Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Za-Ilmaknun
- Member
- Posts: 4486
- Joined: 15 Jun 2018, 17:40
Post
by Za-Ilmaknun » 30 Jul 2024, 13:32
የፕሪቶሪያው ግጭትን በዘላቂነት የመቋጨት ስምምነት የክልሉን መንግሥት እንዲያፈርስ እንዳደረገው እና ይሄንንም ተግባራዊ አድርገዋል ተብለው በፓርቲያቸው መተቸታቸውን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ገልጸዋል።
ህወሓት “የተደራጀ ስም የማጥፋት ሥራዎች” ሲያካሂድብኝ ቆይቷል ሲሉት አቶ ጌታቸው “በውስጣዊ አለመግባባቶች፣ በፖለቲካዊ ሽኩቻዎች ምክንያት፣ አንዱ የጀመረውን እንቅስቀሴ ሌላው ስም ስለሚሰጠው” ጊዜያዊ አስተዳደሩ ሥራውን መሥራት አልተቻለውም ሲሉ ተናግረዋል።
አሁን መንግሥት አፍርሰው ነው የመጡት እየተባልን ነው። ያኔ ጉዳዩ የመንግሥትነት አልነበረም፤ የትግራይ ሕዝብ በሙሉ በፌደራል ሠራዊት ስር እንዲገባ እጃችሁን ስጡ ስንባል ነው የነበረው። በወቅቱ የህወሓት ሊቀመንበር [ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ] ‘ዛሬ ካልፈረማችሁ ወደ በረሃ መውጣታችን ነው’ ብሎኛል” የሚሉት አቶ ጌታቸው አሁን የሚወቅሷቸው አካላት ስምምነቱን እንዲፈርሙ እንደነገሯቸው ገልጸዋል።
አክለውም “የፕሪቶሪያን ስምምነት በምንፈርምበት ሰዓት
ምን ዓይነት ጭንቅ ውስጥ እንደነበርን አስታውሰዋለሁ።አሁን ከአንድ ዓመት ከስምንት ወር በኋላ ያኔ ስምምነቱ
ካልተፈረመ አደጋ ላይ እንወድቃለን ሲል የነበረው አካል ‘መንግሥት እንድታፈርሱ ሥልጣን አልሰጠናችሁም - ስህተት ነው’ ሲል ከጅምሩ አልተቀበለውም ነበር ማለት ነው” ብለዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c9r3v12y4xvo
-
Za-Ilmaknun
- Member
- Posts: 4486
- Joined: 15 Jun 2018, 17:40
Post
by Za-Ilmaknun » 30 Jul 2024, 13:41
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ : ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ጉባኤ ከማካሄዱ በፊት “በሕጋዊ መንገድ መመዝገብ እንዳለበት” አስጠነቀቀ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማስጠንቀቂያውን የሰጡት ህወሓት “ጠቅላላ ጉባኤ እንዳናደርግ የሚከለክለን ምድራዊ ኃይል የለም የሚል መግለጫ እያወጣ ወደ ትናንትና ፉከራው፣ ወደ በሽታው እየገባ ባለበት ሁኔታ የጊዜያዊ አስተዳደሩ መከለስ የለበትም ወይ?” የሚል ጥያቄ አቶ ከበደ አሰፋ በተባሉ የትንሳዔ 70 እንደርታ ፓርቲ ተወካይ ከቀረበላችው በኋላ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “ህወሓት አሁን ማድረግ ያለበት ምርጫ ቦርድ ጋር ሂዶ በሁለት እና ሦስት ሳምንት ውስጥ የሚጠበቅበትን ሰነዶች አሟልቶ በሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ ወይም ፈቃዱን reinstate [መልሶ አግኝቶ] ነው ጉባኤ ማካሄድ ያለበት” ሲሉ በአጽንኦት ተናግረዋል።