያ ለዲሞክራሳዊት ኢትዮጵያ ነው የምታገለው እያለ ለትግራይ ህዝብ ደግሞ ለነፃነት ነው የሚታገለው የሚል ሁለት መልክ ያለው ግራጫ የትግል ካርድ አመጣ፡፡ ይሁንና ግራጫ ዓላማው ሄዶ ሄዶ ታጋዩንም፣ ህዝቡንም ሌሎች የውጭ ተመልካቾችም ግራ ስላጋባ ስልጣን ብቻ ዓላማ አድርጎ የወጣው ቡድን ሌላ አደራጋሪ እና መርዘኛ ካርድ ይዞ ብቅ አለ፡፡ የፋሽሽታዊ ስርአት ድርግ ማጥፋት እና የሌኒን ማክስስት ፍልስፍና፡፡
እነዚህ ሁለት ካርዶች ለህወሓት ማደናገርያ ካርድ ቢሆኑም ብዙ ድጋፍ አስገኘላቸው፡፡ አንደኛ ካርዱ በተቻለው መጠን እየጋበዘም ይሁን የይነካካ ደርግ በህዝብ ላይ እንዲጨክን አደረገው፡፡ ፋሽሽት የሚለውን ቋንቋ ከኢህአፓ የወረሰው ቢሆነም ደርግ ህዝብ በተሰበሰበበት ገበያም ይሁን ሃይማኖት ተቋማት ግፍ እንዲፈፅም ሆን ብሎ በመረጃም ይሁን በሌላ እያመቻቸ ደርግ ለማሰይጠን ብዙ ለፋ ህዝብም ከህወሓት ጎን አሰለፈ፡፡ ለምሳሌ ሃውዜን ጭፍጨፋ ብናይ ህወሓት በራሳቸው እንዳስፈፀሙት የራሳቸው ታገዮች አረጋግጠዋል፡፡ ያም ሆነ ይህ ፋሽሽት የሚለውን ደርግ ለማስወገድ ዕድል የረዞለት መጣ፡፡
በሌላ በኩል ምንም እንኳ በደርግና ህወሓት ምንም ዓይነት የፕሮግራም ሊዩነት ባይኖርም የሶሸሻሊዝም ጠላት ሶሻሊስት ሆኖ በመቅረቡ የምዕራቡ ዓለም ድጋፍ አስገኝቶለታል፡፡ ስለዚህ የመጀመርያው ካርድ ደርግ ለማስወገድ ትልቅ አቅም ፈጠረለት፡፡
ሁለተኛው ካርዱ ደግሞ የማለሌት ፍልስፍና ተራማጅ ሃይል ሆኖ እንድታይ እና ዓለም ዓቀፋዊ ፍልስፍና በመሆኑ ህዝብ ለመቀስቀስ ተጠቀመበት ማደናገርያም ሆነ፡፡ ማሌሊት ወጣቶች ለመቀስቀስ ፣ የማይታይ መስመር በማበጀት ጠላቶችን ለማጥፋት ተጠቅሞበታል፡፡ የማርክስስት ሌኒንስት ፍልሰፍና ህዝባዊ ታጋይ ለመፍጠርና እደ ከብት የሚነዳ ታጋይ ለማደራጀት ቁልፍ መሳርያ ነው፡፡ በል የተባለውን የሚል. አድርግ የታባለውን የሚያደርግ፣ የትግራይ ብሎም የኢትዮጵ ክብር የሚያጠፋ አረመንያዊ ስርአት እና ሰራዊት እንዲመሰረት አስችሎታል፡፡
የህወሓት ታጋይ በማለሌት ፍልስፍና የተመሰረት ስለሆነ ሰብአዊ ክብር፣ ማህበራዊ እና ተፈጥራዊ አልነበረውም፡፡ የሱ ክብር ህወሓት ያዘዘውን ማድረግ ብቻ ነው፡፡ በመሆኑም የትግራይ ሃገር ሽማግሌዎች፣ ሃይማኖት አባቶች እና ትላልቅ ሰዎች ያለምህረት ተረሽነዋል እንዲጠፉ ደርገዋል፡፡ አረመንያዊ ሰራዊት በመገንባታቸው አብያተክርስትያናት እና መስግዶች ጥይት ማስቀመጫ ሆነዋል፤ ቄስ ከገደለ አቅደስም የሚለውን ቤተክርስትያን ስርአት በማፍረስ ለዓላማ ተታገለ ቄስ መቀደስ አይከለከልም በምል ህግ ተሸረዋል፡፡ አሁን ትግራይ ሲዋጋ ነበረውን ቄስ ይቀድሳል ይባርካል፡፡ ለዚህ ነው ጳጳሳት ትግራይ ዓለማቀፋዊ ሃይማኖት ትተው ከህወሓት የወገኑት፡፡
