ህወሓት የክልሉን “መንግሥት የሚያፈርስ ስምምነት ፈርመሃል” ሲል እንደወቀሳቸው አቶ ጌታቸው ተናገሩ
Posted: 30 Jul 2024, 13:32
የፕሪቶሪያው ግጭትን በዘላቂነት የመቋጨት ስምምነት የክልሉን መንግሥት እንዲያፈርስ እንዳደረገው እና ይሄንንም ተግባራዊ አድርገዋል ተብለው በፓርቲያቸው መተቸታቸውን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ገልጸዋል።
ህወሓት “የተደራጀ ስም የማጥፋት ሥራዎች” ሲያካሂድብኝ ቆይቷል ሲሉት አቶ ጌታቸው “በውስጣዊ አለመግባባቶች፣ በፖለቲካዊ ሽኩቻዎች ምክንያት፣ አንዱ የጀመረውን እንቅስቀሴ ሌላው ስም ስለሚሰጠው” ጊዜያዊ አስተዳደሩ ሥራውን መሥራት አልተቻለውም ሲሉ ተናግረዋል።
አሁን መንግሥት አፍርሰው ነው የመጡት እየተባልን ነው። ያኔ ጉዳዩ የመንግሥትነት አልነበረም፤ የትግራይ ሕዝብ በሙሉ በፌደራል ሠራዊት ስር እንዲገባ እጃችሁን ስጡ ስንባል ነው የነበረው። በወቅቱ የህወሓት ሊቀመንበር [ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ] ‘ዛሬ ካልፈረማችሁ ወደ በረሃ መውጣታችን ነው’ ብሎኛል” የሚሉት አቶ ጌታቸው አሁን የሚወቅሷቸው አካላት ስምምነቱን እንዲፈርሙ እንደነገሯቸው ገልጸዋል።
አክለውም “የፕሪቶሪያን ስምምነት በምንፈርምበት ሰዓት ምን ዓይነት ጭንቅ ውስጥ እንደነበርን አስታውሰዋለሁ።አሁን ከአንድ ዓመት ከስምንት ወር በኋላ ያኔ ስምምነቱ ካልተፈረመ አደጋ ላይ እንወድቃለን ሲል የነበረው አካል ‘መንግሥት እንድታፈርሱ ሥልጣን አልሰጠናችሁም - ስህተት ነው’ ሲል ከጅምሩ አልተቀበለውም ነበር ማለት ነው” ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c9r3v12y4xvo