Page 1 of 1

በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ዋልጋና ዳርጌ ከተሞች የተከሰተው

Posted: 06 Aug 2024, 12:26
by Za-Ilmaknun
ትናንትናው እለት ወደ ስፍራው የገቡ በርካታ የመንግስት ሀይሎች ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ የቤት ለቤት ፍተሻ በማድረግ በዛ ያሉ የአካባቢውን ወጣቶች እና ባለሀብቶች በቁጥጥር ስር እንዳዋሉ ከስፍራው ለመሰረት ሚድያ የደረሰው መረጃ ይጠቁማል።

“ኮማንዶ ፌደራል ፖሊስና የተለያዩ ከባድ መሳሪያዎችን የያዙ የመንግስት ሀይሎች ዛሬ ከጠዋት 11:30 ጀምረው ባለሀብቶች እና ወጣቶችን ፋኖን ታደራጃላችሁ በማለት ሲያፍሱና በኦራል ሲጭኑ ውለዋል” ብለው መረጃ ያደረሱን አንድ የአካባቢው ነዋሪ ናቸው።

ሌላ መረጃ ሰጪ ደግሞ ድርጊቱ መፈፀሙን ጠቁሞ አሁን ከ70 በላይ ሰዎች ለእስር እንደተዳረጉ እና “የጦር መሳሪያ አላችሁ” በሚል የመሳርያ ለቀማ ተከናውኗል ብለዋል።

“ከተሞቹ በአሁን ሰአት ምንም የሚንቀሳቀስ ሰው የለም፣ ማህበረሰቡም ተረብሿል” ያሉት የመሰረት ሚድያ የመረጃ ምንጮች ወረዳው በብዛት የአማራ ብሔር ተወላጆች የሚኖሩበት እንደሆነ ጠቁመዋል።

-መሰረት ሚድያ-

Re: በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ዋልጋና ዳርጌ ከተሞች የተከሰተው

Posted: 06 Aug 2024, 12:52
by Dama
Abiy try your best. You know you are just buying time by your draconian measures.