ይሁንና ካርድ ማርጀቱ ስለማቅር ሁለቱም ካርዶች ደርግ ሲወድቅ አብረው ተቃጥለዋል፡፡ ህወሓት ሁለቱም ማታገያ ስልቶቹ ከደርግ አብረው ሙተዋል፡፡ ከ1983 ዓ፣ም በኋላ ቀባሪ ያጣ ህወሓት ነው ያለው፡፡ የማሌሊት ፍልስፍና እና ፋሽዝም ደርግ ከሞተ በኋላና ትልቋ ሶቬት ስትፈርስ አከተመለት ፣ህወሓት በቁምዋ ሞተች ፡፡ አልሞት ባይ ተጋዳይ እንደሚባለው ማደናገርያ አብዮታዊ ዲሞክራሲ፣ አሃዳዊ፣ ጠባብ እና ገለ መሌ የሚሉ ማደናገርያዎች ለማምጣት ቢሞከርም አንዴ ሙተዋልና ለመነሳት አስቸጋሪ ነው፡፡
ለዚህ ነው እስከ አሁን ፋሽሽት እያሉ የሚሳደቡት፣ ለዚህ ነው ላይመለስ የተቀበረው ደርግ እያሉ የሚሳደቡት ፡፡ በዚህ ዘመን ደርግም ሆነ ፋሽሽት የሚያውቅ ወጣት የለም ህወሓ ግን ስድቡም ያው ደርግና ፋሽሽት ነው፡፡ ፀማምያስ ሓደ ደርፉ ይባላል በትግርኛ ፡፡ የደንቆሮ ዘፈን አንድ ነው ለማለት ነው፡፡ መለስ ዜናዊ የሚተጣጠፍ ሰው ስለነበር የህወሓት ሬሳ ሳይቀበር ለረዥም ዓመት አቆይቶታል፡፡ አሁን ግን መለስ ለራሱ ተቀብረዋል፤ ከሱ በፊት የሞተው ህወሓ ግን ቀባሪ አጥቶ እስከ አሁን አለ፡፡
በርግጥ የዘር ጉዳይ ተላላፊ በሽታና መቆምያ ስለሌለው ሬሳም ሆኖ ከትግራይ መንደር ደርሰዋል፡፡ ሰሞኑ እንደምነሰማው ዘር ቆጠራው ከብሄር ብረሰቦች አልፎ መንደር ገብተዋል፡፡ ዓድዋና የእንደርታ ሰዎች ጎራ ለይተው እየተፋጩ ነው፡፡ በሁለቱም ጎራዎች ምንም ዓይነት የፕሮግራም ሆነ የዓላማ ልዩነት የለም፡፡ መርዘኛው ዘረኝነት ግን ሬሶችም በማጣላት ላይ ነው፡፡ የሬሳ ጉባኤ እናካህድ አናካህድ የሚለውን ጥል በዓለም ከዚህ በፊት ታይቶ እንደሆነ እኔ አለውቅም ፣በትግራይ ምድር ግን በዚህ ዘመን እያየን ነው፡፡
ሟቹ ህወሓት በህይወት በነበሩ ብአዴን፣ደህዴን እና ኦህዴድ ታግዞ ከ1983 ወዲህ ብዙ ጉባኤዎች አካህደዋል፡፡ ጉባኤዎቹ ግን እዚህ ግባ የሚባሉ አለነበሩም የሟቹ ዘፈን እተዘፈነባቸው ነው ያለፉት፡፡ አሁን ግን ሬሳው ብቻውን ቀረ የሚዘፍንለት ኣጥቶ ጉባኤ እናካህይድ ኣናካህይድ በሚል በመንደር እተጣሉ ነው፡፡
ጉባኤው ቀባሪ የሚገኝበት ወይስ የሬሳው ጠባቂ የሚገኝበት ይሆናል መልሱ ቀይተን የምናውቀው ይሆናል፡፡ ቀባሪ አገኘ ኣለነገኘ ህወሓት ላይነሳ በ17 ዓመቱ በ1983 ጉንበት 20 ሙተዋል፡፡
ሰናይ ቅነ